• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

በመላው አለም ለምትገኙ ለመስቃን ቤተ ጉራጌ ተወላጆች በሙሉ


አምባሳደር ድንበሩ አለሙ የመስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር
በመላው አለም ለምትገኙ ለመስቃን ቤተ ጉራጌ ተወላጆች በሙሉ

የተከበራችሁ የመስቃን ቤተ ጉራጌ ተወላጆች በያላችሁበት ሰላም ለናንተ ይሁን!

እንደሚታወቀው የመስቃን ቤተጉራጌ የራሱ የሆነ ታሪክ ፣ባህል ዘዬ እና የሚኖርበት መልክአ ምድር ያለው ሲሆን በአካባቢው ከሚኖሩ ሌሎች ቤተ ጉራጌዎች እና ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በሰላምና በፍቅር የሚኖር፣ አቃፊ ማህበረሰብ እና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ህዝብ ነው።

የመስቃን ማህበረሰብ ከአብራኩ ብዙ ሙሁራኖች፣ባለሀብቶች፣ታዋቂና ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች እንዲሁም አንቱ የተባሉ የአገር ሽማግሌዎች ያፈራ ጠንካራ ማህበረሰብ ነው። ይሁን እንጂ መህረሰቡ እስከዛሬ በአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማህበራው እንቅስቃሴዎች ጥሩ የሚባል አስተዋፅኦ ያደረገ ቢሆንም እንደሌሎች ማህረሰቦች ተቋም ገንብቶ የመንቀሳቀስ ባህል ስላልፈጠረ በማህረሰቡ ሁለንተናዊ እድገት ዙርያ ማበርከት የሚገባውን አስተዋፅኦ ሁሉ ለማድረግ እንዳልቻለ ሁላችንም የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።

ከዚህ አኳያ ችግሩን ለመቅረፍ የመስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት የካቲት 2011 ዓ.ም ተቋቋቁሞ ሰኔ14 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት በማግኘት ይፋ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በአዲስ አበባ ዋና ፅ/ቤት ፣በቡታጅራ እና በሪያድ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ -ዋሽንግተን ዲሲ፣ በአውሮፖ ለንደን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ቻፕተሮችን እያቋቋመ ይገኛል።

በመሆኑም በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምትኖሩ የማህበረሰቡ ተወላጆች ለበጎ አድራጎት ድርጅቱ አላማና ተልእኮ መሳካት በአባልነት እንድትመዘገቡና የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ ጥሪያችንን እያቀረብን ለምትሰጡት አዎንታዊ ምላሽ በቅድሚያ ለማመስገን እንወዳለን።

ለተጨማሪ መረጃ

1. ዋና ፅ/ቤት አዲስ አበባ

- ወ/ሮ ሱክራን አክበር - ስራ አስኪያጅ - 00 251 983 754146

- ወ/ሮ ገነት ፍሬሰንበት - የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ - 00 251 91 120 7854


2. ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቡታጅራ

አቶ ሰመሩ ስርዋጃ ቅርንጫፍ ስራአስኪያጅ - 00 251 913444368


3. ዱባይ

አምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ ቦርድ ሰብሳቢ - 00 971 508197062

4. አዲስ አበባ

አቶ ኽይሩ ስርጋጋ ም/ቦርድ ሰብሳቢ - 00 251 911426436


5. ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ ቅርንጫፍ

  • አቶ ኢዱና አህመድ ኡስማን (ሰብሳቢ) - 00966 535217526

  • አቶ መሃመድ ሳኒ ሞሳ (የሂሳብ ሹም) - 00966 539170351

  • አቶ አህመዲን ውልጫፎ - 00966 564603531


6. በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ዋና አስተባባሪ

  • አቶ ዳኛቸው ፍሰሃ ውልጊቾ

  • ወ/ሮ ቀመርያ አደም ሐሰን

  • አቶ ሳዲቅ አህመድ ኡስማን

የስልክ ቁጥር 0013017958196


7. አውሮፓ ለንደን ዋና አስተባባሪ

አቶ ሩድዋን ከድር 0044 7475 733865


8. ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ ዋና አስተባባሪ -

አቶ ታሪኩ ጀማል ኑሪ 002761 663 7556 በመደወል አስፈላጊውን መረጃ ያገኝሉ።

የመስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት ፅ/ቤት

459 views1 comment