የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

Aug 19, 20191 min

ፓኒክ ዲስኦርደር- “ፍርሀትን መፍራት” – ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ፓኒክ ዲስኦርደር

ፓኒክ በድንገት የሚመጣ ከፍተኛ ፍርሀት ሲሆን አእምሯዊም አካላዊም ምልክቶች አሉት፡፡ ትንፋሽ ማጠር፣ ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ማላብ፣ መደንዘዝ፣ ማቅለሽለሽ “ልሞት ነው?” “አእምሮዬን ልስት ነው?” የሚሉ ሀሳቦች፡፡ ፓኒክ ግፋ ቢል አስር አስራአምስት ደቂቃ የሚቆይ ይሁን እንጂ ፓኒክ ያጋጠማቸው ሰዎች ያላሰቡት ቦታ ወይም ሁኔታ ውስጥ ድጋሚ እንዳያግጥማቸው መፍራት እና መጨነቅ ይጀምራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከቤት ውጭ

ፓኒክ እንዳያግጥማቸው በመፍራት ከቤት የማይወጡ ሰዎች አሉ፡፡ ለዚህ ነው ፓኒክ ዲስኦርደር “የፍርሀት ፍርሀት” የሚባለው፡፡ ፓኒክ ዲስኦርደር ከመቶ ሰው ከአንድ እስከ አራት ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ሴቶች ላይ የመከሰት እድሉ ከወንዶች ይልቅ ሁለት እጥፍ ነው፡፡

የፓኒክ ዲስኦርደር መንስኤዎች ብዙ ሲሆኑ በባህሪያቸው የሚጨነቁ እና ጭንቀት ጎጂ ነው ብለው በሚያስቡ ሰዎች ላይ ይጨምራል፡፡

በተጨማሪም የህይወት ጫና፣ ከሚወዱት ሰው አለመግባባት ወይም መለየት ሊቀሰቅሱት ይችላሉ፡፡ ፓኒክ ዲስኦርደር ያለባቸው ብዙዎቹ ሰዎች ቡና ሲጠጡ የመጨናነቅ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

የፓኒክ ምልክቶች አካላዊ ስለሆኑ ታካሚዎች ወደ የውስጥ ደዌ ወይም የልብ ስፔሻሊስት ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ በምርመራ ግን የሚገኝ ነገር አይኖርም፡፡ ፓኒክ ዲስኦርደር ውጤታማ በሆነ ሁኔታ በንግግር ህክምና ወይም በመድሀኒት ሊታከም ይችላል፡፡

ምንጭ - http://getutemesgen24.com

    620
    0