top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የመስቃንኛ፣ አማርኛና እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ምረቃ (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

Updated: Jul 16, 2022ለመልካም ጅማሮ ለመልካም ስራቹ ምስጋናና አድናቆት እና ክብር ለአዘጋጁ ሃይረዲን አወልና ለአሳታሚዎችና ሀገር ተረካቢዎች አርዴ ጊየዝ እያልኩኝ የጉራጊኛ ቋንቋ ጥናትና ከጥናቱ ዉጤቱ በስተጀርባ ስላሉት ዳተኞች አንድ ልበል፡-

በሃገራችን እዉቅና ከተሰጣቸዉ 87 ብሄረሰቦች ዉስጥ 54 ብሄረሰቦች በክልላችን 35 የሚጠጉ ብሄረሰቦች ቋንቋቸዉን የትምህርት የሚድያ እና የስነጽኁፍ አድርገዉ ይጠቀማሉ። በተነጻጻሪዉ ሰፊዉ የጉራጊኛ ቋንቋ እንደማንኛዉም ብሄረሰቦች የመማሪያ፣ የስራና የሚድያ ቋንቋ ባለመሆኑ እየጠፈና እየተዳከመ መሆኑን በማጤን ያሉትን ሰባት የሚጠጉ ዘዬዎች በማጥናት ሁሉንም የጉራጌ ጎሳዎች በተሻለ ሚያግባባዉን ዘዬ በመምረጥና የጎደለዉን በማልማትና በመጨመር አንድ ዘዬ በመዉሰድ ለመጠቀም ባለፉት አመታት የወልቂጤ ዩንቭርሲቲና የጉራጌ ዞን አስተዳድር ከፍተኛ የሆነ የበጀት የዕዉቀት የጊዜ መስዋዕትነት ተከፍሎበት በሳይንሳዊ ዘዴ ተጠንቶ ዉጤቱም ለተለያዩ የብሄረሰቡ አካላት በተለያዩ መድረኮች ቀርቦ ተተችቶ ወደ ተግባር ለመግባት ተወስኖ ነበር። በአጋጣሚ ሳይንሳዊ ጥናቱ ካሉት ዘዬዎች የተሻለ ሁሉንም ጉራጌዎች ያግባባል ብሎ ያመጣዉ የመስቃንኛ ዘዬ እንደሆነ በተለያዩ መድረኮች በተለያዩ የማህበረሰቡ አካላት በተገኙበት የጥናት ዉጤቱ ይፋ ተደርጎ በጥቂት ጊዜያት ወደ ተግባር እንደሚገባ በዋና አስተዳድሩ ተገልጾ ነበር። ይሁን እንጂ በተለያዩ መድረኮች ግን የታየዉ የትምክት አይሉት የብልጣብልጥ ሃሳቦች በሙህሩም በባለሃብቱም በታዋቂ ግለሰቦችም ይንጸባረቅ ነበር የቀረበዉ ሳይንሳዊ ጥናት ዘዴ ልክ እንደ ጉራጌ ጥናት ቀደም ብሎ የሲዳማ የወላይታ የጋሞ ብሄር ብሄረሰቦችም ዉስጥ ተመሳሳይ የዘዬ ችግር የነበረባቸዉና በተመሳሳይ ሙህራንና ሳይንሳዊ ጥናት ዘዴ በተገኘ ዉጤት መሰረት ተቀብለዉ በማስፈጸማቸዉ ዛሬ አንድ ሆነዉ ይታያሉ እኛጋ ሲመጣ ግን ሌሎች ያደነቁትና የተቀበሉትን የጉራጌ ተወላጅ የሆነዉ የቋንቋ ሳይንቲስቱን ጭምር በማጥላላትና በመካድ ለቋንቋዉ እድገት ከመጨነቅ ዉጤቱን ላለመቀበል አንዴት የእገሌ ዘዬ አልሆነም ብዙ የጉራጌ ዘፈን የተዘፈነበት ብዙ የጉራጌ መጽሃፍት የተጻፈበት መጻህፍ ቅዱስ የተተረጎመበት ዘዬ እያለ የሚል በተደጋጋሚ እንሰማለን፣ ቀጥሎም አይ የሰሜን ጉራጌው ለብቻዉ መታየት አለበት የሚል ደግሞ ቀጥሎ ይደመጣል፣ ሌላኛዉ ደግሞ ይነሳና ለመሆኑ ሌሎቹ ዘዬዎችስ ይጥፉ ነዉ ምትሉት ይላል። በእኔ አመለካከት ወደድንም ጠላንም አንድነትን ከፈለግንና በአንድ ዘዬ ቀጣዩ ትዉልድ እንዲግባባ ከፈለግን ሁሉም የራሱን ዘዬ በማህበረሰብ ዉስጥ እየተጠቀመ አንድ የተመረጠዉን ዘዬ ደግሞ በትምህርት ዉስጥ አስገብቶ አዲሱ ትዉልድ እንዲማረዉ ማድረግ ሞኝነት ሳይሆን ብልህነት ነበር። የሃረር፣ የባሌ፣ የሸዋ፣ የአሩሲ እና የወለጋ የኦሮምኛ ዘዬዎችም የተለያዩ ዘዬዎች ነበሩዋቸዉ ልዩነታቸዉን በጥናት በመለየትና የተመረጠዉን ዘዬ በቁቤ ትዉልድ አሳድገው ነዉ ዛሬ ከጫፍ አስከ ጫፍ ያሉ የኦሮሞ ልጆች እኩል የሚሰሙትና የሚናገሩት ቋንቋ ሆኗል ። የእኛው ግን የፉክክር ቤት አይነት ሆኖ ያለመስዋዕትነት "አንድነት ለማምጣት ይቻላል" ብሎ እራሱን የሚሸዉድ ቀላል የማይባል የጉራጌ ትምክህተኛ ካድሬ በመፈጠሩ ምክንያት ነዉ። ሁሉም አካባቢ ለጥናቱ ተገዢ አልሆን ብሎ በራሱ ዘዬ ለማስተማር ወደ ቀደመዉ ልዩነት እንዲመለስ የተደረገዉ። በመጨረሻም ጉራጌን በዝቶ እንዲያንስ ገዝፎ እንዲኮስስ ያደረገውን መናናቁን ትተን ያለንበት ጊዜ መደመርና ሰጥቶ በመቀበል ነዉና ለትግበራው ሀላፊነት ብንወስድ እላለሁኝ።

አመሰግናለሁ

ታዬ ተስፋዬ ስሜ

134 views0 comments

Comments


bottom of page