top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

መስቃን ማረቆ (አህመድ ኑሪ ሳሊሃ)


መስቃን ማረቆ (አህመድ ኑሪ ሳሊሃ)
መስቃን ማረቆ (አህመድ ኑሪ ሳሊሃ)

ምስራቁን ክፍል ከፋፍሎ ለመያዝ በየቀኑ ማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም!! ስስ ብልታቸውን ይነካልናል ያሉትን ሁሉ ይሞክራሉ!! አንዳንድ ግለሰቦች በዚህ የንፋስ አቅጣጫ በርበሬያችሁን ላለመንፋት መጠንቀቅ አለባችሁ።


የመስቃን እና የማረቆ ህዝብ በመከራም ሆነ በደስታ ወቅት ሊነጣጠሉ የማይችሉ ህዝቦች ናቸው። መከራም እኩል ነው የሚቀምሱት!! ደስታቸውም የጋራ ነው። ቢጣሉም እርቅ እየፈፀሙ ይኖራሉ። ሌላ ምርጫም የላቸውም። መሬት ተንቀሳቃሽ ሀብት አይደለም። እኔ ከእነ እገሌ ጋር መኖር ስለምፈልግ መሬቴን ይዤ እሄዳለሁ አይባል።


ተጋብቶተዋልዶ አብሮ የሚኖር ህዝብ ላይ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በመነጣጠል ለማኖር የሚሹ አካላት አደብ ያዙ ማለት ያሻል። የከፋፍ ለህግዛው ህግ የተጠናወታቸው ዛሬም በሁለቱ ህዝቦች መሀል ገብተው የፖለቲካ ቁማራቸው መጫወት የፈለጉ ይመስላል። የጉራጌ ክልል አስመላሽ ኮሚቴ ነን ባዮች በፌስቡክ ቁማራቸው አጣጡፈዋል። የችግሩ ጠንሳሽና ምንጩ ማን ሆነና ነው?


በየትኛውም ወገን የሚነሱ የትኛውንም ጥያቄ በሰከነ መንገድ በውይይት እና በአሰራር መፍታት እየተቻለ ቁማርተኛ አመራሮች ሲፈልጉ ችግር እንዲፈጠር እያደረጉ ሲፈልጉ የመፍትሔ አካል እየሆኑ ሰነባብተዋል።


ስግብግቦቹ የጉራጌ ክልል ጉዳይ በባሌ መንገድም ይሁን በቦሌ መንገድ ማሳካትን እንጂ የህዝቦች አብሮነት እያሳሰባቸው አይደለም፤ እሳቤያቸው " የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው" ነው።


ጉራጌ ብቻውን ክልል የመሆን ዕድል ቢያገኝ እንኳ ማረቆ ብሔረሰብ በጉራጌ ክልል ስር ይሆናል ብሎ የሚያሰብ ካለ የዋህ ነው ማለት ነው ወይም ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ እንደማታለያ የሚጠቀሙ ሴረኞች ናቸው ማለት ነው። በጉራጌ ክልል ስር ያለመሆን ደግሞ የምስራቁ ጉራጌ ፍላጎት ጭምር ነው።

ባለፈው ፅሁፌ ላይ በጉራጌ ዞን ውስጥ ያሉት ሁለቱ ብሔረሰቦች ማለትም ማረቆና ቀቤና በየትኛው ክልል ውስጥ መካተት እንደ ሚፈልጉ ዕጣ ፋንታቸው የሚወስኑት በራሳቸው ም/ቤት እና ህዝብ መሆኑ ገልጬ ነበር።


ታድያ እንደዚያ ከሆነ መስቃንም ሆንክ ማረቆ ይህንን ጥያቄ ልጠይቅህ

  • ማረቆበሌላ ክልል መስቃኑ በሌላ ክልል ቢሆኑ በሁለት ክልል መሀል ያለ ግጭት በመፍጠር ሁልጊዜ ስለፀጥታ እና ደህንነት ጉዳይ እያሰቡ የልማት ጥያቄዎች እንዳታነሳና ፊትህ ወደ ልማት እንዳታዞር የቤት ስራ እየተሰጠህ እንድትኖር ትፈልጋለህ?

