top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

እራስህን እንደምስኪን ወይም እንደተበዳይ እየቆጠርክ ነውን? መውጫው መንገድ እነሆ… (በሚስጥረ አደራው)


ጥሎብን ምስኪንነት እንወዳለን። ሰዎች  እንዲያዝኑልን አልያም ለራሳችን የምስኪንነት ስሜት እንዲኖረን እንሞካራለን። ለውድቀታችን ለሃዘናችን ወይም የማንፈልገውን ኑሮ ለመኖራችን ሌሎችን መውቀስ ይቀናናል። ምክንያቱም ለህይወታችን አለመስተካከል ሌሎችን ስንወቅስ የጥፋተኝነት ስሜቱን ስለሚቀንስልን። ለደስታችን መደብዘዝ፤ በትምህርት ላለመግፋታችን፤ የምንፈልገውን ኑሮ ላለመኖራችን ምክንያቱን እራሳችን ውስጥ ከመፈለግ ይልቅ፤ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ለውድቀታችን ያደረጉትን አስተዋጽዎ ስናሰላስል ከመፍትሄው ጋር እንተላለፋለን። እርግጥ ነው በአንዳንዶቻችን ህይወት ውስጥ የሌሎች ሰዎች አሉታዊ ተጽዕኖ ቀላል አይደለም። ግን ያለፈው ህይወታችን ላይ መጥፎ አሻራቸውን ጥለው ካለፉ፤ ትዝታቸው ደግሞ የወደፊቱን እድላችንን እንዲያጨልመው ለምን እንፈቅዳለን?

“Feeling sorry for yourself and your present condition is not only a waste of energy but the worst habit you could possibly have” dale carngie

“እራስህን እንደምስኪን መቁጠሩና አሁን ላለህበት ሁኔታ ስለራስህ እያሰብክ መቆዘሙ አቅምህን የሚያባክን ብቻም ሳይሆን፤ ለማስወገድ የሚከብድ  እጅግ መጥፎ ባህሪም ጭምር ነው።” ዴል ካርኒጊ

እርግጥ ነው  ከልጅነታችን ጀምሮ በህይወታችን ላይ የሚያርፈው የሌሎች ሰዎች አስተዋጽዎ ቀላል አይደለም። ነፍስ ካወቅን ጀምሮ ግን ህይወታችንን በራሳችን ቁጥጥር ስር የማድረጉ አቅም አለን። ይህ አቅም  ነፍስ መዝራት የሚችለው ግን  በራሳችን ላይ የተስተካከለ አመለካከት ሲኖረን በቻ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች እራሳችንን ከተበዳይነት  ስሜት እንድናወጣ የሚረዱን ነጥቦች ናቸው-

የዛሬው ህይወትህ የነገውን ማንነትህን ሊገልጸው አይችልም– “If you treat an individual as he is, he will remain how he is. But if you treat him as if he were what he ought to be and could be, he will become what he ought to be and could be.” -Johann Wolfgang- ሰውን አሁን ባለለበት ሁኔታ አልያም ባለፈው ህይወቱ ከዳኘነው፤ ሊሆን የሚችለውን ማንነቱን ወይም ያለውን አቅም  ማየቱ ይሳነናል። አንዳንዴ የማይገልህ በሽታ ይበልጥ ያጠነክርሃል ይባላል። ያሳለፍናቸው መከራዎች እና ፈተናዎች ጥንካሬዎቻችን እንጂ ማነቆዎቻችን ሆነው ቀሪው እድሜያችንን የታሪካችን እስረኛ ሊያደርጉን አይገባም።ትልቁ በቀል የግል ስኬትህ ነው– “The best revenge is massive success” -Frank Sinatra- ወደታችን የጎተቱህን መበቀል የምትችለው ከፍ ብለህ ስትገኝ ብቻ ነው። በቀል ስል አይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ የሚሉት አይነት በቀል ሳይሆን፤ መልካም በቀል ነው። ምናልባት ሰዎች ትላንት በተለያየ መልኩ ጎድተውህ ይሆናል። ሁለተኛ እንዲጎዱህ የምትፈቅድላቸው ግን የበደላቸውን ትዝታ ይዘህ ስትኖር ነው። “እንዲህ ባይሆን ኖሮ……” እያልን በትላንት ላይ ስንቆዝም ዛሬ መፍትሄውን እንደያዘ ከፊታችን ይጠፋል……እራስህን እንደ ምስኪን መመልከቱን አቁም– አንድ አንድ ሰዎች ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ሌሎች ያደረጉባቸውን በደል ሲያስቡ ለመፍትሄ የሚሆን ጊዜ ያጣሉ። እራስን እንደምስኪን ወይም እንደ ተበዳይ መቁጠር በራስ የመተማመንን ስሜት ከማጥፋቱም በላይ በራሳችንም ሆነ በሌሎች ላይ የለንንን እምነት እንድናጣ ያደርገናል። እንደውም ሌሎችን በጥርጣሬ እንድንመለከት የሚይደርገን ትልቁ ምክንያትም  ይህ ነው። ለውስጥህ ሰላም መደፍረስ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች መውቀሱን አቁም- “Stop blaming outside circumstances for your inside chaos.” -Steve Maraboli – የደፈረሰን ኩሬ ከውጪ ሆኖ ሊያጠራው የሚችል ምንም ነገር የለም። የደፈረሰ ኩሬ ሊጠራ የሚችለው መማሰሉ ሲቆም ብቻ ነው። የሰው ልጅም ሰላም እንዲህ ነው በውጪ ሃይል ሳይሆን በውስጣዊ መረጋጋት የሚሰክን መንፈስ ነው። እራሳችንን እንደምስኪን ወይም ተበዳይ ስንቆጥር የውስጣችንን ሰላም በትዝታ ማማሰያ እያደፈረስን መሆኑን እናስታውስ። አየሩን መለወጥ ካልቻልክ አለባበስህን አስተካክል- “You must take personal responsibility. You cannot change the circumstances, the seasons, or the wind, but you can change yourself. That is something you have charge of.” ― Jim Rohn–  እንደሰው አቅማችን ውሱን ነው። በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ የመለወጥ አቅሙ የለንም። ጸሃይዋ ለምን እንዲህ ሞቀች ብለን ከጸሃይ ጋር ሙግት አንገጥምም፤ ሙቀቱን ለመከላከል ዣንጥላ እንይዛለን እንጂ። ሲበርድም እንደዛው። ቀዘቀዘ ብለን ከብርዱ ጋር አይንጣላም፤ ልብስ እንደርባለን እንጂ። ይህ ህግ ለጸሃይ እና ለብርድ ብቻም ሳይሆን ለሁሉም ነገሮች ይሰራል። ሌሎችን ወይም የሌሎችን አስተሳሰብ የመለወጥ አቅም የለንም ልክ የዝናቡን መጠን የጸሃዩን ሙቀት መወሰን እንደማንችል ሁሉ። ስለዚህ እራሳችንን ከሌሎች ቀንበር ለማላቀቅ ይህ አመለካከት ወሳኝ ነው፤ አቅም ያለን እራሳችንን ላይ ብቻ ነው።


በሚስጥረ አደራው

57 views0 comments

Comments


bottom of page