top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ሐሰን ኢንጃሞ ማን ነው?

Updated: Sep 21, 2020


ሐሰን ኢንጃሞ ማን ነው?

ሐሰን ኢንጃሞ በልጅነቱ በእነሞር በአባቱ በተመሰረተው መስጊድ፣ ከዛም በቀቤና እና አምበልታ (ወለኔ ውስጥ) ከታዋቂው ሼህ አብዱልአዚዝ ዘንድትምህርቱን ተከታትሏል። የአሊ ደነቦን የሚስት ልጅ ያገባው ሐሰን ከአባቱ ሞት በኋላ በአባቱ እግር ተተክቶ የዑመር ቃል-አቀባይ ሆነ። በሐሰንኢንጃሞ የሰላሳ ዓመታት የሥልጣን ቆይታ የቀቤና መንግሥት እጅጉን እንደተጠናከረ ነው ታሪክ የሚያወሳው። በዚህም መሰረት ከምስራቅ እስከምዕራበ ከሰሜን እስከ ደቡብ በሚደረገው የንግድ እንቅስቃሴ ቀቤና አንደኛዋ የንግድ ማዕከል ሆነች። ከዚህም ሌላ አዳዲስ መስጊዶችንና ኢስላማዊትምህርት ቤቶችን በመክፈት ብዙ ታዋቂ የሙስሊም መንፈሳዊ ምሁራንን መሳብ የቻለች መንግሥት ሆነች ቀቤና።

ዑመር ቤኬሳ ለሸዋው ክርስቲያን ንጉሥ ምንሊክ ለመገበር በ1867 ዓ.ም. ተስማማ። በዚህም ስምምነት መሰረት ዑመር ከንጉሡ የደጃዝማችነትማዕረግ ሲያገኝ ሐሰን ኢንጃሞን ግን አስቆጣው። ለሸዋው ክርስቲያን ንጉስ ለመገበር መስማማት ኢስላምን መካድ ነው ሲል ዑመር ለጦርነት ተዘጋጀ።

በዚህም መሰረት ለረዥም ጊዜ በንግድና በእስልምና ካፈራቸው ወዳጆቹ ከወሎ፣ ከወለኔ፣ ከጂማ ፣ ከአርሲ ከሱዳንም ሳይቀር እርዳታ አግኝቷል።በተለይም የቀድሞው መምህሩ ሼህ አብዱለአዚዝ ዘመቻውን በማስተባበር በኩል ትልቅ ስራን መስራታቸው ይነገራል። በ1870 ዓ.ም የአጼ ዮሐንስንየግዴታ ክርስትናን ተቀበሉ ትዕዛዝ እምቢኝ ብለው በሼህ ዚዪን እየተመሩ ቀቤና የደረሱት ሙስሊሞች የሱዳን ማህዲስቶች ማበረታቻ ለሐሰንኢንጃሞ የልብ ልብ ሰጡት። ከዚህ በኋላ ሐሰን ኢንጃሞ ወደ ወለኔ በማቅናት ከሼህ አብዱልአዚዝና ሼህ ዚዪን ጋር መከረ። በምክራቸውም መሰረትጂሀድ ለማወጅ ተስማምተው ወደ ጋርባጃ ኮረብታ ዚያራ አደረጉ።

በዚህም መሰረት ለረዥም ጊዜ በንግድና በእስልምና ካፈራቸው ወዳጆቹ ከወሎ፣ ከወለኔ፣ ከጂማ ፣ ከአርሲ ከሱዳንም ሳይቀር እርዳታ አግኝቷል። በተለይም የቀድሞው መምህሩ ሼህ አብዱለአዚዝ ዘመቻውን በማስተባበር በኩል ትልቅ ስራን መስራታቸው ይነገራል። በ1870 ዓ.ም የአጼ ዮሐንስንየግዴታ ክርስትናን ተቀበሉ ትዕዛዝ እምቢኝ ብለው በሼህ ዚዪን እየተመሩ ቀቤና የደረሱት ሙስሊሞች የሱዳን ማህዲስቶች ማበረታቻ ለሐሰንኢንጃሞ የልብ ልብ ሰጡት። ከዚህ በኋላ ሐሰን ኢንጃሞ ወደ ወለኔ በማቅናት ከሼህ አብዱልአዚዝና ሼህ ዚዪን ጋር መከረ። በምክራቸውም መሰረትጂሀድ ለማወጅ ተስማምተው ወደ ጋርባጃ ኮረብታ ዚያራ አደረጉ።

