top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር (OBSESSIVE COMPULSIVE DISORDER) – ዶ/ር ዮናስ ላቀው


OBSESSIVE COMPULSIVE DISORDER)

ሁላችንም የሆነ ቀን “በሩን ዘግቼዋለሁ ወይስ?” ብለን ተመልሰን ቼክ አድርገን “ስቶቩን አጥፍቼዋለሁ?” ብለን አስበን ወይም ጥሩ ያልሆነ ሀሳብ ድንገት አእምሯችን ላይ ብቅ ብሎብን እናውቃለን፡፡ ከዛ ረስተነው ሌላ ነገር መስራት እንቀጥላለን፡፡ ኦሲዲ ያለባቸው ሰዎች ግን ሀሳቡ እየተመላለሰ ስለሚነዘንዛቸው ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል፡፡

ኦብሰሽን ተደጋጋሚ የሆነ የማይፈለግ እና የሚያስጨንቅ ሀሳብ ወይም ምስል ሲሆን ኮምፐልሽን ደግሞ ጭንቀቱን ለመቀነስ የሚደረጉ ድርጊቶች ናቸው፡፡ የንጽህና ሀሳብ የሚመላለስ ከሆነ ኮምፐልሽኑ ደጋግሞ መታጠብ ሲሆን ስቶቩን አጥፍቼዋለሁ? ወይም በሩን ዘግቼዋለሁ? የሚል ጥርጣሬ ከሆነ ኮምፐልሽኑ ተመላልሶ ማረጋገጥ ይሆናል፡፡

ኦሲዲ ያለባቸው ሰዎች ብቸኝነትና ጭንቀት የሚሰማቸው ሲሆኑ ሀሳባቸውና ድርጊታቸው ምክኒያታዊ እንዳልሆነ ስለሚረዱ ‘ራሴን ልስት ነው?’ ብለው ይጨነቃሉ፡፡ ለሰው በግልጽ ለመናገር ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ በዚህ ምክኒያት አብዛኞቹ ወደ ህክምና የሚመጡት ከአመታት በኃላ ነው፡፡ ሀሳቦቹ በራሳቸው ጊዜ የሚመጡ ሲሆን የግለሰቡን አእምሮ ይይዙታል፡፡

ሰዎች ታዲያ “ሀሳቦቹን ችላ በላቸው” ብለው ምክር ይሰጣሉ፡፡ መቆጣጠር የማይችሉትን ነገር ችላ በለው ሲባል የሚፈጥረውን ስሜት መገመት ይቻላል፡፡ ሀሳቡን ተከትሎ የሚመጣውን ጭንቀት ለመቀነስ ልማድ የሆኑ ተደጋጋሚ ድርጊቶችን ያከናውናሉ፡፡

የኦሲዲ ምልክቶችን ለመቀነስ የሚረዱ ውጤታማ መድሀኒቶች አሉ፡፡ እንዲሁም የንግግር ህክምና በተጨማሪነት ሲሰጥ ውጤታማነቱ የተሻለ ይሆናል፡፡


መልካም ጊዜ!


ምንጭ - getutemesgen24.com

24 views0 comments
bottom of page