top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ምኞት" - በነጻነት አምሳሉ


"ምኞት" - በነጻነት አምሳሉ

“ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ” - እያልኩ ስማጸነው

የስንቱ ቆሻሻ

እኔ ላይ ተደፍቶ - ጠዋት አየዋለሁ

ልቤን ላጥራብዬ - ስደክም ስለፋ

ደፋር እጣቢውን

የስሜም ንጣፍ ላይ - እያየሁት ደፋ!


አንዳችን ላንጠራ - እንዲህ እየተግማማን

እንዶድ አይችለንም - ፈትጎ ሊያጠራን !

ነውራችን ሲገለጥ - በዘመን ቆዳ ላይ

ጭቅቅት ሆነናል - ደግ ዘመን ላናይ !


የግብራችን ክፋት - ላይጠፋ በእጣኑ

ተረግሞ ከሰመ - የእግዜር ደግ ቀኑ !

ልቻለው እያልኩኝ - ያለፍኩት በመላ

ፊቴላ ይተጥፎ

ጠባሳ ሆነብኝ - በስተርጅናዬ ገላ !

አቃቂርአውጥቶ - ስም ሳያወጣ ከቶ

ሽብሽብ ቆዳዬ ላይ .......

ብልዝ ዓይኖ ቼላይ .......

ሽበት ጸጉሮቼ ላይ .........

ፊቴን ያነበበ - ደርሶ ያዝንልኛል - መጠቃቴን አይቶ!


ቅንነት ላይበቅል - በልባችን እርሻ

ረግጦ ማለፍ ሲሆን - የፍርዳችን ድርሻ

እኔ እንደ ምን ብዬ - ንጹህ ልብ አንጥፌ

መኖር እችላለሁ - ጠላቴን አቅፌ ?

እንክርዳድ ሲወረው - ሀገር ምድሩ ሁሉ

ወይ አብሮ መቃጠል .......

አልያም መረገጥ ነው - የስንዴ እድሉ!


እናማ አምላኬ - ድካሜን እይልኝ

ክፉ በመሆኔ - ከቶ አትፍረድብኝ!

ጥላቻን ጠልቼ - መኖር እያማረኝ

በሰው ክፉ ተንኮል - መራመድ አቃተኝ!


እጄን ባልዘረጋም - ለበቀል ጨክኜ

ብድር ባልመልስም - ስውር ስፍራ ሆኜ

እስቲ ለወዳጄም - ምህረት ስጠውና

ከማያልቀው ጸጋህ - ጥቂት ይቅመስና

ይቅርባይ - ደግሰው - ትሁት የዋህቀና

እንዲሆን አድርገው - ልቡን እጠብና

አንተን በማወቁ ........

አትራፊ ነው እንጂ .......

“ከሰርኩኝ” እያለ - ደጁን የሚዘጋ - ከቶ የለምና!

እኔም በስተርጅና - ይህን ቀን ልይበት በከዘራ ዘመን - ቀና ልበልበት በሽብሽብ ቆዳዬ - ወዝቼ ልውጣበት ሁለት ጸጉር ይዤ ....... መቃብር ላይ ቆሜ ....... በሞቴ ላይ ስቄ - ነገ ልሙበት! (ነፃነት አምሳሉ)


34 views0 comments

Comments


bottom of page