የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
"ሶስተኛው ምርጫ እና አስራ አንድ አመታትን የፈጀዉ የቡታጅራ ካምፓስ ጥያቄ"

የቡታጅራካምፓስ ጉዳይ
ምርጫ ሲመጣ ከሚነሱና ከምርጫ በዃላ ከሚጣሉ አጀንዳዎች አንዱ የቡታጅራ ካፓስ ጉዳይ ነዉ። በምርጫ 97 ጉራጌ ሴረኛዉን መንግስትን ካስተማረ በዃላ በ2002 ዓ/ም ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር የጉራጌ ማህበረሰብን ወልቂጤ ላይ መጥተዉ ካወያዩ በዋላ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲን መሰረት ድንጋይ አስቀምጠዉ የዝዋይ ቡታጅራ ጉብሬ አስፓልት መንገድ ቃል ገብተዉ ሄደዋል።
በዚህ ዉይይት ላይ ከተነሱ በርካታ ሀሳቦች አንዱ የቡታጅራ ጀግናዋ ወ/ሮ ዘይቱና አህመድ ወደ ስብሰባዉ እንዳትገባ በሴረኛ አመራሮች መንገዶች ሁሉ ቢዘጋባትም ሁሉንም ሰባብራ በመግባት በስብሰባዉ ታድማለች ብቻም ሳይሆን እድል በመውሰድ የወልቂጤ ዩንቭርሲቲ ሲፈቀድ የእህት ከተማ ቡታጅራም ካምፓስ እንዲከፈትልን ስትል ጥያቄዋን አንስታ ጠሚዉ መለስ ዜናዊ ፖዘቲቭ ምላሽ ሰጧት እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡታጅራ ከተማን ሲገልጹ በራሷ ግዜ የምታድግ የውስጥ ፖቴንሺያል ያላት ከተማ ናት በማለት ገራሚ ሃሳብ ለተሰብሳቢ አካፍለዋል። የነበራችሁ ታስታዉሳላችሁ ፡፡ በዚህም ዓመት ይህንን ተስፋ ተይዞ ምርጫ 2002 ተደረገ 99 ፐርሰንት ደኢህዴን አሸነፈ።
ከዛ በመቀጠል ይህ የካምፓስ ጥያቄ በተደጋጋሚ በማህበረሰቡም በአመራሩም ሲነሳ ቆይቶ 2004 ላይ ወልቂጤ ላይ በነበረዉ የጉራጌ ዞን አጠቃላይ የአመራር መድረክ መድረኩን ለሚመሩትና በወቅቱ የዩንቭረስቲዉ የቦርድ ሰብሳቢ ለነበሩት መኩሪያ ሃይሌ ጥያቄዉ ተነስቶላቸዉ ሲመልሱ አሁን ዩንቭርሲቲዉ በደንብ አልተደራጀም ሌላ ካምፓስ መክፈት አይቻልም አሉ፡፡
በድጋሚ 2007 ምርጫ ከመድረሱ በፊት የዝዋይ ቡታጅራ ጉብሬ መንገድ ምረቃ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመስቃን ወረዳ አዳራሽ ላይ ከሰተበሰቡት የጉራጌ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ሲወያዩ በአቶ ፍቃዱ አሴሮ እና በአቶ ፓዉሎስ ባለቤት/ስማቸዉን ስላላስታወስኩት ነዉ/ አማካኝነት የቡታጅራ ካምፓስ የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የቡታጅራ ሆስፒታል እድገት በተመለከተ ጥያቄዉ ተነስቶላቸዉ ምላሽ ሲሰጡ ቡታጅራን ለረጅም ግዜ እንደሚያዉቋትና ካምፓስ ሳይሆን እራሱን የቻለ ዩንቭሲቲ የሚገባት ከተማ ናት ካምፓስማ በጣም ቀላል ጥያቄ ነዉ አጠገቤ ያለዉ ደሴ ዳልኬ /የቀድሞው ደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ማለት ነው/ እና