top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ከሶሎሞናውያን እስከ ብልፅግና (ይፋዊ መንግስት vs ህቡዕ መንግስት) - ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሳኢትዮጵያ በአንድ መንግሥት ትናንትም ዛሬም አልተመራችም። ቅድመ 1967 ሶሎሞናዊው መንግሥት ይፋዊው መንግሥት ሲሆን ሁለተኛዋ መንግሥት ደግሞ ሲሶ መንግሥቷ ነበረች።


ድህረ 1967 በኋላ ይፋዊዎቹ መንግሥታት ደርግ፣ ኢህአዴግና ብልፅግና ሲሆኑ ሁለተኛው መንግሥት ግን አንድ ኃይል ነው። ይህ መንግሥት ይፋነቱን በየካቲት 1966 ተካትሞ ህቡዕ የገባ ነው። ስለዚህ አገራችን በይፋዊ መንግሥትና በህቡእ መንግሥት (Deep State) ትመራለች።


መሰረተ ባህሪያቸው


ድህረ 1967 የተከሰቱት ይፋዊ መንግሥታት በመርህ ደረጃ በዴሞክራሲና በእኩልነት የሚያምኑ በመሆናቸው የአንድን ብሄርና አባላቱን ወይም ኃይማኖትና ምእምኑን ለይተው በፓርቲያቸው ህገ ደንብ፣ በፖሊሲዎቻቸውና በአመራራቸው ግሃዳዊ የሆነ ቀጥተኛ አድሏዊነት፣ ጨቋኝነት፣ ገፊነት፣ ጠላትነት ያለው አካሄድ አይሄዱም።


ግና እነዚህ መንግስታቶች የቆሙት በፖለቲካ በመሆኑ መንግሥታቱ የአገሪቱን ልዩ ልዩ ኃይሎች የአደረጃጀት (የሰው ኃይል)፣ ተቋማት (institutional power)፣ የመደራደር አቅም (bargaining power)፣ የሎቢ አቅም፣ የፋይናንስና የፖለቲካ ተፅዕኖ በማጥናት የተሻለውና ጠንካራ ከሆነው ኃይል ጋር መንግሥታቱ የይፋና የህቡእ ድርድር ያደርጋሉ።


በፖለቲካቁማርም ቀጥተኛ ባልሆነና በተጠና መልኩ የህቡእ መንግሥትነትን አቅም ከያዘው ኃይል ጋር ይደራደራሉ፣ ይሰጣሉ ይቀበላሉ፣ የህቡዕ መንግስቱን አጀንዳ እንደየ ሁኔታው በይፋና በቀጥታ አሊያም በስውርና በተዘዋዋሪ ተቀብለው ይፈፅማሉ ያስፈፅማሉ።


ይፋዊውመንግስት ሲጠነክር የሉዓላዊነት ወሰኑን እያሰፋና እያጠናከረ ይሄዳል። በመጨረሻም አሲምፕቶታዊ ራስ ቻሌ ይሆናል። በፍፁም ከህቡእ መንግሥቱ ተፅዕኖ ሙሉ በሙሉ ባይድንም በእግሩ ቆሞ ከአጀንዳ ተሸካሚነት ይላቀቃል።


እንደኢትዮጵያ ባሉ የዴሞክራሲ መንግስት እድገት ቀርፋፋ በሆነባቸው አገራት ቸርችና ስቴት ትናንት 1967 ተፋትተው ሳለ ይፋዊው መንግሥት በአጭር ጊዜ ከህቡእ መንግሥቱ ተፅዕኖ ይላቀቃል ብሎ ማሰብ ፈፅሞ እቡይነት ነው።


ህቡእ መንግሥት የምንለው የቱን ነው?


በኢትዮጵያህቡእ መንግሥት አቅም ሊኖረው የሚችለው በታሪክ የይፋዊ መንግሥትነት ተሞክሮ ያለው፣ በታሪክ ይፋዊ የገዥነት ስነልቦናዊና ቁሳዊ ጥቅሞቹን በአንድ የታሪክ አጋጣሚ በማጣቱ ቁጭት ያለው፣ በሪሶርስ ሞቢላይዜሽኑ ፍፁም ውጤታማ የሆነው፣ በአደረጃጀቱ የደረጀ ተሞክሮ ያለው፣ በተቋማቱ ጥርስ ያለው፣ የፖለቲካ መቆመሪያ ሜዳውን ማስፋትና መለዋወጥ የሚችል የፖለቲካ ተሞክሮና ክህሎቱ ያየለው ነው።


መገለጫቸውምንድን ነው?


