የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ሚናህ የጥይት አይነት ብቻ አይሁን

የሰው ልጅ ሆነህ ሚናህ የጥይት አይነት ብቻ አይሁን። አንዳንዴ አስተኳሽ… መሆን ባትችል እንኳን የጠብመንጃን ሚናን ልትጫወት ይገባል።
ጥይት ተተኳሽ ነው። ማገናዘብ አይችልም። ሚናው በሌላው መተኮስ ወይም መወርወር ብቻ ነው። ጠብመንጃው ደግሞ መተኮሻ ነው። ጥይቱ ከውስጡ ቢገባም እንኳን ቃታው ካልተሳበ የያዘውን… እንደያዘ ይከርማል። ይቆያል። አስተኳሹ ግንጠንሳሹ ነው። አስተኳሽም ነው። አንዳንዴ ተኳሽም ነው። እናልህ… ወንድሜ! እባክህን… ሚናህ በፈለጉት ጊዜ ወደ ፈለጉት ቦታ እና አቅጣጫ የሚወረውሩት ወይም የሚተኩሱት ጥይት አትሁን። ያ… ጥይት አንዴ ከተተኮሰ በዃላ ከኢላማው ደረሰም - አለደረሰ ሚናው ያበቃለታል። ተመልሶ ጥይት ሊሆን አይቻለውም። ጠብመንጃው ግን ቢሰበር እንኳን ይጠገናል።በተጨማሪም እንዳይበላሽ እና እንዳይዝግ ዘይቱን ቀብተው፣ ጠራርገውና ሸፋፍነው ያስቀምጡታል። እስካሁን የተባለው ሁሉ ግልጽ ካልሆነልህ እኔና እኔ ልናግዝህ ዝግጁ እና ፍቃደኞ ነን።