የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ሰላም...ሰላም

· የዓለም ሰላም ከውስጥ ሰላም ይጀምራል:: (ዳላይ ላማ)
· ውስጣዊ ሰላም ከሌለ፣ ውጭያዊ ሰላም አይኖርም፡፡ (ጌሺ ኬልሳንግ ጂታሶ)
· የስኬት መለኪያ፤ ደስታና የአዕምሮ ሰላም ነው፡፡ (ቡቢ ዳቭሮ)
· ሰላም የሚመነጨው ከውስጥ ነው፡፡ ከውጭ አትፈልገው፡፡
· ሰላም በሃይል ሊጠበቅ አይችልም፤ እውን ሊሆን የሚችለው በመግባባት ብቻ ነው:: (አልበርት አንስታይን)
· በዚህ ዓለም ላይ ከአዕምሮ ሰላም የሚልቅ ሀብት የለም፡፡
· የአዕምሮ ሰላም ያለው ሰው፤ ራሱንም ሌሎችንም አይረብሽም፡፡ (ኢፒኩረስ)
· ሰላም ከፈገግታ ይጀምራል፡፡ (ማዘር ቴሬዛ)
· የመምረጥ ነፃነት ያለው ሕዝብ፣ ሁሌም የሚመርጠው ሰላምን ነው፡፡ (ሮናልድ ሬጋን)
· ከራስህ ጋር ሰላም ስትፈጥር፣ ከዓለም ጋር ሰላም ትፈጥራለህ፡፡ (ማሃ ግሆሳናንዳ)
· ሰላምን ከነፃነት ልትለየው አትችልም፤ ማንም ቢሆን ነፃነቱን እስካላገኘ ድረስ ሰላሙን አያገኝም፡፡ (ማልኮልም ኤክስ)
· ወደ ሰላም የሚያደርስ መንገድ የለም፤ ራሱ ሰላም ነው መንገዱ፡፡ (ኤ.ጄ. ሙስቴ)
· ሰላም የጦርነት አለመኖር አይደለም፤ የፍትህ መስፈን ነው፡፡ (ሐሪሰን ፎርድ)
ምንጭ - ኢንተርኔት