• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ኢትዮጵያ እና ጠላቶቿ ( ታሪኩ ጀማል ኑሪ)


በኢትዮጵያ ላይ ለሚፈጠሩ ውስጣዊ ችግሮች ሲተነትኑ ብዙዎች ምንጫቸው ከውጭ የመጡና አገር ውስጥ ባሉ በጥቅምና ባለማውቅ የተሳሳቱ ትርክቶችን በመቀበል ና በማጉላት እርስ በርስ ጥርጣሬን በማንገስ አገሪቷን በማዳከም ፈራርሳ እንድትጠፋ የጠላትን ህልም ለማሳካት በሚደረግ ሴራ ነው።

ለመሆኑ እነዚህ ጠላቶቻችን በስንት ይከፈላሉ ምክንያታቸውስ ምንድነው ብሎ በመጠየቅ እኔ ለራሴ ወደሰጠሁት ምላሽ ይወስደናል ሁሌም ስለሀገሬ ሳስብ ና መቋጫው ምን ሊሆን ይችላል ብዬ ሳስብ እዳቅሚቲ የራሴ የሆኑ መላምቶችን በማስቀመጥ ለራሴ መልስ ስሰጥ ቆይቻለሁ። አሁን ግን አገራችን እምትገኝበት መስቀልያ መንገድ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል መርህ ላይ ቆመን አገር የማዳን እንቅስቃሴዎች ላይ የራሳችንን አቋም እምንለካበት ግዜ ላይ መሆናችንን ልብ ብለን ቀዳሚ በሆነው ነገር ላይ ያለልዩነት መዝመት ግዴታ ይሆናል አለበለዚያ በጥቃቅንና ግዜ ባለፈባቸው ነገሮች ስንነታረክ የሳት እራት ሆነን አገር አልባ እንዳንሆን እሰጋለሁ።


ጠላቶቻችን ከሶስት ምንጭ ይቀዳሉ።

1- ከሀይማኖት

2- ከታሪክ እና

3- ከመልከአም ምድር ናቸው


እስቲ ዘርዘር አድርገን እንመልከታቸው:-


1. ሀይማኖት

በብዙ ኢትዮጲያዊ ዘንድ የሀይማኖት ግጭት ሲነሳ ከአረቦችና ከእስልምናጋር የማያያዝ ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ነገር ግን አረቦች ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አፍራሽ ተልኮ ፍፁም ከሀይማኖት ጋር የተያያዘ ሳይሆን በሶስተኛነት በምናነሳው ምክንያት ባላቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቅምና አረባዊ ወገንተኝነት የተቆራኘ ብቻ ነው ባይ ነኝ ምክንያቱም በእስልምና ታሪክና ነባራዊ ሁኔታ እውን በትክክል ቅዱስ ቁርአንና መልአክተኛውን ነብዩ መሀመድን(ሰአወ) መልእክትን እሚቀበሉ ሙስሊም ከሆኑ ኢትዮጵያን ሊያከብሯት ግድ ስለሚላቸው ና በእስልምና ተከታይም ቢሆን ከብዙ አረቦች የሚልቅ አማኝ እሚገኝባት አገር ነች ሙስሊም ሀገሮች በሌላ ምክንያት ካልሆነ ኢትዮጵያን በጠላትነት ሊያስፈርጅ ሀይማኖታዊ መሰረት የላቸውምም አይኖራቸውምም። እናስ ሀይማኖታዊ የችግር ምንጭ ከየት በኩል ነው የሚመነጭ ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል? ይሄም ወደሌላ የተሳሳተ ትርክት ይወስደናል ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን እስራኤልን የክርስትና ጠበቃ አድርጎ የመውሰድ ዝንባሌ ነው?

እስራኤል ማለት በአብዛኛው በሚባል ደረጃ የአይሁድ እምነት ተከታይና በዛ አስተምሮት እምትመራ አገር ናት ታዲያ አሁድ ማለት እየሱስ ክርስቶስን በሀሰት ወንጅለው ለስቅላት ዳርገውት እንዴት ስለ እየሱስ ክርስቶስ ሞቶ መነሳትን ለሚመሰክሩ የክርስትና አማኞች ጠበቃ እሚሆኑት?

