የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ቀዳሚዉን ስታመሰግን ቀጣዩ ይበረታል! - የተለየ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አመራሮች ክብር እንስጥ!

ቅጽ 4
አቶ ታዬ ተስፋዬ ማነዉ? የትምህርት ዝግጅቱና የስራና የአመራርነት ልምዱን እናካፍላችሁ
ታዬ ተስፋዬ አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ቡታጅራ አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ቡታጅራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቆ ከፍተኛ ዉጤት በማምጣት ወደ መቀሌ ዩንቭርሲቲ በመግባት የመጀመሪያ ዲግሪዉን በመሬት ሃብቶች አስተዳድር እንዲሁም ተጨማሪ ድግሪም በንግድ ስራ አመራር አግኝቷል:: ሁለተኛ ዲግሪዉን ከሃዋሳ ዩንቭርስቲ በንግድ ስራ አመራር በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቋል:: በስራዉ አለም በመስቃን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከወረዳ ኤክስፐርትነት ጀምሮ የግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊነት፤ የወረዳዉ ፋናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊነት ፤ የወረዳዉ ድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊነት፤ እንዲሁም የመስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ያገለገለ ሲሆን በሱ ያመራርነት ዘመንም ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን በህዝቡ ዘንድ እስከዛሬ የሚታወስና በተለይም መስቃን ወረዳን በግብርና ልማት ስራዎች፤ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን፤ በርካታ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶችን፤ በመስራት በሃገር አቀፍ በክልልና በዞን ደረጃ እዉቅና አንዲሰጠዉ አድርጓል:: በወረዳዉ የራሱ የስብሰባ አዳራሽ እንዲገነባ አድርጓል:: የመንገድ ግንባታና ሌሎች ማሽነሪዎችን ገዝቶ በማቅረብ ማህበረሰቡን በመንገድ ልማት አነቃቅቶዋል:: በወረዳዉ በተደጋጋሚ በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸዉን ቀበሌዎችን መንግስትን በማስጨነቅ ተገቢዉን ድጋፍና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ አበክሮ ሰርቷል:: መስቃን ወረዳ ዉስጥ የሚገኙ ህብረተሰቦችን በእኩልነትና በፍትሃዊነት በማስተዳደርና ችግሮቻቸዉንን በመፍታት በህዝቡ ዘንድ ተገቢዉን ክብርና ቦታ ያገኘ አመራር ነዉ::
ወደ ጉራጌ ዞን ከገባም በኋላ የዞኑ ፕብሊክ ሰርቪስ መምሪያ ሃላፊ፤ የዞኑ ከተማ ልማትና ቤቶች መምሪያ ሃላፊ፤ በመጨሻም ለፉት ሁለት አመታት ደግሞ የዞኑ የግብርና መምሪያ ሃላፊ በነበረበት ወቅት ክልሉ ከዞኑ በጀት ላይ ያለአግባብ የቀነሰዉን 198ሺ ሄ/ር መሬት ወይም 300 ሚሊየን ሚጠጋ ብር እንዲመለስ አድርጓል:: ከአርሶ አደር የተመለሱ የማዳበሪያ ገንዘቦች በክልሉ አመራሮች በህገ ወጥ መንገድ እንዳይቆረጡ በማጋለጥ ታግሏል:: ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ተገቢዉን ሰብኣዊ እርዳታ እንዲያገኙ ጥረት አድርጓል:: ወደመባቸዉ ሃብትና ንብረትም እንደሌሎች ህዝቦች በፍትሃዊነት እንዲተካለቸዉ በዋንኛነት በዞኑ ዉስጥ ለዘመናት የቆዩ ይህንን ቀጠና የሚበድሉ አሰራሮችን ፊት ለፊት በመጋፈጡ እንዲሁም ሁሉም የዞኑ ህዝቦች በእኩልነትና በፍትሃዊነት እንዲሳተፉና እንዲጠቀሙ ማንንም ሳይፈራ ታግሏል፡፡ ትግሉንና ማጋለጡን የፈሩት ጥቂት የክልልና የዞን ባለስልጣናት ከአመራርነት ያለግምገማ እንዲወጣ አድርገዉታል። ይህንን የተረዳዉ ህዝብ ብልጽግናን ወክሎ እንዲቀርብ ሲጠይቅ ጥቂት በወረዳና በዞን ደረጃ ያሉ አምባገነን ባለስልጣናት በፍጹም አይመጣብንም በማለታቸዉ ህዝቡን ከነዚህ ከሴረኛ ፖለቲከኞች ለመታደግ በዉስጡ የያዛቸዉንና ሲታገልባቸዉ የነበሩትን አጀንዳዎች በመያዝ የፍትሃዊነትና የእኩልነት ጥያቄዎች ድምጽ ለማሰማት በህዝቡ ጥያቁ መሰረት ብልጽግና ወክሎ እንዲቀርብ ቢጠየቅም ጥቂት ትምክተኛ የጉራጌ ካድሬዎች እሱ አይምጣብን በማለታቸዉና በር በመዝጋታቸዉ ህገ መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም በግል ለመወዳደር መጥቷልና አሻም በሉት ።