  • በችግርህጉዳይ ላይ በአንድ ክልል ስር ሆነህ ብትፈታ ነው ወይስ በሁለት የተለያዩ ክልሎች ውስጥ ብትሆን ነው በተሻለ መንገድ ልትፈታው የምትችለው?

  • ማረቆውስጥ ያለው መስቃን ሆነ መስቃን ውስጥ ያለው ማረቆ በተለያዩ ክልል ውስጥ እየተዳኙ ዘላቂ ሰላም ይመጣል ብለህ ታስባለህ?

መልሱንለ አንባብያን ትቻለሁ!!


ሌላው በሀድያ ትበደላለህ እያሉ ሊያስፈራሩህ ይሞክራሉ። ያሰቡልህ ይመስል። የሚቋቋመው ክልል የጉራጌም፣ የስልጤም የሃድያም የሃላባም የከንባታም.... የሁሉም ነው። እበደላለሁ ብለህ ካሰብክ ወደራስህ ማየት አለብህ። እውነት ላይ መቆምህን አረጋግጥ። አንድነትህ አጠናክር።

ፍርሀትህን አስወግድ!! ያንተን የሆነ ነገር ማንም አይወስድብህም!! ያንተን ያልሆነ ነገር በግድ የምታቆየው ነገር አይኖርም። በእውነት መዳኘትን ብቻ ነው መሻት ያለብህ!!


የሀድያ ሱልጣኔት ስር ትወድቃለህም ይሉሀል። የሀድያ ሱልጣኔት ምንድን ነው? ስግብግቦቹ ይሄንን የሚነዙት ህዝብን ለማደናገርና በፍርሀት ይደግፉናል ብለው ስለሚያስቡ ነው።

ለማንኛውም የሀድያ ሱልጣኔት ማለት በ13ኛ ክ/ዘመን በኢትዮዽያ ከነበሩት ሰባት ሙስሊም መንግስታት (ሱልጣኔት) አንዱ ነው። የሀድያ ሱልጣኔት ርዝመቱ 160 ኪሜ ስፋቱ 180 ኪሜ ያህል የነበረ ሲሆን አጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 28800 ኪሜ ስኩዌር ነበር። ህዝቦቿ የተለያዩ ጎሳዎች( ብሔሮች) ነበሩ። ሀዲያ የአረብኛ ቃል ሲሆን ስጦታ ማለት ነው።


ሌላው ስለማንነት በማንሳት በደቡብ ሸዋ ክልል ስር ከሆንክ ማንነትህ ይጨፈለቃል ሊሉህም ይሞክራሉ። በደቡብ ሸዋ ስር መሆን ማንነት የሚጨፈለቅ ከሆነ ጉራጌ ብቻ ሳይሆን ስልጤም ሌላውም ይጨፈለቃል ማለት ነው!! ማን ማንን እንደሚጨፈልቅ ግራ ቢያጋባም!! ከዚያስ?

እራስህን ፈትሽ! "ሌባ እናት ልጇን አታምንም" ይባል የለ!


እራስን በሌላው ጫማ ውስጥ ሆኖ አለማየት በሸታ ነው!!

ስልጣንና ጥቅም በበላይነት ይዞ የቆየ አካል አይ አይሆንም ከአሁን በኋላ እኩል መሆን አለብን ስትለው ሞት መስሎ ነው የሚታየው - በህወሓት የጠላነው ነገር።


በጉራጌ ክልል ስር ከሆንክ በምዕራቡ ጉራጌ አመራሮች ይሁንታና በጎ ፍቃድ ብቻ ነው የአካባቢ ሁኔታ የሚወሰነው!! የፖለቲካ ትርፍ ያስገኛል ብለው ካመኑ ያሻቸው እንደሚያደርጉ እስከዛሬ የመጣንበት መንገድ ህያው ምስክር ነው።


መስቃንምሆንክ ማረቆ ቀጠናህን ነቅተህ ጠብቅ!! የሌሎች ጥቅም ማስፈፀሚያ አትሁን!!


አህመድ ኑሪ ሳሊሃ

Comments


bottom of page