አናም ለአንድ አይሁድ እምነት ተከታይ ክርስትና ማለት ከሳሽና ሀሰተኛውን ክርስቶስ ተከታይ ማለት ነው።ምክንያቱም በአይሁድ አስተምህሮ ገና እንደሚመጣ እንጅ ከሰመሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ የሚለውን የክርስትና አስተምህሮ ስለማይቀበሉ።

እናም ለጁዳይዝም ክርስትና ማለት ከክርስትናም ኦርቶዶክስ ከኦርቶዶክስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ባላት ጥበቅ አስተምህሮና ከዚያ በቀደሙ የብሉይ ኪዳን ላይ ባሉ ኢትዮጵያን ባስቀደሙ የመፅሀፍ ቅዱስ መእራፎች ላይ ባላት ልዩነት መፅሀፍ ቅዱስን እስከመቀየርና ያደረሳት ብሎም ፅላተ ሙሴን ኢትዮጵያውስጥ መኖር በፍለፊት ባለመቀበል በሚስጥር ፅላቱን ከኢትዮጵያ ለማሠረቅ እያደረገች ያለችውን ዘመቻ ለተመለከተና በሌሎችም ሌሎች በስፋት ሊገልጿቸው በሚችሉ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ መኖር አለመኖር ለተፃፉት ሀሰተኛ መፃፎች ቅቡልነትና ለቀጣይም ላላት ሀይማኖታዊ የበላይነት እንደ ጥርጊያ መንገድ አይታሰብም ማለት የዋህነት ነው።


2. ታሪክ

ሁለተኛው የችግራችን ምንጭ ደግሞ ታሪክ ይኸው ሰሞኑን ልናከብረው ሽርጉድ የምንለው የአድዋ ድል ተሸናፊዋ ኢጣልያ ማመን አቅቷት አመታትን አስቆጥራ ለሌላ ወረራ ተመልሳ መምጣቷ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም እሳቤ ባለፈ የባለፈውን ሽንፈት ቀጣዩን ወረራ አሸንፎ ኢትዮጵያን ዳግም ቅኝ በመግዛት የታሪክ ጠባሳን ለመሻር የታሰበ ቢሆንም አባቶቻችን እሚቀመሱ አልነበሩምና ጣሊያንዬ ዳግም ውርደት ተከናንባ ወዳገሯ ተመልሳለች። ታዲያ ነገሩ የኢትዮጵያ ና የጣልያን ከመሆን በዘለለ የነጭ ኮለኒያሊስት ና የጥቁር ህዝብ ተደርጎ ስለተወሰደ መላው አውሮፓ በጣሊያን ቢሳለቅም ኢትዮጵያን በአውሮፓዊያኖች ጥርስ ውስጥ ከመግባት አላዳናትም ለዚህም ይመስለኛል ሁሌም ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ ስትገባ ፍርደ ገምድል ውሳኔዎችን እሚሰጡትና አገሪቷን ወደመፍረስ አደጋ የሚገፏት።

3. መልከአም ምድር

ይሄኛው ዋነኛውና ከላይ የተጠቀሱትን እንደግብአት በመጠቀም አስፈላጊ ሲሆን ሁለቱንም በሌላ ጊዜ በተናጥል አረባዊ ወንድምነት በሚልና አካባቢው ላይ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን በማስጠበቅ ግብፅ በምትሰጣቸው ችሮታ በእኛ ቁስላይ ያለምንም ርህራሄ እንጨት ሲሰዱ የተለመደ ሆኖዋል። ከቅርብ ጊዜ ቦሀላ ደግሞ የግድቡ መጠናቀቅ እውን ሊሆን ሲቃረብ ግብፆች የሚይዙትን የሚጨብጡትን አሳጥቷቸው ባለበሌለ ሀይላቸው አገሪቷን ለማመስ ከተቻለም ለማፍረስ ማይሸርቡት ሴራ የለም ።

ስለዚ መፍትሄው ምንድ ነው?

አንደኔ መፍትሄ ብዬ እማስበው እንደህዝብ ችግሮች ቢኖሩም በንፅፅር ጥሩ አመራርና ለለውጥ የሚመች ጊዜ ላይ ስለምንገኝ ጥቃቀቅን ችግሮቻችንን በይደር በመተው ትኩረታችንን አገርን ማስቀጠል ላይ ብናተኩርና የለውጥ ሀይሉን ከነግድፈቱ ቢያንሰ ጅምሩ ኢትዮጲያዊ ሽታ ስላለው የጠላት መሳሪያ ሆነን አገር እንዳናጣ ጥንቃቄ ብናረግ።

መንግስትም ሶስተኛውን የችግር ምንጭ ማድረቅ የመፍትሄው ቁልፍ መሆኑን በመረዳት የህዳሴው ግድብን ከማጠናቀቅ ባለፈ ሌለሎች ኢኮኖሚያዊ ጉልበቱን በማፈርጠም የግብፅን ሩጫ ማስጨረስና ከተንኮል ወደ ወንድማማች ትብብር ማምጣት ለነገ የማይባል የቤት ስራ ሊሆን ይገባል።

ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይታደግ!

ታሪኩ ጀማል ኑሪ


39 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean