top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ልዩ አማካሪ - ሆሳዕና

መስከረም 23/2016 ዓ/ም


ጉዳዩ፡- የምስራቅ ጉራጌ ዞን የአመራር አደረጃጀት ላይ ቅሬታችን ስለማቅረብ

ከላይ በርዕሱ እንደተገለጸዉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን እንሁን ጥያቄ ህዝባችን ያለፉትን 30 ዓመታት ከሚደርስባቸዉ በርካታ የመልካም አስተዳድር ፍትሃዊ የልማት የፖለቲካ እና ሃብት ክፍፍል ችግሮችና እና አገለግሎትን በቅርበት የማግኘት ጥያቄዎች ጋር ተዳብሎ ጥያቄዉን ለመንግስት እያቀረበ እዚህ ደርሶ በብልጽግና መንግስት ምላሽ አግኝተን ህዝቡ ደስታዉን በየደረጃዉ እየገለጸ ይገኛል::

ለጥያቄየቻን ምላሽ ማግኘት ዋንኛዉና መንግስትና ፓርቲ ቢሆንም ከመንግስትና ፓርቲ ጎን ሆነዉ ትግሉን የመሩለት የህዝቡ ልጆችና የከፈሉት መስዋእትነት ማወቅ ደግሞ ወደፊት የሚኖረዉ የፖለቲካ ጉዞዋችን እንዴት መመራት እንዳለበት የሚያሳይ ይሆናል ምክንያቱም የትግሉ አደናቃፊዎችንና ገለልተኛ ሆነው የቆዩትን አካላት የዞኑን አደረጃጀት ባለቤት እንዲሆኑ የተደረገበት አካሄድ ህዝቡን የናቀና የህዝቡን ህልውና የተፈታተነ ተግባር መሆኑ ማንም ሊያውቀው የሚገባ መሆኑ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል ብቻ ሳሆን ቀጣዩን የፖለቲካ ጉዞ በህዝቡ ዘንድ አጠራጣሪ ተዓማኒነት የጎደለዉንና መልሶ የምዕራብ ጉራጌ የሞግዚት አስተዳድርን ለማስቀጠል ያሰበ ይመስላል::

እንደሚታወቀዉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን እንሁን ጥያቄ ዘመናትን ያስቆጠረ ጥያቄ የነበረ ሲሆን ይህ ጥያቄ ግን ነብስ ዘርቶ ህይወት ያገኘዉ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ነዉ፤፤ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በፌድራል መንግስትና በድርጅቱ መሪዎች ዘንድ ተገቢዉን መረጃ ያልነበረዉ ከፍ ሲልም በሰባት ቤት ጉራጌ ከፍተኛ አመራሮች ዘንድ የህዝብ ጥያቄ ሳይሆን ጥቂት ያኮረፉ አመራሮች አጀንዳ ነዉ ተብሎ ሲደፈቅ በመቆየቱ ነዉ:: ይህን ጥያቄዉን የማዳፈን ስራ እንዲጋለጥና ትክክለኛ የህዝብ ጥያቄ እንደነበር አበሬታ ለማድረግ ትልቁን ድርሻ የወሰዱት ግን ጥቂት የቡታጅራ አካባቢ ሙህራን ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ናቸዉ፤፤ እዉቀታቸዉን ጉልበታቸዉን ጊዜያቸዉን ገንዘባቸዉን ጭምር መስዋት በመድረግ በተደጋጋሚ ወደ ፌድራል መንግስቱና ክልል መንግስታት በመመላለስ አቤቱታቸዉን ሲያሰሙ ቆይተዋል::

ተጨማሪም የጉራጌ ክልል አቀንቃኞች በመላ ሃገሪቱና በዉጭ ሃገራት ጉራጌ ክልል ነዉ የሚል ዘመቻ በመክፈታዉ በርካታ የህብረሰተሰባችን ክፍሎች ለዚህ ሃሳብ ተገዥ ሆኖ መንስት ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር መንግስት ያቀረበዉን የጥናት አማራጭ ባለመቀበል በዞን ምክር ቤት ጭምር ዉድቅ በማድረግ ክልሉንና ሃገር ላይ አደጋ ዉስጥ አስገብተዉ በነበረበት ወቅት ይሄንን ዘመቻ ለመቀልበስ በሃገር ዉስጥና በዉጪ ሃገራት ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ዘመቻዎችን በፌስቡክ በቲዉተር በዋትስአፕ በቲክ ቶክ በዩ ቱዩብ እና መሰል ማህበራዊ ሚድያ በመጠቀም የተሰራዉ ስራ ማንም ሊክደዉ የማይገባ ሃቅ ነዉ:: በተጨማሪም ዋንኛ ትግል የነበረዉ መሬት ላይ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ሰነዶችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት የተለያዩ ብሮሸሮችን በማዘጋጃት ህብረተሰቡን የማወያት የማንቃትና የማስረዳት ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል::

በዚህም ትግላቸዉ በአንዳዶቹ ላይ በጽንፈኛ የምዕራብ ጉራጌ ዲያስፖራዎች የግድያ እና የመሳሰሉ ጥቃቶች እንዲደርስባቸዉ ለማድረግ ተሞክሯል፤፤ ብቻም ሳይሆን አሁን በዞንና ከተለያዩ ቦታዎች የተሰባሰቡና አሁን አዲሱን ሹመት የተቆጣጠሩ የምስራቅ ጉራጌ ተወላጆች አንዳንዶቹ ለስልጣናቸዉ ሲሉ ከሌሎች የጉራጌ ክልል አቀንቃኞች ጋር በመሆን በታጋዮች ላይ እስርና ማስፈራሪያዎችን ሲያደርሱ ቆይተዋል በተለይም በአቶ እርስቱ ይርዳዉና በዞኑ አስተዳዳሪ መሃመድ ጀማል የሚታዘዘዉ የቡታጅራ ከንቲባን በመጠቀም ወጣቶችን ሽማግሌዎችን ሙህራንን የማሰር የማሳደድና የማሸማቀቅ ተግባራት ሲደረግባቸዉ ያን ሁሉ ተቋቁመዉ ትግሉን ከመንግስትና ከፓርቲ ጎን በመሆን አስከመጨረሻዉ ታግለዋል::

ታዲያ አጠቃላይ ማህበረሰቡ እነዚህ ታጋዮች ከፊት መሪ ሆነዉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ይለዉጣሉ ብሎ ተስፋ ባደረገበት ማግስት የትግሉ አደናቃፊ እና ገለልተኛ ሆነው የቆዩትን የዞኑን አደረጃጀት ባለቤት እንዲሆኑ የተደረገበት አካሄድ ህዝቡን የናቀና የህዝቡን ህልውና የተፈታተነ ተግባር መሆኑ ማንም ሊያውቀው የሚገባ መሆኑ አጽንኦት በመስጠት አፋጣኝ እርምት መዉሰድ ይገባል።

ስለሆነም የምንጠይቀዉ እርምት መተመለከተ

  1. የዞን አደረጃጀቱ ምደባ እንደገና ተስተካክሎ መሰራት አለበት ምክንያቱም ለህዝቡ ክብር የሰጠ አደረጃጀት መሰራት ስለአለበት፣

  2. ከመንግስትና ፓርቲ ጎን በመሆን የህዝቡ ትግል የደገፉ ልጆቹ ያለምንም ቅድመ - ሁኔታ ወደ አመራርነት እንዲመጡ መደረግ አለበት፣

  3. ከመንግስትና ፓርቲ በተቃራኒ በመሆን የህዝቡን ትግል ሲያደናቅፉና ከትግሉም ገለልተኛ ሆነው የቆዩተወላጆች ያለምንም ቅድመ- ሁኔታ ከአመራር መድረኩ እንዲሰናበቱ መደረግ አለበት፣

  4. በዞን አደረጃጀቱ የተመጣጠነ የህዝብ ውክልና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲከበር መደረግ አለበት፣

  5. የዞኑ የአደረጃጀት መመሪያ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ መሆን ይገባዋል፣

  6. በመጨረሻም መንግስታችንና ፓርቲያችንለድላችን የነበራቸውን ከፍተኛ እገዛ በአጽንኦት እያስታወስን የድላችን ተጠቃሚ እንድንሆን በድጋሚ ሊያግዘን ይገባል እንላለን።

ከሰላምታ ጋር

የቡታጅራ እና መስቃን ወረዳ የሃገር ሽማግሌዎችና ወጣት ተወካዮች

ግልባጭ

· የፌደራል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

· ለኢፌድሪ የፌደሬሽን ም/ቤት አዲስ አበባ

· የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሆሳዕና

· የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ወልቂጤ

· የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብ/ሰቦች ም/ቤት ሳጃ
54 views0 comments

Comments


bottom of page