በ1870 ዓ.ም ሐሰን ኢንጃሞ ዑመር ላይ ጦርነት ከፈተበት። የሐሰንን ጦር መቋቋም ያልቻለው ዑመር ሲሸሽ፣ ንብረቱ የሚዘረፈው ተዘርፎ የተቀረውወደመ። ምንም እንኳን ዑመር ከወለኔ፣ ሙኸር፣ ጉመር እና ቸሀ በመታገዝ ሐሰን ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ቢከፍትም ሳይሳካለት ቀረ። በዚህ ድልምክንያት ሐሰን ኢንጃሞ የቀቤና መንግሥት ቁንጮነቱን ማረጋገጥ ችሎም ነበር። ከዚህ በኋላ የሐሰን ኢንጃሞ እንቅስቃሴ የነበረው በዑመር ቤኬሳዘመን ተበርዟል ያለውን እስልምና ማጽዳትና ለሸዋው ንጉስ በገበሩት ጎረቤት መንግሥታት ላይ ዘመቻ መክፈት ነበር። ሐሰንን ለማግባባትየዲፕሎማሲ ሙከራዎችን አድርጎ ያልተሳካለት የሸዋ መንግሥትም የሐሰን ኢንጃሞን ጦር ለማንበርከክ በቀኛዝማች ውቤ አርጃኖ፣ ደጃዝማች ወልዴአሻጋሪ እና በባሻ ሀብተሥላሴ የተመራ ጦር አዘመተ። ነገር ግን ሐሰን ኢንጃሞ በቀላሉ የሚሰበር ሰው አልነበረም። የሸዋውን ጦር ድል በመንሳት ሰባትቤት ጉራጌን እና አክሊልን ተቆጣጥሮ ዑመር ቤኬሳን በቁጥጥሩ ስር አዋለ። ከዚህ በኋላ ለሐሰን የገባው ዑመር ቤኬሳም የሐሰንን ዘመቻ በመቀላቀልበሰባት ቤት ጉራጌ እስልምና እንዲስፋፋ ሲደረግ ባህላዊ አምልኮዎችና የአምልኮ ስፍራዎች እንዲወድሙ ተደረገ። በዚህ ጊዜ እስልምናን ተቀብዬ የአባቶቼን ባህላዊ የአምልኮ (ዋቅ) ስረዓት አልተውም ብሎ ያመጸው ሳራሞ ጋቼኖ በያበዜ በህዝብ ፊት እንዲገደል ሲደረግ፣ ክርስቲያኖቹ መኸሮችበእቸኔ እና በያሚናን ደም አፋሳሽ ውጊያ አድርገዋል። በመጨረሻው ግን ድሉ የሐሰን ኢንጃሞ ሆነ።

ታላቁ የሀዲያ-ጉራጌ የጂሃድ ዘመቻ ከአርሲ ኦርሞ ኃይል ጋር በመተባበር ለሸዋ መንግሥት ከፍተኛ የራስ ምታት ሆኑበት። ምንም እንኳን በ1878 እና80 በደጃዝማች ወልዴ አሻጋሪ የተመራ ጦር እንደገና ቢዘምትም ድል ሊቀናው ግን አልቻለም። ወሊቆ ላይ በተደረገ ውጊያ ድል በድጋሚ የነሐሰ ንኢንጃሞ ሆነ።

በመጨረሻም ንጉሥ ምንሊክ ታላቁን ጦራቸውን በራስ ጎበና ዳጨ መሪነት አዘመቱ። በወሊሶ አቅራቢያ ጀቢዱ ሜዳ ላይ በሐሰን ኢንጃሞየሚመራውን የተባበረው ሙስላም ጦርን የገጠመው ራስ ጎበናም ድል ሲቀናው ሐሰን ኢንጃሞም ወደ ጂማ ሽሽት ጀመረ። በዚሁ ጉዞ ላይ እያለምጊቤን ሲሻገር በወባ በሽታ ተጠቅቶ ሰባ ሲደርስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የሐሰን ኢንጃሞ አስክሬን ያረፈውም በቤተሰቦቹ የቀብር ስፍራ ላይ ነበር።


ምንጭ - ሰዋ ሰው ድረ ገጽ

63 views0 comments

Comments


bottom of page