የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
እሾክ ከስጋ ገብቶ (በሚፍታ ሸምሱ)

የወጋኝ እሾክ ፣ እንቢ አለ በመርፌ ፤
አልሆነም አምጡልኝ ፣ ልሞክር በወስፌ፤
ገላእሾክ ይዞ ፣ እንዴት ይረጋጋ ፤
ላውጣው እንጂ በግድ ፣ ከገባ ከሥጋ ።
ማንከሴም ቢሆን ለቀናት ብቻ ነው ፤
ከዘራ መያዙም ፣ ከቶ ምን ሊጎዳኝ ፣ ነገዬን ካሳመረው ። "
አቤት መመሰጥ ፣ ግጥሙ የኔ አይደለም
ባይሆን ለገጣሚው ፣ ይህ መልዕክቴ ይድረሰው ፤
ስጋህ ቢፈወስም ፣ ልብ ካልታከመ ፣ መች ይድናል ሰው ።
አሾሁን አውጥተህ ፣ ስጋህ ቢፈወስም ፤
ከማያላውስ ህመም ፣ ከጥላቻ አልዳነም ።
እሾሁ ሲወጋህ ፣ የቋጠርክባቸው ቂም ፤
የጎን ውጋት ሆኖ ፣ ከልብህ አልወጣም ።
ይቅር ተባብለህ ፣ የወጋህን እሾህ ፣ የወጋህ ካልነቀለው ፤
የልብ ህጥላቻ ፣ መልሶ ያስወጋሃል ፣ ትላንት የወጋህን ሰው።
ስለዚህ ወንድሜ ፣ ዜሮ ድምር አይሁን ፣ ስጋህም ልብህም፤
ይቅር በመባባል ፣ በምክክር ካልሆነ፣ በጭራሽ አይድንም።