top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

አስምረህ አንጥረህ የንዝረቱን ፓተርን ተከታተልልኝ‼



በዐብድልጀሊል ሸህ አሊ ካሳ


እባክህን ፅሁፋ ረዘመ ብለህ አትለፋው፤ አንብበው ጉዳዩ ከባድ ነውና!


በአገሪቱ ግዙፍ ፕሪጀክቶች እየተካሄዱ ነው። ንዝረቱን ማዳመጥ ከቻልክ ጠጠር ሲወድቅ የሚሰማ ንዝረት አይደለም! የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነው። አንዛሪዎቹ እነማን ናቸው? አንዱ ዝሆን ከታች ያለው ነው። ተለይቷል። ሌላኛውም መንግሥትነትን የወረሰው ነው። እሱም ተለይቷል‼ ሌሎቹ እነማን ናቸው?


1982 ብላቴ ማሰልጠኛ ከገቡት መካከል ሁለት ቡድኖች ተደራጁ –የሙስሊምና የኦ/ክርስቲያን ማህበራት።


1983—1987 የሙስሊሙ ሙነዘማ የሚባል ቅርፅ ያዘና መሬት ያልቆነጠጠ፣ ኢትዮጵያን ስሪት ያላገናዘበ ያልበሰሉ እንቅስቃሴዎችን አደረገ፣ዓለምአቀፋዊ ሙስሊምነት ሰፊነት ላይ ነበሩና የቆሙባቸውን ማስቀደም አልተቻላቸውም ነበር። ግን ደግሞ ብዙ ተስፋ የሚጣልባቸው ነበሩ። ከረጅም የአፈና ዘመን በኋላ የመጡ ነበርና በአንድ ጊዜ ሮጡ፣ ስህተታቸው ቀስ ብለው አለመሮጣቸው ብቻ እንጅ ግሩም ፣ ድንቅ ትውልዶች ነበሩ። ግና ስለ ኢትዮጵያ state Machine ስሪት በቅጡ የተረዱ አይመስሉም። በአፄው ዘመን የነበረው ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊነቱን assert የማድረግ ትግል ተቀዳሚያቸው የነበረ ይመስላል። ግና በተቀነባበረ ሴራ የ1987ቱ የአንዋር መስጅድ ግርግር ተስፈኛው የብዙ ሚሊዮኖቹ አደረጃጀት ፈረሰ፣ አባላቱ ታስሩ፣ ተገደሉ፣ ተሰደዱ። ድርጀቱም ታሪኩም ተዳፍኖ ቀረ። አከተመ‼


1982/4 –1997 ማህበረ ቅዱሳን የተሰኘ እጅግ ጠንካራ ተቋም ተፈጠረ፣ ምን መሥራት እንዳለበትና ምንን ማስቀደም እንዳለበት በቅጡ የተረዳ፣ አባላት በሰፊው የሚመለምል፣ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ የሞነሳ፣ በርካታ ሴኪዪላር በሚመስሉ ኢትዮፕያኒስትና በወቅቱ በአማራ ዘውግ ላይ ባተኮሩ ፓርቲዎች አካባቢ የሚያዘወትር። ከአፄው ሥርዓት የቀጠለውን ቢሮክራሲ ኃይል እንዳሻው የሚዘውር! አስፈላጊ ሲሆን በሚገባው የሚጠቀም።


ኢህአዴግ ማህበሩን ከመላ አማራ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጋር ያለውን ስውር መዋሰብ ደርሸበታለሁ ብሎ በድርጅቱ ላይ ዓይኑን ጣለ። ማህበሩ ሴኪዩላር በሚመስሉ ልሳናት periodicals በኩል በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል። ከ1984–1998 የሰበሰባቸውን የተዛቡ መረጃዎች ለመንፈሳዊውም ለአለማዊውም የግቡ መዳረሻዎች በማዋል የዘመኑን ጥናቶች፣ ምርምሮች፣ ሚዲያዎች፣ ለመፃኢው ንድፉ አውሏቸዋል።


በ1997ቱ ምርጫ ከቅንጅት ጋር ተያይዞ ብዙ ድርሻ እንደነበረው ኢህአዴግ ደጋግሞ ወተወተ። የቅንጅት እንቅስቃሴ ውስጥ ጭሶቹም ታዩ።


1998—2005 ድረስ የሙስሊሙን ኃይል ለአንዴየና ለመጨረሻ ጊዜ ይደፍቅልኛል ያለውን ሴራ እጅግ በጠነከረ መልኩ አሴረ። ሙስሊሙ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የኢህአዴግ አደገኛ ስጋት መሆኑን ሊያሳዩለት የሚችሉ ሁለንተናዊ ርብርብ አደረገ። ከዓለም አቀፍ አጥኚዎች እስከ ተራ ፀሀፊዎች ድረስ ርብርብ አደረጉ። ዝርዝሩ ኪስ ይቀዳል።


2004—2009 ድረስ የመንግሥትን "የፀረ–ሙስሊም አክራሪነት ዘመቻ" ቢሮክራሲውን በመጠቀም ለራሳቸው ድብቅ አላማ በተለየ መልኩ ተጠቀሙበት፣ አደረጃጀቶቻቸውን በመጠቀም ጠንካራ የእስልምና እንቅስቃሴ ይካሄድባቸዋል በሚል ቀድመው በለዩአቸው ከገጠር እስከ ከከተማ ባሉ ቀጠናዎች ሙስሊም ልሂቃንን፣ አንቂዎችን፣ ጠንካራ ሙስሊሞችን ታርጌት ያደረገ እንቅስቃሴ አደረጉ። ትጥቁና ዕዙ ከመንግሥት ነው፣ የጃንሆይ "ሰይፉ እኛ ብንሆንም ክንዱ ቤተ ክህነት ናት‼" ያሉት ነገር ዳግም እውን የሆነ መሰለ።


ከ70ሺ ሙስሊሞች በላይ ታሰሩ፣ በአስር ሺዎች ተሰደዱ፣ በረረካቶች ተገደሉ። የአገሪቱ የእስልምና እንቅስቃሴ ቀጥ ብሎ የኋሊት ተምዘገዘገ። መድረሳዎች ተዘጉ፣ መርከዞች ተቆለፉ፣ ሐሪማዎች ደረሶቻቸውን በተኑ፣ የሙስሊም የፅሁፍና የተንቀሳቃሽ ምስል ሚዲያዎች ተዘጉ። የደዕዋ ሥራ ቀጥ አለ። መፅሐፍት መታተም ቀረ። ሁኔታው የተመቻቸላቸው ማሳያ ሙስሊም አክራሪዎች ደግሞ በነፃነት ብቅ ብቅ አሉ። እነማን ናቸው? ዝርዝሩ ኪስ ይቀዳል አሁንም። የኢህአዴግ ምልምሎች ብቻ መሆናቸውን ያዝልኝ!


የመንግስት ዓላማ hijacking ደረሰበት። በየጣቢያው የነበሩ ምርመራዎች የመንግሥትን ዓላማና አቅጣጫ የተከተሉ አልነበሩም። ስለ ቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የነበረ ምርመራ ፕሮግራም ተጠልፎ ስለ ኢስላማዊ መንግስት፣ ስለ አልሸባብ፣ ስለ መስጅዶች ብዛት ነበር።


2005—2010 የሙስሊሙን ድምፃችን ይሰማ ትግል ለራሳቸው ግብ መጠቀም በሚያስችላቸው መልኩ ለመጥለፍ ወይም ህወኃት/ኢህአዴግን ለመጣል ትግሉን ለመጠቀም ሰፊ እጆችን ሰግስገውም ተጠቅመውበታል።


በሌላ በኩል በድህረ ኅወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት ስለሚጣው ኦርቶ–መንግሥት አመቻማች የሚሆኑ በትካታ አደረጃጀቶችን በመዘርጋት የብሔር ቅርፅና የአሃዳዊነት ቅርፅ ያላቸው ፓርቲዎችን ከጀርባ ሆነው ፈጥረዋል አደራጅተዋል። የአማራ ብሔርተኛ ድርጅቶች የማህበሩን አደረጃጀቶች፣ የፅዋእ ማህበራትን አደረጃጀቶች ተጠቅመው እንዲደራጁ ተደርጓል።


2010—ሐምሌ/2011 ሴኪዩላር በሚመስሉ የብሔርና አሀዳዊ ፓርቲዎች በኩል መፃኢ ኦርቶ–መንግሥት ወይም ኦርቶ ዘመም መንግሥት ለመፍጠር ጥረቶች ቢኖሩም የጴንጤ–ኦሮ መንግስት በአንድ በኩል የጃዋር እንቅስቃሴ በሌላ በኩል እጅግ አይነኬና አይቀመስ ሆነው በመምጣታቸው በአማራ ክልል በኩል የተለየና ከዚያ ነጥሮ የሚመጣ አደረጃጀት ለመፍጠር ብዙ ተሞከረ።


በተለይም በአብን፣ በአዴፓ፣ በአርበኞች ግንባር በኩል ከአማራ ክልል ተነስቶ ወደ አራት ኪሎ የሚጫን ኃይል ለማደራጀትና በዚያ በኩል ከፍተኛ መረባረብ ተደርጓል።አብን በተወሰነ መልኩ ከላይ በኩል ራሱን በይፋ ከስውሩ ፅንስ ለመላቀቅ ሞከረ። አባላቱ ግን አሁንም ዝርዝሩ ኪስ ይቀዳል።


ሰኔ/2011 የማህበሩን ልዩ ተልእኮ በተለየ መልኩ ባረገዙ የ8ወር እርጉዞችና በተወሰነ መልኩ ዓላማውን ከማህበሩ በፀነሱ የ3ወር እርጉዞች መካከል አንተ በጣም አማራ አይደለህም ተባብለው ተላለቁ። ፅንሱ እንደሰይሆን ሆኖ የabortion ስጋት ደረሰበት። በሴኪዩላር አደረጃጀት ሽፋን ፅንሱን ማስቀጠል የሚችል ማህፀን የጠፋ መሰለ።


ሐምሌ/2011–ሰኔ/2012

ቤተ–ክርስቲያኒቱ ፅንሱን በኪራይ ማህፀን ለማሳደግ መሞከሯን ትታ ቀጥታ ራሷ ፅንሱን ወልዳ ለመንግሥትነት እንድታበቃ አጀንዳው ወደ ቤቱ ተመለሰ። የቤተ–ክርስቲያኗ ጥቃት ፖለቲካዊ ትርጉምና ተልዕኮበ እየተሰጣቸው ሰፊ ርብርብ ተደረገ፣ ዋይታው………ኡኡታው………እሪታው ቀጠለ። አማራ ክልል በይፋ የኡኢታው ዋና ማይጋፎን ሆነ። የሚና መደበላለቁ ተጧጧፈ። victimhood እንቅስቃሴ ያለ የሌለ እሪታ ቀጠለ፣ "ክርስቲያን መስሎ አታለለን» ተባለ። የኦሮሚያ ቤተ–ክህነት የሚባል ማስለቀሻ አጀንዳ ተፈጥሮ ወደ አደጋ ከመቀየሩ በፊት ወደ ቦዩ ተመለሰ።


ቤተ ክርስቲያኗ በይፋ የታጠቁ፣ የተደራጁ፣ የቤተ–ክርስቲያኗን ክብር አስመላሽ ግብረ ኃይል እንዲቃቋሙ አፀደቀች። የጴጥሮሳውያን ህብረት ሚሊዮኖችን ይዞ ተነሳ። ይፋዊ የታጠቁ ግብረ ኃይሎች እንዳሏት ተሰበከ። ተነገረ። ቀውሱ ተጧጡፎ አርቲስት ሀጫሉ ተገድሎ በነጃዋር መታሰር የስኬቱን እረካብ የጨበጠ መሰለ።


ጥቅምት/2013—ህዳር/2014

በዚህ ወቅት ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት ከትግራይ በኩል ያለውን ጣጣ በሴኪዩላሩ መንግሥት በኩል ይዞ ሄደ።


ከዚያ ሁሉ እልቂት በኋላ መንግሥት እርቅ ብሎ መጣ።


ድህረ ህዳር/2014 በትግራይ በኩል የታቀደው የከሸፈ መሰለ። ፅንሱ ድጋሚ የabortion ስጋት ደረሰበት። አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ አጀንዳው ወደ ቤቱ ተከተተ። የመስቀል አደባባይ የኛ ነው እሪታው ቀጠለ። የወይብላ ማርያም ኬዝ ተፈጠረ።


ጥር/2014 እንደ ትናንቱ ሁሉ የኦርቶዶክሳውያንን ጥያቄ በማንኛውም መልኩ የሚያስመልስ "የሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል" ተቋቋመ።



እስላሙ አረቢያን መጅሊስ ተወዶበት ለሁለተኛ ሚስቱ ሶፋ በመግዛቱ እየተበሳጨ ነው።

20 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page