top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ባለሶስት እግሩ (ባጃጁ) ፖለቲካችን (ታሪኩ ጀማል ኑሪ)

Updated: Aug 3, 2023


ባለሶስት እግሩ (ባጃጁ) ፖለቲካችን (ታሪኩ ጀማል ነሪ)

እንደ ሀገር የገባንበት መአት ሁሉም የራሱን ጥግ ይዞ በሌላው ላይ በማላከክ ወደማያባራ ትርምስ እየተንደረደረ የኢትዮጵያን ጠላቶች ህልም ለማሳካት እየሰራ ይገኛል:: ከዚህ ደግሞ እንደ አጠቃላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዛሬ ያለውን ጭላንጭል እንኳ ማየት እማይችልበት ጊዜ እሩቅ አይደለም።

ዛሬ አገራችንን እያመሳት ያለው ሶስት ቦታ የረገጠ የፖለቲካ አካሄድ ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎች መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ የኦሮሞ የአማራና የትግራ ይፅንፍ የረገጡ ኤሊቶች የሚመሩት ቅጥ ያጣ የፖለቲካ አካሄድ አንድ እግሩን ጫካ ሁለተኛውን በሰላማዊ ተቃውሞ ስም አገር ውስጥ ሌለኛውን በገዢው ፓርቲ ውስጥ በመርገጥ አገሪቱን የማያባራ ነውጥ ውስጥ ከቷታል። በጃዋር የሚመራው የጥላቻ ትርክቶችን በመዘርዘር በአማራጥላቻ የተመረዘ ፖለቲካውን ያነገበው የኦሮሞ ፅንፈኛ በ2016 ለንደንላይ ባፀደቀው መግባቢያ ሰነድ ኦሮሞ ያልመራት ኢትዮጵያ ትበተን በሚልሁ ሉንም ለመሰልቀጥ እየጣረ ይገኛል። ሰላማዊ ትግሉ እንደ ማያዋጣው አምኖ ጫካ በረገጠው አግሩ(ሸኔ) አማካኝነት አንድ ዘርላይ ፍጅት በመፈፀም ህዝቡን በማማረር ህዝብን ወደ ተቃውሞ በመግፋት የመንግስትን ተአማኒነት በመሸርሸር እና ጥርጣሬ ውስጥ በመክተት ወደ ሌላ ፅንፍ እንዲገባ የተሳካ ስራ እየሰራ ይገኛል።


ሸኔን እንደ ግብአት የሚጠቀመው በደርጉ ሺአለቃዳዊት ወ.ጎርጊስ/ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፅንፍ የረገጠ ቡድን ሁሉንም ኦሮሞ በጠላትነት በመፈረጅ ኦሮሞፎቢያን የትግሉ መሠረት አድርጎ ጫካ ገብቻለሁ ካለ ወራቶች ቢቆጠሩም ውጤቱ የአማራን የስራ ሀላፊዎችን በመግደልና በማሳደድ የክልሉን ሰላም በማናጋት ስራውን ሀ ብሎ የጀመረ ይመስላል። ሌላኛውና የትግራዩ ፅንፈኛ ቡድን ደግሞ በሄደበት የሀይል መንገድ በህዝብ ትግል ዋጋውን አገኝቶ በሰላም ስምምነት ስም ወደሰላማዊ ትግል ተመልሻለሁ ቢልም እንደ ላይኞቹ አሱም እራሱን በሶስት የከፈለ ይመስላል:: እነዚህ ደግሞ ትግራይ ያልመራት ኢትዮጵያ መቸም ለትግራይ አትሆንም:: በሚልፈሊጥ ያለፈውን አገዛዛችን መመለስ ባንችል እንኳ አገሪቷ ስትታመስ የሚገኘውን ቀዳዳ ተጠቅመን እምንችለውን ነገር እናድርግ በሚል ይመስላል አካሄዳቸው። የነዚህ የሶስቱ እንደምሳሌ አነሳን እንጂ ሌሎች ጋር ችግር የለም ማለት አይደለም:: የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥያቄ የጋምቤላና የቤኒሻንጎል ታጣቂዎች ቸግር መንግስትን ከህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ እያደረጉት ይገኛሉ።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ፅንፍ የረገጡ አስተሳሰቦች የነበሩ ያሉ ወደፊትም ሊኖሩ የሚችሉ ቢሆኑም እንዲ ፋፍተው የሀገር ስጋት እዲሆኑ ያገዛቸው ብዬ እንደራሴ እማምነው የብፅግና ካድሬዎች ውልደትና እድገት ይመስለኛል:: ምንያቱም እነዚህ ካድሬዎች በህውሀት መራሹ ኢህአዴግ ተመልምለው ለአቅመ ካድሬነት ሲበቁ በቂምና በጥላቻ ፖለቲካ ስለተጠመቁ ነው። ምንአልባት ጥቂቶች ከዚህ በሽታ የመፈወስ እድል አግኝተዋል ብንልም ብልፅግና እንደሽንፍላ ታጥቦ አለመጥራቱን የአቶ ሽመልስና ሌሎችም እሚያሰሙት ዲስኩርና እየሄዱት ያለበት መንገድ እንደማስረጃ ቢቀርብ ለአንባቢ እንግዳ ይሆናል ብዬ አላስብም። እርግጥ ነው ከላይ የተጠቀሱት ፅንፈኞች ንድፈ ሀሳብና የጥፋት መንገድ ስልታዊ በሆነና በረቀቀ ስልት የፅንፈኛ ኤሊቶት ጭኖቅላት በሚመጥንና የግል ጥማታቸውን በሚያረካ መንገድ በማሳየት ሳያውቁት ትግላቸው ተመጋጋቢ እንዲሆንና በአቅም ችግር እንዳ ይገጥማቸው ሀገራችንን በሀይማኖት በመልክአም ምድርና በታሪክ ያፈራቻቸው ጠላቶች መኖራቸው አሌ የማይባል ሀቅነው።

በመጨረሻም አገርን ለመታደግ እነዚህ ፅንፈኞች ብልፅግና የረገጠውን እግራቸውን መንቀል ዋነኛው ብልፅግና ላይ ያሉ አገር ወዳድ ካድሬዎች የተጣለ ከባዱ ሀላፈነት ነው:: እንዴት ብትሉኝ? ለእኔም ከባድነው:: ነገር ግን የፈጣሪ አገዛ ባይታከልበት ህውሀት በዚህመልኩ ተፍረክርኮ ከመሀል ጥግ ይይዛል ብሎ የገመተ አልነበረም።

እናም ለህዝባችን ስክነት ለመከለከያችን ጥንካሬ ብልፅግናም ውስጥ ሆነ በሰከነ ፖለቲካ ውስ ያሉትን የኢትዮጵያን ትነሳኤ የሚመኙ ቡድንና ኤሊቶች ህብረትን ሰጥቶ ፈጣሪ ከመጣው መአት ሀገራችንን ይታደጋት።

አሜን!!! ታሪኩ ጀማል ነሪ


60 views0 comments

Comments


bottom of page