የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

Jun 30, 20181 min

ሐሳብ - ክፍል 02 (በኢዱና አህመድ)

Updated: Jun 9, 2019

ደግሞም እኮ አለኝ ያ…ሃሳብ

በሃሳብ…

ዘመን አልፎ… ዘመን ሲተካ

በደሉ… ጫናው በዝቶ ሰማይ ሲነካ

በሁለት አስርቱ የአብሮነት የይምሰል ጉዞ

ተስፋው ጨልሞ... ትዝታው ደብዝዞ

ያ… እርሷን እርሷን ማለቱ

ከእርሷ ጋር... በርሷ መዋተቱ

ስለእርሷ መልካም… በመልካም ማውጋቱ

ጣዕሙ ተሟጠጠ... አንደበት ተለጎመ

መአዛው ከረፋ... ክጃሎት ከሰመ

ተሰደድ ቢጤውን... አጋሩን ፍለጋ

አዎን ያ… ህሊና ነጎደ ነጻነትን ፍለጋ

እልፍ... ሲሉ እልፍ ይገኛል ነውና

ጨለማውን ገፎ ከሩቅ በፈነጠቀው ፋና

እይታህን ሰፍቶ

ህሊናህ ጠርቶ

ምርጫህ ተበራክቶ

ክጃሎትህ ጸንቶ

የልክህ ከጅህ ገብቶ

ሃሴት በሁለመናህ ተንሰራፍቶ

ተሰራጭቶ...

የአበውን.. ደንብና ልምድ ተከትለህ

ከመላህ... ከትሩፋትህ

ለነዚያ... ለተገፉት ብጤዎችህ ለማጋራት

ካደባባይ ብትወጣ ድምጽህ ለማሰማት

እያለ... አለ ያ... ሃሳብ

እኔም ሃሳብን... በሃሳብ

ሳስብ... ስብሰለሰል በሃሳብ

ያ...ሃሳብ መጣና በሃሳብ

መለሰኝ…

ወሰደኝ…

.

.

.

ይቀጥላል

(በኢዱና አህመድ)

    220
    0