• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ከሚያጋጥመን የፀፀት ስሜት ለመውጣት የሚያግዙን ምክሮችጥፋትዎን አምነው ይቀበሉ – በእርግተኛነት በእርስዎ ምክንያት የተደረገውን መልካም ያልሆነ ነገር ጭንቅላትዎን ሙሉ በሙሉ አሳምነው ይቀበሉ። ጥፋቱ የርስዎ እንዳልሆነ አራስዎን ለመደለል አይሞክሩ።

2. ይቅርታ ይጠይቁ – አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በእርስዎ ጥፋት ምክንያት የተጎዳ ሌላ ወገን ካለ በነገሩ እንዳዘኑ ገልፀው ከልብ ይቅርታ ይጠይቁ።

3. እራስዎን ከፀፀቱ ለማላቀቅ ይወስኑ – ጥፋትዎን አምነው ከተቀበሉ እና የበደሉትን ሰው ይቅርታ ከጠየቁ በሁዋላ፣ ከሚያሰቃይዎ የፀፀት ስሜት ነፃ መውጣት እንደሚገባዎት እራስዎን ማሳመን ይገባል።

በዚህ ዓለም ላይ አውቆም ሆነ ሳያውቅ የማያጠፋ የለምና የእርስዎም ክስተት ከብዙዎቹ አንዱ እንደሆነ አምነው እራስዎን ነፃ ያውጡ። በነገሩ ውስጥ ከእርስዎ ቁጥጥር በላይ የሆነ ነገር ከነበረ፣ ይህንኑ ለራስዎ ተገንዝበው ወደሚቀጥለው የሕይወት ምእራፍ ለመሸጋገር ሳያመነቱ ይወስኑ።

4. ከክስተቱ ትምህርት ይወሰዱ – ያለፈው አልፏል እና በነገሩ እየቀዘሙ ከመሰቃየት፣ የበለጠ ለወደፊት ሕይወትዎ ጠቃሚ የሚሆነው ከክስጠቱ ትምህርት ወስዶ ተመሳሳይ ስህተት ውስጥ እንዳይገቡ መማር ነው።

ልምድዎትንም ተጠቅመው ሌሎችን ለመርዳት እና ለመምከር ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

5. በክስተቱ በማለፍዎ እራስዎን በምስጋና ይሙሉ – ውስጥዎን ክፍት አርገው ከተቀበሉት ያለፉበት ልምድ ሁሉ የእራሱ የሆነ ልምድ እና ግንዛቤን አስጨብጦዎት ያለፈ ክስተት ነው።

ስለሆነም በክስተቱ በማለፍዎ ስላገኙት አንድ ከፍ ያለ የሕይወት ልምድ ውስጥዎን በምስጋና ለመሙላት ይሞክሩ።

ይህ ያገኙት ልምድ ከእራስዎ አልፎ ሌሎችን የማዳን ተግባር ሊፈፅም የሚችል ኃይልም እንደሚነሮው እራስዎን ያስታውሱ።

ምንጭ - ሰዋሰው

35 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean