top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

አዎ ፈሪ ነኝ !

ለዚህም ምክንያት አለኝ ። አዎ ፈሪ ነኝ ምክንያቱም በእኔ የአንድ የቃላት ውርወራ ወይም ጽሁፍ ብዙዎች ይጎዳሉ። ብዙዎችም ይረበሻሉ ። እኔ ለጊዜው ስናገረው ወይም ስፅፈው ላይመስለኝ ይችላል ። እንደተመቸኝና አእምሮዬን ሀሳብ እንዳፈለቀልኝ ያለምንም ማስተዋል እፅፍና ብዙዎቹ እጎዳለሁ። አንድ የቃላት ውርወራ በተጠቀምኩ ቁጥር የምጎዳቸው ብዙሀን ስለሚመስሉኝ ዝምታን እመርጣለሁ ።ሰላምን እሻለሁ። ታዲያ ይህ በብዙዎች እይታ ፈሪ ያስብለኛል ። ለህዝቤና ለሀገሬ ስል ሰላም መምረጤ ፈሪ ካስባለኝ አዎ በጣም ፈሪ ነኝ ። ምክንያቱም ከህዝብና ከሀገር የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ። ያንዱን ሰላም በመፈለግ የራሴን ስሜት እየተከተልኩ የመጣልኝን ከመፃፍና ከመናገር ከተቆጠብኩ ይህም ፈሪ ካስባለኝ አዎ... ፈሪ ነኝ! ለዛውም የሀገሬ እና የወገኔ ሰላም የሚያሳሳኝ ፈሪ። ብዙውን... ጊዜ በብዙዎች ዘንድ የመጣላቸውም ይሁን ያሰቡትን ከመናገር የማይቆጠቡና ከአንደበቴ ምን ይወጣል ብለው ሳያስቡ ይናገራሉ ይፅፋሉ ። ግና... የተናገሩትም ይሁን የፃፉት ለመልካም አስበው ካልሆነ በስተቀር እንኳን ለሀገርና ለህዝብ ቀርቶ ለግለሰብ የማይጠቅም ሆኖ ነው የሚገኘው። ይሁንና ከጽሁፎቹ መካከል የሀይማኖት ትምህርቶችና ጽሁፎች ብቻ ሲቀሩ በተጨማሪም ሰዎች በመልካም እና ለመልካም ብለው የሚጥሩት ሲቀሩ ሁሉም ፍሬ ከርስኪ ናቸው። የሆነው ሆነና ያሰብኩትን ነገር በሙሉ በንግግርም ይሁን በጽሁፍ ወደ ሶሻል ሚዲያ ለማድረስ የሚሰማኝን ወይም የውስጤት ሃሳብ አውጥቼ ለማካፈል ህዝብን ከህዝብ በተጨማሪም ግለሰብን ከግለሰብ ያጫርሳል ብዬ እሰጋለኩ! ለዚሁም ሁሌ እራሴን እጠይቃለሁ "ዝም ብል ምን እጎዳለሁ"? በማለት። ነገር ግን በሌሎች ዘንድ ፈሪ ቢያስብለኝም ለመልካም ታስቦ እስከሆነና ለሌላው ሰላም ተፈልጎ እስከሆነ ድረስ ፈሪ ሊያስብለኝ ይችላል ። ይሁንና የግል ምክንያቴ ፈሪ ካስባለኝ አዎ 100% ፈሪ ነኝ። ይልቁኑ ለምንናገረውና ለምንፅፈው ነገር እኛው እራሳችን ሀላፊነቱን እንውሰድ ። "አንተ ከሶፋው ላይ ቁጭ ብለህ በመደብ የተቀመጠውን ህዝብ በመጥፎ አታነሳሳ" ብለዋል የተከበሩት ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ አብይ ። እላይ ለተጠቀሰው የጠቅላያችን አባባል ዋነኛ ምክንያቶች በተለያዩ የስደት አለም ቁጭ ብለን ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን አንጣር። ለፈላጭ ለቆራጭነቱ ከህዝብ ጎን በህዝቡ ፍላጎት የተሰየመ አካል ይገኛል እና አርፈህ ተቀመጥ። በተጨማሪም ለግል ተራ ፍላጎት ጥቅም ሲባል ማህበረሰቡ ውስጥ ሁከት ከመፍጠር እንቆጠብ ዋጋ ያስከፍለናል። እናስተውል ጎበዝ!

Written By Semu Bint Shifa

34 views0 comments
bottom of page