top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“ከአይን የራቀ ከልብም ይርቃል” (ኢዱና አህመድ)


“ከአይን የራቀ ከልብም ይርቃል” (ኢዱና አህመድ)

የጉራጌ ሁለንተናዊው ሁኔታ ሲቃኝ ቤተ ጉራጌዎች የጋራ የሆኑ እሴቶች እንደሌሉን ታሪክና ለአመታት ያነገብናቸው ጉዳዮች እንዲሁም የተጓዝንባቸው መንገዶች ገላጮች ናቸው። እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ብሔረሰብ በተወሰነ መልኩ ችግሮች ቢኖሩበት እንጂ እንደ ቤተ ጉራጌዎች ምስቅልቅሉ የወጣ አይደለም። በዚያች የበሬ ግንባር በምታህለው የጉራጌ ዞን ውስጥ የሚኖሩት እኒሁ ቤተ ጉራጌዎች በታሪክ የጋራ የሆነ ጉዳይ ኖሯቸው አያውቅም። ለምሳሌ ያህል የሽምግልና ስርዓቱን ብንቃኝ ሶዶ፣ መስቃን እና ሰባት ቤተ ጉራጌ የየራሳቸው የሆነ የሽምግልና የዳኝነት ሰርዓት አላቸው። እኒሁ ሶስቱ ቤተ ጉራጌዎች በተለያየ ጊዜ ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንደ መጡ ታሪክ ይናገራል። ጉዳዩ ለምን የተለያየ የሽምግልና የዳኝነት ስርዓት ኖራቸው ሳይሆን ለምን የጋራ ወይም የተጣመረ የላቸውም የሚለው ነው። በእርግጥ በታሪክ የአመጣጣቸው ሁኔታ እንደተለያየ ሁሉ በቋንቋም በተወሰነ መልኩ ልዩነት አላቸው። የቋንቋ መለያየቱ ለመግባባት ችግር እስካልፈጠረባቸው ድረስ የጋራ የሆነ እሴት ለመገንባት ችግር ይኖራል ብዬ አላስብም። የጋራ የሆነ ማንነት፣ የጋራ የሆነ ባህል፣ የጋራ የሆነ የሚያስተሳስረን አመታዊ ቀን እንዲሁም የሚያቀራርበን ጉዳይ ያስፈልጋናል።

“ከአይን የራቀ ከልብም ይርቃል” አይነት እንዳይሆን የዘቢዳር ተራራን ጥሰን ወደ ላይ መውጣት አለብን እነርሱም እኛ ለማግኘት ቁልቁል መውረድ አለባቸው። በተጨማሪም ከሁላችንም ዘንድ የሚገኘውን አጉል እልህ በማስወገድ ቁርጠኛ በሆነ አቋም መልካም የሆነውን ዘር መዝራት አለብን። የመልካም ዘር ውጤቱ መልካም ነውና።


ኢዱና አህመድ ኡስማን

26 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page