ባለፉት ጊዜያት ምን ሰራ በጥቂቱ
በታዬ ተስፋዬ የመስቃን ወረዳ የአመራርነት ዘመን የተሰሩ ልማት ስራዎች በከፊል እናስተዋዉቆ ለማነጻጸርና ለመመዘን ይረዳዎታልና የሚያወራ ሳይሆን የሚሰራ ማን እንደሆነ ለሰልጣኑ ያደረና ለህዝብ የሚኖር ማን እንደሆነ ለወደፊቱም እዉነተና ሞጋች ወካያችን ማን እንደሆነ አዉቀዉ ይመርጣሉ::
መንገድ ልማት ስራዎች እንመልከት ህብረተሰቡን ባለሃብቱንና የመንግስት አቅም በመጠቀምና በማቀናጀት የአርሶ አደራችንን ችግር ከነ ጉድለቱም ቢሆን በመቅረፍ ክረምት ከበጋ የሚያገናኙ መንገዶችን ከ2004-2009 ባሉት የአመራርነት ጊዜችን ሰርተን ያሳየን ሲሆን አሁን ያሉት ምን እንደሰሩ እየጠየቃችሁ የተወካያችን ጥረቶቹ እነሆ፦
ከእንሴኖ ዲዳ ወጃ 7 ኪሜ
ከአካሙጃ ዊጣ ይመርዋጮ 123 ሃሙስ ገበያ 9.4 ኪ/ሜ
ቡታጅራ ወሌንሾ ሶስት አምባ ዘቢዳር 9 ኪሜ
ቡታጅራ መቅች ጎይባን ሸበሬር 8.8 ኪ/ሜ
ቡታጅራ በሬሳ ዶበና እንሴኖ 14 ኪ/ሜ
አጎዴ ሚካኢሎ 4.6 ኪ/ሜ
ቡታጅራ መቅች ዶቢ ጎጋ ከፍተኛ ጥገና
ሜርሲ ማዞሪያ የተቦን
ቡታጅራ 130 ወሌንሹ 1 መሰረተ ወገራም 12 ኪሜ
ሃሙስገበያ ማዞሪያ አስከ መቂ ወንዝ ከነ ከፍተኛ ድልድይ 8 ኪ/ሜ
የቆቶ ዉሪብ ኦዶ ተጀምሮ 2012 የተጠናቀቀ
ጆሌ ማዚሪያ አስከ ጆሌ2/3 ጀንራል ድልድይ 7 ኪ/ሜ
ቡታጅራ ቡድቄሳ የተቦን
ሞሬ ግዴና አቦራት ሎያ በወረዳና ህብረተሰቡ ተሳትፎ
ገተማ ዶቦጡጦ በተሳትፎ
ገተማ ምስራቅ መስቃን በተሳትፎ
እንዲሁም ለወረዳዉ ግሬደር በመግዛት ከላይ ያሉትን ጨምሮ በየቀበሌዉ ህዝቡ ናፍጣ ብቻ በመግዛት የዲዳ ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ የወጃ የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ሸርሸራ ቢዶ ዉስጥ ለዉስጥ ሌጃኖ ዉስጥ ለዉስጥ ዶበና ጎላ ዶበና ኢሌ መንገዶች ተሰርተዋል
የእንሴኖ ከተማ ዉስጥ ለዉስጥ መንገዶች በመከፈት በየአመቱ ቀይ አሸዋ በማፍሰስ ከጥልቅ ጭቃ ማዳን ተችሎዋል የሚያሳዝነዉ ግን በዚህ ሶስት አመት ይሄ ሁሉ የተሰሩ መንገዶች የሚያስጠግናቸዉ በማጣታቸዉ ሁሉም እየፈረሱ ይገኛሉ
በትምህርት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች
እኔና ጓደኞቼ በጥቂት አመታት ውስጥ ህዝብና የወረዳውን መንግስት አቅም ብቻ ተጠቅመን ከዞኑ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የነበረውንና 1 ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት ብቻ የነበረውን መስቃን ወረዳ በ5 አመት ብቻ 10 ሁለተኛ ደረጃ አድርሰናል አንደኛ ደረጃም ከ36 ወደ 71 አሳድገናል።
የእንሴኖን አንደኛ ደረጃን ት/ት ቤትን ወደ ፕርፓራቶሪ አሳድገናል
የሃሙስ ገበያን 1ኛ ደረጃን ህዝብ አስተባብረን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት አሳድገናል
የዶቢን 1ኛ ደረጃን ባለሃብት በማስተባበር ወደ ሁለተኛ ደረጃ አሳድገናል
አዲስና ሙሉ ሃይስኩል አካሙጃ ናዊጣ ሃይስኩል እንዲኖር አድርገናል
የደቡብ ሸርሸራ አንደኛ ደረጃን ህዝብ አስተባብረን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት አሳድገናል
የቆቶን 1 ደረጃን ት/ትቤትን ፦ከፕሮጀክት ሜርሲ ጋር በመሆን ሙሉ አዲስ ትት ቤት አስገንብተን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትት ቤት አሳድገናል
የመሰረተ ወገራም አንደኛ ደረጃን የአካባበውን ባለሃብት በማወያየት አዲስ ሙሉ ግንባታ በማድረግ ወደ 2ኛ ደረጃ ትት ቤት አሳድገናል
የዶበና 1ኛ ደረጃን ወደ 2ኛ ደረጃ ትት ቤት አሳድገናል
የውሪብ ወዶን 1ኛ ደረጃን ወደ 2ኛ ደረጃ እንዲያድግ አደርገናል
የወጃ 1ኛ ደረጃን ወደ ሁለተኛ ደረጃን የማሳደግ ስራ ተሰርቷል፡፤
ቅጽ 5 ይቀጥላል ተከታትለዉ ያንብቡት እባክዎ ሌሎች እንዲያነቡት የቻሉትን ያህል share ያድርጉ