top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

በመስቃን ማህበረሰብ ላይ ያጠላው ከባድ አደጋ!

Updated: Apr 19, 2022


በመስቃን ማህበረሰብ ላይ ያጠላው ከባድ አደጋ!

የተከበራችሁ የመስቃን ማህበረሰብ ተወላጆች እና ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የሚመለከታቸው ታማኝ የመንግስት አካላት ቀጥሎ የተቀመጡት ሐተታዎች በአቶ እርስቱ ይርዳው የተጫነባቸውን እርኩሳዊ ሃሳብን የመስቃን ወረዳ አመራሮች እምቢኝ ብለው በማሽቀንጠር ውድቅ ያደረጉበትን የስብሰባ ሁኔታ በደረሰን መልኩ አቅርበነዋል።


የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶቻችን ክስተቱ እንደሚከተለው ነበር።

የመስቃን የአራቱም መዋቅር አመራሮች፦

1. የምስራቅመስቃን ወረዳ

2. የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር

3. የነባሩ መስቃን ወረዳና

4. የቡታጅራ ከተማ አስተባባሪዎች

ባለፈው ሐሙስ ክልል ተጠርተው በነ እርስቱ ይርዳው አና በጉራጌ አስተባባሪዎች የወረዳ ስያሜ ጉዳይ እንዲያስፈፅሙ ማስፈራሪያ ጭምር ቢደረግባቸውም ስልጣናችን ውሰዱት እንጂ በዚህ ጉዳይ ፈፅሞ አታስቡት አይሆንም ብለው ፍጹም በሆነ ፅኑ አቋም እምቢታቸውን አሰምተው መጥተዋል። ነገር ግን የሠባት ቤት ካድሬዎች መስቃንን ቆራርሶ ለማሽመድመድ በግልፅ በዶቢ ባለሀብቶችና በማረቆ ተወላጆች በኩል ረብጣ ገንዘብ የፈሰሰላቸው እስኪመስል ድረስ ይህንን የስያሜ ጉዳይ ሳናስፈፅም ቤት አንገባም የሚል ፅኑ አቋም ይዘዋል።

ውድ ተወላጆቻችን የሰባት ቤት ጉራጌ ባለስልጣነት የመስቃን አካባቢ እንዳይረጋጋ በማድረግ ሁለት ነገሮችን ለማሳካት ይፈልጋሉ፦

  1. ዶ/ር አብይ ባለፈው አቅጣጫ ሲያስቀምጡ ጉራጌ ለብቻው ክልል አይሰጠውም፡፡ ነገር ግን ስልጢ ዞን፣ ሀላባ ዞንና የም ልዩ ወረዳ ጨምሮ በክላስተር ይደራጅ፡፡ ማዕከሉም ቡታጅራ ይሁን በማለት አስቀምጠውት በነበረው አቅጣጫ ሌሎቹ ዞኖች በአቋም ሲስማሙ ሰባት ቤት ጉራጌ ግን በሐሳቡ ባለመስማማት ቡታጅራ ማዕከል ከሚሆነው ክልሉ ይቅርብን እኛ ለብቻችን ክልል ይሰጠን እንጂ ከሌሎች ደባል መሆን አንፈልግም ስላሉ በአንድም ይሁን በሌላ ይህ ጉዳይ እንዳይሳካና አካባቢውን እንደለመዱት የስጋትና የጦርነት ቀጠና እንዲሆን ለምስራቁ ጉራጌ አጀንዳ መስጠት ነው።

  2. በአሁኑ ሰዓት የመስቃን አመራሮች እና የሰባት ቤት አመራሮች ሴራ እጅጉን ስላንገሸገሸው መስቃን አራት /4/ መዋቅር ይዞ፣ ሶዶ ሶስት / 3/ መዋቅር ይዞ ፣ ማረቆ እራሱን አስችሎ እና ሰባት ቤት ጉራጌ እራሱ ችሎ ከሚደራጀው ጋር በክላስተር ይደራጅና እኛም ብቻችን ምስራቅ ጉራጌ ልዩ ዞን መሆን አለብን የሚል የጋራ አቋም የያዝን ስለሆነ ይህንን ሀሳብ ለማጨናገፍ እና ምስራቅ ጉራጌ ውስጥ ያለው ማህበረሰብ እርስ በእርሱ እንዲበላላ ማድረግ። በተጨማሪም የያዘውን አቋም እንዲያፈርስ መስቃን እና ማረቆ እና መስቃንና ዶቢ የሚለው ጥያቄ ምላሽ እንሰጣችኃለን በሚል የማማለያ ሀሣብ እና በታትነውን ጉራጌ እራሱ ችሎ ክልል እንዲሆን እንዲደግፏቸው ማድረግ ነውና ይህ መሰሪ አካሄዳቸው በደንብ ተረድተን እኛ መስቃኖች በሀገር ቤትም በውጪም ያለን የጋራ አቋም ይዘን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን አጠናክረን እኩይ ሴራቸውን ማክሸፍ አለብን ።

ይህ ወላሂ ሱመ ወላሂ ሳልጨምር ሳልቀንስ ሀቅ ነገር ነው ያስቀመጥኩት፡፡ በማለት ሃሳባቸውን ይቋጫሉ።


በሃገርም ሆነ ከሃገር ውጪ የምትኖሩ የመስቃን ማህበረሰብ ተወላጆች የሰባት ቤት ጉራጌ ባለስልጣናት የመንግስት መዋቀርን ሽፋን በማድረግ ለአመታት ይፈጽሙት ከነበረው በባሰ ሁኔታ የመስቃን ማህበረሰብን ለማሸበር እና የተለመደውን ወያኔያዊ ተግባራቸውን ለማስፈጸም ቆርጠው ተነስተዋል። አካባቢው ወደ ከፋ ግጭት ውስጥ ከመግባቱ በፊት በፌደራል ደረጃ ለሚገኙ ለሚመለከታቸው የመንግሰት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ሐላፊዎች የጉዳዩን አደገኛነት በማሳወቅ በመንግስትን መዋቅር ሽፋን በመስቃን ማህበረሰብ ላይ እኩዩ ተግባር እንዲፈጸም በዋነኝነት እየሰሩ የሚገኙት የደቡብ ክልል መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የጉራጌ ዞን አስተዳደር አቶ መሃመድ ጀማል ከእኩይ ድርጊታቸው ተቆጥበው የጉራጌን እና የደቡብ ማህበረሰብን በእኩል እንዲሁም ሰላም እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲያስተዳድሩ በተጨማሪም በህዝብ ላይ እየፈፀሙት የሚገኘው ወንጀል ተጣርቶ አስፈላጊው እና ህገ መንግታዊ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መደረግ መቻል አለበት።

ተወላጁ ልክ የመስቃን ማህበረሰብ እድገት እና ብልጽግናን እውን ለማድረግ እንዲሁም ከጉዳት ለመጠበቅ በአንድ በተበጀ ቦይ በአንድነት ከመሄዱ ባሻገር መስቃንን ለማሳደግና ከጉዳት ለመከላከል እየሰሩ የሚገኙት አመራሮቻቸን እና ቀደምት አመራሮቻችን በተጨማሪም በተለያየ ዘርፍ የመስቃንን መብት ለማስጠበቅ እየሰሩ የሚገኙት እህትና ወንድሞች ተወላጆቻችንን ከአስፈላጊው የሃሳብ እገዛ በተጨማሪ ትግልን ለማቀጣጠል እና ወደ ተፈለገው ግብ ወይም ከፍታ ለማድረስ ይረዳ ዘንድ ተወላጁ በሙሉ የፋይናንስ እገዛ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።


ሰላም እና ብልፅግና ለመስቃን ማህበረሰብ!


Meskan Media Network

April 16 2022




249 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page