top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“ሺ... ቢታለብ ያዉ በገሌ ነዉ አለች ድመት” (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)


“ሺ... ቢታለብ ያዉ በገሌ ነዉ አለች ድመት” (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)
“ሺ... ቢታለብ ያዉ በገሌ ነዉ አለች ድመት” (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

አንዳንድ የጉራጌ አክቲቪስቶች የጉራጌ ፖለቲካን እንደመርካቶ ምናለሽ ገበያ በምዕላና በእርግማን ለመሸጥ ሰባራ ሰንካላዉም ስታወሩ ትዉላላቹ በመሰረቱ አንዳዶቻቹ መረጃና ማስረጃ የሌላቹ ደረቅ ፍልስፍና ለመጋት የምትሞክሩ ጉራጌነትን እንደብትን ጨርቅ ለክታችሁ ቆርጣቹ ለእያንዳዱ ለማልበስ የምትዳዱ ደፋሮች ናችሁ::

የጉራጌ ፖለቲካ የጠነዛዉና የቆረፈደዉ የዛሬ 15 ቀን ወይም የዛሬ አመት ወይም እነእንትና ከስልጣን ስለተነሱ ሳይሆን ከሃያ አምስት አመት በፊት በነበሩ አሁንም በስልጣኑ ያሉ ወይም አዲሳባና የተለያ ቦታዎች ቁጭ ያሉ ስግብግብና የማጠግቡ ከራሳቸዉ ዉጪ ማዳመጥ የማይፈልጉ አሮጋንት የሰባት ቤት ካድሬዎች ምክንያት ነዉ::

የጉራጌ ካድሬ የስልጤን ህዝብ በፍትሃዊነት በእኩልነት አቅፎ ቢይዝ ስልጤ ጉራጌ እንካ ባይሆን ጉራጌ ነኝ ብሎ አንድነቱን አጠናክሮ ይቀጥል ነበር:: በክልሉም ይሁን በሃገር ደረጃ በተለየ ሁኔታ ጉራጌ ዞን ዉስጥ የጭቅጭቅ የንትርክ የግብግብ ፖለቲካ ከቀቤናዉ፤ ከወለኔዉ፤ ከማረቆዉ፤ ከመስቃኑ፤ ከሶዶዉ ወይም ከእንደጋኙ ሚነሳዉ የተለየ በሽታ በነዚህ ማህበረሰቦች ስላለ ሳይሆን የጉራጌ ፖለቲካ እየተነዳ ያለዉ አንተ አክቲቪስቱ የእኔ የምትላቸዉ የአፓርታይድ ስርዓት የሚያራምዱ ጥራዝ ነጠቅ ስግብግና እራሳቸዉን እንደ ፈላጭ ቆራጭ አንደኛ ደረጃ የጉራጌ ማህበረሰብ የሚያዩ ኮንስፓይሬሲ የማይለቃቸዉ የሰባት ቤት ካድሬዎች በመመራቱ እንደሆነ ጠንቅቀህ ልታዉቅ ይገባል ወይም ደግሞ እንደሆነ ታዉቃለህ::


ለዛምነዉ ለጉራጌ ዞን ለብቻዉ ክልል ብትሰጠዉ አስካሁን ባለዉ የድፍጠጣና የሞኖፖሊ እሳቤ ይዞ ሰለሚመራ የነበረዉ ቁስል መርቅዞ ሞትን መፈናቀልን እርስ በርስ መጠላለፍን በመዉለድ ክልል ከመሆን ከሚገኘዉ የኢኮኖሚ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ትሩፋት በላይ ጉዳት ሚያደርሰዉ::


ሌላዉ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር አንዳንዱ አክቲቪስት በሉት የሆነ ነገር ይሄ እኮ በቀላሉ የሚፈታ ነዉ የ1 ወር ስራ ነዉ ለዚች ተብሎ እንዴት ጉራጌን እንጎዳለን ብሎ ይሳለቃል::

ግን ደግሞ ከላይ የጠቀስኩት መርዘኛ ሰባት ቤት ተኮር እሳቤ ከካድሬዉ ባሻገር በሙህሩ በነጋዴዉ በአርቲስቱና በአንዳንድ የከተማ ነዋሪ አስተሳሰብ ዉስጥ ያለ በመሆኑና ይሄን አስተሰብ በማስወገድ ወይም በመቀነስ የእኩልነት የፍትሃዊነትና የአንድነት አስተሳሰቦችን ለማምጣ ግዜያትን የሚወስድ እንደሆነ ጠፍቶህ ወይም ሳያዉቅ ቀርቶ አይደለም:: እንዴት ካልክ ከዚህ ቀደም በመረጃ በማስረጃ አስደግፌ ከጻፍኳቸዉ ሰባት ቅጾች ማየት ትችላለህ::


ማንነትና የብሄር አደረጃጀት በድህነት ዉስጥ እና እየተጨቆነ ላለ ማህበረሰብ ከሞላ ጎደል ጥቅም ማስጠበቂያ አደረጃጀት እንጂ የህይወት ህልዉና ማቆያ የሃማኖት ወይም እምነት መርህ ነዉ አብዬ ልወስደዉም:: በመሆኑም ጉራጌነቴ ልማትን እኩልነትን ፍትሃዊነት ካላጎነጸፈኝ ጥንቅር ብሎ ቀርቶ የእኔም ሆነ ማህበረሰቤ አለማዊና ምድራዊ ፍላጎት የትኛውም ብሄር ሳልሆን ሰዉ ብቻ ሆኜ ፍላጎቴን ባሟላ እመርጣለሁ::Comments


bottom of page