የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

Oct 3, 20201 min

አፈ... ጮሌ! (ከበደ ሚካኤል)

አፈ... ጮሌ! (ከበደ ሚካኤል)

አጥፍቶ አሰዳቢ፤ ዋሽቶ የሚረታ

ሰብሮ የሚያስከፍል፤ ቀብጦ የሚያስመታ፤

ተማቶ የሚያስቅ፤ ተሳድቦ እሚቆጣ

ተበድሮ አስከፋይ፤ ሰርቆ የሚያሳጣ፤

አስቀይሞ አኩራፊ፤ አስለቅሶ አዛኝ

በድሎ የሚካስ፤ ቀምቶ ተለማኝ፤

የሚታዘዝለት ሰው ሁሉ እንደሎሌ

አለ በያለበት፤ አንዳንድ አፈ ጮሌ፡፡

ከበደ ሚካኤል

    200
    0