• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

እራስን ከጭቆና ማራቅ ብልህነት ነዉ (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

Updated: Mar 29“እንደ ሃገር ያለዉን ጭቆና ይብቃ ስንል እኔስ ጋር ያለዉ ጭቆና ምን ይመስላል ማለትና እራስን ከጭቆና ማራቅ ብልህነት ነዉ”


አቅላይነት የብልጽግና መዳረሻ አንዱ ፈተና ነዉ ይላል መደመር!


በእኔ አረዳድ በሀገር ደረጃ ይህንን እጅግ አደገኛና ፈታኝ ለዉጥ እንዲመጣ ካደረጉ ነገሮች አንዱ በሃገሪቱ ምንም አድገት አልነበረም ከሚል መነሻ ሳይሆን በእድገቱ ዉስጥ መመዘን ያለበትን የህዝቦች ፍትሃዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በፖለቲካዉ ተያይዞም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማቶችም ስላልነበረ ነዉ፡: ይህንን ለማስተካከልም በዶ/ር አብይ የተወጠነዉ የመደመር እሳቤን፣ የብልጽግና ራዕይና መዳረሻ ወያኔ ኢህአዴግ ከሚለዉ አስመሳይ /ፋልሴቶ/ ህብረብሄራዊ አንድነት ወደ ትክክለኛ እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ወዳለዉ ብልጽግና ጉዞ እወስዳለሁ የሚል እንደሆነ እረዳለሁ። ላለፉት ዘመናት ፖለቲካዉ በሰፊዉ የሚዘወረዉ በአንጻራዊነት አነስተኛ ቁጥር ካለዉ ብሄር ከእሱም ዉስጥ በአንድ አካባቢ የተሰባሰቡና የተደራጁ አካላት ሲሆን ከነሱ ስድስት እጥፍ ከሚበልጠዉን ማህበረሰብ ያቀፉትን ሰፊዉን የኦሮሞና የአማራን ህዝብ በአቻ ግምት በመደልደልና ፖለቲካዉን በመጠምዘዝ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማቱን ለማዛባት ሞክረዋል። እንዴት? የሚለዉ ለመዘርዘር አልዳክርም።

ከዛመለስ ብዬ ከላይ ወደ ጠቀስኩት ሃሳብ ስመለስ እኛስ ጉራጌ ዞን የህዝቦች የፖለቲካ ተሳትፎ ምን ይመስላል? የሚለዉን ልተች። በዞኑ የጉራጌ የቀቤናና የማረቆ ብሄረሰቦች ይኖራሉ በብሄረሰብ ደረጃ ማለት ነዉ ብሄረሰብን ትቼ ወደ ማህበረሰብ ስወርድ እያንዳንዱ አካባቢ ወይም ማህበረሰብ አስከ አሁን በተጻፈም ይሁን ባለተጻፈ ህግ ተሳትፎዉ ምን ይመስላል የሚለዉን እንደሚከተለዉ እተቻለሁ። ወደፊትም ተስተከክሎ ዞናዊ አንድነታችን ተጠናክሮ ሁሉም በሙሉ ልብ እኛ ብሎ ጥያቄዎቹ ሚያቀርብበት መንግስትም ጥያቄዎቹ እንደተነሱ ሚመለሱበትአዉድ ይፈጠራ ብዬ አምናለሁ፡፡

