የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

May 10, 20201 min

"ትንሽ ጣፋጭ ብዙ ጉንዳኖችን ትጠራለች" (በእሙ ኢሳን)

ትንሽ ጣፋጭ መሬት ወድቃ

እዛው ከርማ.. እዛው ደርቃ

ከቦታው ላይ ሁና ሰላች

በብዙ ጉንዳኖች ተወራለች

እነ… ጉንዳን ተጠራርተው…

…ተመካክረው…

…ተበራክተው…

በዙሪያው… ተረባርበው

ከዚያው ዙሪያ ሳይወጡ

እዛው... ላይ እንደሰመጡ

እሷኑ… እንደመጠጡ

እስከ ዛሬም አልተለወጡ

በእሙ ኢሳን

ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ

    520
    1