ከፊት ወንበር ተቀምጦ የነበረዉን የዩንቭርሲቲዉን ቦርድ ሰብሳቢ መኩሪያ ሃይሌን እየጠቆሙ የነሱ ዉሳኔ ብቻ ይበቃዋል ከጥቂት ቀን በዋላ ምላሽ ይሰጣሉ አሉ በመቀጠልም ይህንን ዉሳኔ ለማስፈጸም በወቅቱ የዞኑ አስተዳዳሪና የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኤሊያሽ ሽኩር አማካኝነት ሸብ ረብ ተባለና ቦታ መረጣ ይደረግ ተብሎ ቦታ ተመረጠ መሰረተ ድንጋይም ይጣላል ተብሎ ሲጠበቅ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ካምፓሱ እንዳይከፈት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኗል አይቻልም ብለዉ አረፉ። ይሁን እንጂ እሳቸዉ እንደዛ ባሉ በጥቂት ወራት ዉስጥ የሃዋሳ ዩንቭርሲቲ አራተኛ ካምፓስ ትንሿ ዳዬ ከተማ ላይ ደሴ ዳልኬና ሽፈራዉ ሽጉጤ የመሰረተ ድገንጋይ አስቀመጡ ጅማ ዩንቭርሲቲ አጋሮ ካምፓስ ባህርዳር ዩንቭርሲቲ ፍኖተሰላም ካምፓስ ወላይታ ሶዶ ዩንቭርሲቲ 2 ካምፓስ ቦዲቲና ተርጫ ካምፓስ ከፍቷል በእድሜ ትንሹ በ2005 የተመሰረተዉ ዋቸሞ ዩንቭርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ሲከፍት በአጠቃላይ በመኩሪያ ሃይሌ ታግዷል ከተባለ በኋላ በሃገሪቱ ዉስጥ እኔ እንኳን ማዉቃቸዉ ከ25 በላይ ካምፓሶች ተገንበተዉ ተማሪዎችን በመቀበል በማስመረቅ ደረጃ ላይ ደርሰዉ ስታይ ሌላ ጊዜ የማብራራዉ ሴራ አንዱ ጎኑ ይታይሃል መቼም ቡታጅራ ከተማ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለ ከተማ ይመስለኛል ባለፈዉ ደግሞ የእድሜ ትንሹ ወራቤ ዩንቭርሲቲ ጦራ ካምፓስ ሲከፍት ስታይ ይሄ ቀጠና በተደጋጋሚ ደህዴንን 99 ፕርሰንት በመምረጡ እንደ ሞኝ ልጅ መቆጠሩ ይገባሃል ግን አንዳንድ ኋላ ቀርና ባህላዊ አመራሮች ብልጽግና ካልመረጥን እንመታለን ይላሉ በ30 አመት ዉስጥ የሆነ ነገር ያገኘን ይመስል እንደኔ ከዚህ በላይ መቀጥቀጥ አለ እንዴ ለዛዉም ወዶ ገባ ቅጥቀጣ አበቃሁ… ምናልባት ዩንቭርሲቲና ካምፓስ መከፈት ምን ያህል ከተማንና የአካባቢዉን ማህበረሰብ በኢኮኖሚ እንደሚጠቅም በመረጃ ዘርዝሬ አቀርብልሃለዉ በተረፈ የትላንትናዉን የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ያለዉንና 900 ሚሊየን ብር አዉጥተን የሚሉ ቅንጥብጣቢና የከሰረ ወሬ አትስሙት!!
በመጨረሻም የጹህፌ መረጃ ነክ ትችት ፖለቲከኛዉን የጉራጌ ካድሬ ካልሆነ በስተቀር አርሶ አደሩን ነጋዴዉን የከተማ ነዋሪዉን ጨዋዉን የጉራጌ ህዝብ ቤቱ ድረስ ገብቼ ስላየሁት በየትኛዉም አቅጣጫ ብትሄዱ እዉነተኛ ጉራጌ ያለዉ እዛ ነዉ በተረፈ አብዛኛዉ ፖለቲከኛ እኔን ጨምሮ ጥቂት የሙህሩ ክፍል ና ባለሃብቶች ግን ከአሰተሳሰባቸዉ ጀምሮ በተግባርም ከፋፋይ አና የጉራጌ አንድነትን የማያይፈልጉ ናቸዉ ብዬ እተቻለሁ፡፡
ታዬ ተስፋዬ ስሜ