የአገሪቱስርዓተ መንግሥት የተቋቋመባቸውን እሴቶች ከእሴቶቻቸው የገነቡ፣ ሀገሪቱ የተጠረነፈችበትን አቁማዳ ሆነው የአገሪቱን መልክ በመልካቸው የሳሉ በመሆናቸው የሃሳዊው ኢትዮጵያዊነት ፊት አውራሪ ናቸው።


ዳይናሚዝምመገለጫቸው ነው። እንደየ አስፈላጊነቱ ኃይማኖተኛ ይሆናሉ፣ ብሄርተኛ ይሆናሉ አሃዳዊ ይሆናሉ። ሶስቱን አጣምረው ወይም በተናጠል ወቅቱን እየገመገሙ ይጠቀሙባቸዋል‼


በታሪክአጋጣሚ በማህበራዊ አግልግሎት መስጫ አውታሮች፣ በፖለቲካ ንቃትና በፖለቲካው መስክ፣ በአመራርነት የቀዳሚነትና የብዙሃንነት እድልን የተጎናፀፉ በመሆናቸው በህቡእ ይፋዊውን መንግስት ከውስጥም ከውጭም የማበስበስና ሽባ የማድረግ ከፍተኛ እድል አላቸው።


በሚዲያ፣በተቋማት፣ በአደረጃጀት፣ በካፒታል አቅም፣ በቴክኖሎጅ ብልጫና ክህሎት፣ በሴራ ፖለቲካ ተገዳዳሪነት የይፋዊውን መንግሥት ቢሮክራሲና ሪሶርስ በመጠቀም፣ አደረጃጀቱን በመጠቀም፣ ፖሊሲውን ኮራፕት በማድረግ፣ ህግ አውጪውን፣ ህግ ተርጓሚውንና ህግ አስፈፃሚውን ክፈል በማንቀዝ ለፈለጉት ዓላማ ማዋል ይቻላቸዋል። ወይም መንግሥት ላይ ከውጭ ተፅዕኖ በመፍጠር ተልእኮ መስጠትም ሆነ አጀንዳ ማሸከም ይቻላቸዋል።


በብዛትየት አሉ? ብነግራችሁ ንቀት ይሆናልና እንለፈው።


ታዲያምን ይሻላል?

ይፋዊውመንግሥት የኃይል ሚዛን ካልኩሌሽንና ለአሲድ ቤዝ የማዘገጀት አቅሙን ማደርጀት ይኖርበታል።

የህቡእመንግሥቱ የውርስ ጠላቶች የመደራደር አቅማቸውን በሰው ኃይል ልማት፣ በተቋማት ልማት፣ በኢኮኖሚ ልማትና ሪሶርስ ሞቢላይዜሽን፣ በቴክኖሎጂና ፖለቲካ ክህሎት እንዲሁም በሚዲያ ልማት በፍጥነት የማሳደግና የመልማት ሩጫ ውስጥ መግባት አለባቸው።


የህቡዕመንግሥቱ ታርጌት ጠላቶች ከርካሽ፣ ከተራ፣ ከፋይዳ ቢስ፣ ከስሜታዊነት ሰማእትነት አባዜ ተላቀው የውስጥ ስራቸውን መከወን፣ ማሳለጥና ማጧጧፍ ይኖርባቸዋል። ከይፋዊው መንግሥት ጋር በአነስተኛ ህመሞች ሳቢያ ግጭት ውስጥ በመግባት ዳዴ ሳይሉ የሚከስሙበትን መንገድ መተው ይኖርባቸዋል።


አላስፈላጊየእርስ በእርስ መተጋገልን በማስወገድ (watch out! Synergy effect matters) ፣ ስትራቴጂክአጋርነትን ከይፋዊው መንግሥት ጋርም ሆነ ከማንኛውም አካል ጋር የአዋጭነት (cost benefit Analysis) ናየተተግባሪነት (feasibility) ሁኔታውበተጠና መልኩ በመፍጠር ጠላትን መቀነስና ወዳጅን የማብዛት ስራ መስራት ያስፈልጋል።


ይፋዊውመንግሥት ከህቡእ መንግሥቱ ተፅዕኖ እንዲወጠና እንዲድን በፍጥነት አማራጭ ወይም መተማመኛ የሆነ የኃይል ሚዛንን መጠበቅ የሚችል አቅም መገንባት ያስፈልጋል። ያኔ ይፋዊው መንግሥት በሁለት እጁ የተሞረከዘውንና ከትከሻው ላይ ሆነው የመሪ ፔዳል የሆነውን ህቡእ መንግስት በሂደት እያራገፈ እጁንም እያነሳ አስተማማኝ አማራጭ የሆነውን ኃይል ማመንና መመርኮዝ ይጀምራል‼


የውስጥ ስራህን ሳትጀመርና ሳታገባድድ የአምስት ብር አቅም ይዘህ የሺ ብር አትጩህ! ጠላትህ የመቶ ሺ ብር መደምሰሻ ያዘጋጅልሃልና‼ ይፋዊውን መንግሥት እንደ ቢንቢ እየተናደፍክ አድምተህ ላታደማው ከእንግድነት ከቤትህ አታባረው አታስኮርፈው‼

42 views0 comments

コメント


bottom of page