top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"የመስቃን እና የማረቆ የእርቅና የሰላም ውይይት በሃዋሳ"

Updated: Jul 4, 2020


የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች መንግሰት ምክትል ርዕሰ መስዳደር አቶ እርስቱ ይርዳው

በሃዋሳ የሰላምና የእርቅ ውይይት እየተረደገ ይገኛል። ከቀናት በፊት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች መንግሰት ምክትል ርዕሰ መስዳደር በአቶ እርስቱ ይርዳው መሪነት ከወረዳዎቹ ዋና አመራሮች ጋር እየተደረገ ያለው ውይይት ፍሬያማ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተሰማ።

የአርቅና የሰላም ውይይቱን የተካፈሉት የመስቃን ወረዳ የስራ ሃላፊዎች ወረራና ጥቃት የተፈጸመብን በእኛው ላይ ሆኖ ሳለ የመስቃን ተወላጆች እና በተለያየ መንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩ የቤተ መስቃን አመራሮች እና የስራ ሃለፊዎች ለእስር መዳረጋቸው የፍትህ መዛባትን ያሳያል በሚል ለአቶ እርስቱ ይርዳው ያቀረቡ ሲሆን የማረቆ ወረዳ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው ሰላሙ እና እርቁን የምንፈለገው ቢሆንም ፌደራል ውስጥ የሚሰሩ የማረቆ ተወላጆች ከውይይቱ ውስጥ ካልተካተቱ የማረቆን ህዝብ ሊያሳምጽቡን ይችላሉ ብለው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ከግለሰቦቹ አንዱ ከመንግስት ጥሪ ተደርጎላቸው የሰላሙን ውይይቱን በመካፈል ላይ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል።

በፌደራል መዋቅር ውስጥ የሰላም እርቁ እንዳይደረግ ተጽእኖ እየፈጠሩ የሚገኙትን ግለሰቦች ማንነታቸውን የምናጣራ ሲሆን የእርቅና የሰላሙን የሂደት ደረጃን ጭምር ለማሳወቅ ጥረት እናደርጋለን።

153 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page