የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ሽንፍላ ! ለ- ባንዳ !!

እነሱው በልተውኝ
ልጠው እንደ - አገዳ
በእሳት እየነደድኩ
ተጥዬ ከሜዳ !
ሰው መሆኔን ክድው
እንዳሻቸው አርገው !!
የቀብሬን ቦታ መኖሪያ ገንብተው !!
ምክር እና ሙጃ
ሲቀልቡኝ ኑሬ :
መንቀሳቀስ ሳልችል
ተከብቤ በአውሬ !!
መሬት ዓልባ ሁኜ ተሰርቃ ሀገሬ !
ተክለህ ብላ ይሉኛል !!
ሰማዩን አርሼ ጉሙን ቆፋፍሬ !!
ሙዝ በዳቦ ሥንግ
ጎመን ፍራፍሬ ::
ኧረረረረ !!!!!
እነዚህብልጥጎች በሃብት የናጠጡ
ታላቅ እና ታናሽ ! ሻኛ ! እየዋጡ
ጎድን ተዳቢቱ ለአገልጋዮች ሰጥተው
ሽንጥና ፍርንባ ! ላሞጋሽ አቅርበው
ምላስእና ስምበር
ላዝማሪው አጉርሰው !!
ሽንፍላ ለባንዳ
ኮቴም ላጨብጫቢ !!
ትራፊ !! ላሽቃባጭ
ሰጥተው ቅንጥብጣቢ
ጥፍራቸውንሰጡኝ
ፆሜን ሊያረክሱ !!
በጭካኔ የፋፉ !! በግፍ የነገሡ ::
የብልጥግ ክምችት
አዳራሹን ሞልቶት
ከአንዱ - ጥግ - አንዱ ጥግ !!
ይብላን ለ- ቅልውጦች !!
እንኳን ትርፍራፊ !
አይኖርም ጥርግርግ ::
( ጃዊሳው ) ዓሊ APRIL 1 / 2022