ምሳሌአንድ ፡- የዞኑ የፖለቲካአመራር ምደባ በተመለከተ በብቃትና በችሎታ ብቻ ሰዎች ለአመራርነት ማጨት ከልቤ ምደግፈዉ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ አካባቢዎችን ማመጣጠን ተብሎ በጎሳ/በወረዳ ደረጃ አመራር ለዘመናት ሲመደብ ቆይቷል። ይህም አሰራር ቢሆን ከብረሰተብ ተሳትፎ አንጻር ሚኮነን አይደለም ግን ደግሞ እንደ አሰራር ከተወሰደ ዋና እና ሁለተኛ ደረጃ ጉራጌ አድርጎ ማሳተፉ ለምን ያስፈልጋል? ለምን የዞኑ አስተዳዳሪ ብቃት ያለዉ ሰዉ ከተገኘ ከመስቃኑም ከሶደዉም ከማረቆዉም ከቀቤናዉም ከወለኔዉም ከእንደጋኙም (ሌላው ጎሳ ሆኗል ብዬ ነው ) ቢሆን ችግር የለዉም የሚል ሀሳብ ከመያዝ ባልተጻፈ ህግ አስተዳዳሪ ከነዚህ ማህበረሰብ መሆን አይችልም ተብሎ ሲተገበር 30 አመት አለፈዉ። ለምንስ የዞኑ አመራር ከየማህበረሰቡ እንዲሳተፍ ከተደረገም በትክክል አይፈጸምም? ላለፉት ዘመናት የተሰሩ ስህተቶችስ ካሉ አሁን ለምን አይታረሙም!! ይህን ማንሳቴ ጎጠኝነት ነዉ ብሎ ዘሎ ከመፈረጅና ነገሩን ከማቅለል ትክለኛ ምላሽ መስጠት የመሰንጠቅ አደጋ እንዳይከሰት ያደርጋል ።

መረጃእንመለከት የጉራጌ ዞን አጠቃላይ በሹመት ደረጃ ያለ አመራር ፑል 66 ነዉ። አስኪ ለ21 መዋቅር እንዴት እንደተከፋፈለ እንመልከት፡-

1. ሶዶደቡብ ሶዶ እና ቡኢ ከተማ አስተዳድር ከ3 ወረዳ 4 አመራር ተሳትፎዋል

2. ከሙህርአክሊል ከአንድ ወረዳ 7 አመራር ተሳትፎዋል

3. አበሽጌከአንድ ወረዳ 6 አመራር ተሳትፎዋል

4. ቀቤና ካንድ ወረዳ 4 አመራር ተሳትፎዋል

5. እነሞርናኤነርእኖር ጉንችሬ ከ3 ወረዳ 9 አመራር ተሳትፎዋል

6. ከመስቃን ምስራቅ መስቃን ቡታጅራ ከ3 ወረዳ በቅርቡ የተጨመረዉን እንሴኖን ሳላካትት) 2 አመራር ተሳትፎዋል

7. ቸሃናእንድብር ከ2 መዋቅር 9 አመራር ተመድቧል

8. ገ/ጉ/ወ ከ1 ወረዳ 4 አመራር ተመድቧል

9. ከጉመርወረዳ (በቅርቡ የተጨመረዉን አረቅጥ ሳላካትት) 3 ታሳትፎዋል

10. ከጌታወረዳ 3 አመራር ተሳትፎዋል

11. እንደጋኝ 3 አማር ተሳትፎዋል እዣ ወረዳ(በቅርቡ የተጨመረዉን አገና ሳላካትት) 4 አመራር ተሳትፎዋል

12. ከማረቆ 3 ተመድቦለታል ለጊዜዉ መዋቅሩ ላይ ባይኖሩም ይህ አሰራር ምን ያህል የተዛባ እንደሆነና በብልጽግና ሁሉም ማህበረሰብ ተመጣጣኝ ዉክልና ያገኛል ከተባለ 21ዱም መዋቅር አዲስ የመጡትን ትቼ እኩል 3 አመራር ይመደብለታል ወይም በህዝብ ቁጡሩ ልክ ተመጣጥኖ መሳተፍ አለበት እላለሁ። ይህ ትችቴ በመረጃ ነዉ ስም መጥራት አያስፈልገኝም። የፖለቲካ ተሳትፎ ኢ- ፍትሃዊነት መኖር በዚህ ዘመን በቀጥታ የሚሻገረዉ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ተሳፈትፎ ኢፍትሃዊነት ነዉና በቀጣይ ያንን እዳስሳለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

“አቅላይ እንሁን ለሚነሱ ጥያቄ መልስ እንስጥ”

ታዬ ተስፋዬ ስሜ


55 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean