top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ (በአሸናፊ ተስፋዬ)


ጌታቸው ግዛው ይባላል የቡታጅራ አማተር የጋዜጠኞች ማህበር ከመሰረቱት ግንባር ቀደሙ ሚና ሲጫወት የነበረው ዋነኛው ሰው ብንል ማጋነን አይደለም።


ብዕር በከተማችን እንድታብብ በከተማችን የስነ ጽሑፍ በወጣቱ ሰርጾ እንዲገባ ከሚያደርጋቸው ጥረቶች መካከል አውዳመትን ተመርኩዞ እንደዛሬ በከተማችን ህንጻዎች ባልተስፋፉበት ግዜ የከተማው ከፍታ ቦታዎች ላይ በመሆን በድምጽ ማጉያ ለከተማው እዝብ እንኳን አደረሳችሁ መልክቶችን በሙዚቃ እና በስነጽሑፍ በማጀብ መልክት ያስተላልፍ ነበር ።


በተጨማሪ ጌታቸው በዚህ ማህበር እና በቡታጅራ በአገሩ አይደራደርም ልክ እንደ እናቱ ልጅ ነው የሚወዳቸው ። ለከተማዋ የኪነ ጥበብ ዋጋ ከከፈሉ ግንባር ቀደሞች ሰወች መካከል ዋነኛው ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም።


እንደ ዛሬው ታዋቂ ደራሲ እና አርቲስቶች ቡታጅራን እንደ ቤታቸው ከመቁጠራቸው በፊት ከተማዋን የጥበብ ሰወች እንዲጎበኟት በርካታ የአገራችን ደራሲዎች እንዲጎበኟት እና ስለከተማዋ እንዲያወሩ በራሱ እና በከተማዋ ደጋግ ባላሃብቶች እንደነ አቶ አወል ሁሴን ድጋፍ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል።


ለምሳሌ ደራሲ ጋሽ ስብሃት አርቲስት ጫንያለው ወ/ጊዮርጊስ አርቲስት ታምራት ደስታ ብቻ ምን አለፋችሁ ቡታጅራ ተብሎ እንዲጠራለት የማይቆፍረው ጉድጓድ አልነበረም።


ከሁሉ... ከሁሉ ሁሌም... ከአይምሮዬ የማይጠፉው እንደ ዛሬ ሬድዮ እና ጋዜጣ ባልበዛበት ቅዳሜ ለወጣቶች እና ምሽት መዝናኛ ፕሮግራም ጌታቸው ግዛው ከቡታጅራ የሚል አስተያየት ሳንሰማ አናልፍም ነበር።


ሌላው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከልጆች አምድ እስከ ከተማው ላይ ሊታረሙ የሚገቡ ጉዳዮችን በራሱ ስም እና በብህር ስሙ ሲከትብ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው።


ጌች ለከተማዋ የጥበብ አድማስ ጭላጭል ስለከፈትክ እናመሰግንሃለን!


የትግህስትን ጥቁር ድንጋይ የፈነቀለ ጌች ብቻ ነው ይለኝ ነበር። ብስጭት ሲል ደግሞ "አምና ከበሬዎች ዘንድሮ ከጥጆች" ይል ነበር።


ጌታቸው ግዛው የሚያውቁት የከተማችን ተወላጆች ስለሱ ሲነሳ ብዙ አስቂኝ እና እዝናኝ ገጠመኞች አሉት ይሉታል ታዲያ እርሶሆስ ከሚያስታውሱት ነገሮች ቢያካፍሉን.....


በአሸናፊ ተስፋዬ

26 views0 comments

Comments


bottom of page