የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ተው!! - በአብዱ ሰዒድ

ተው!!
የተስፋዋን ጭላንጭል ድርግም!
የፀሐይዋን መፍካት ጭልም!
የንጋቷንዘመን ርዝም!
እያደረግክባት ተው አትነግድባት!
የመሻገሪያዋን ድልድይ ስብር!
የመናገሪያዋን ቃል ቅብር!
የማደሪያዋን ቀዬ ሽብር!
እያስደረግክባት
ተውአትቀልድባት!
የልጆቿን እድሜ ቅጭት!
ቂምበቀል ጥላቻን ቅብት!
ግፍና ሰቀቀን ዝርት!
እያስደረግክባትተው አትሸልልባት!
ተው!
ተው ባይጠቅምም ቃሉ
ተው ነው ሰው አመሉ!!!
ተው…