• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"የመስቃን እና የማረቆ የእርቅና የሰላም ውይይት ፍጻሜ በሃዋሳ"


በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች መንግሰት ምክትል ርዕሰ መስዳደር በአቶ እርስቱ ይርዳው መሪነት ከመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች ዋና አመራሮች ጋር እየተደረገ የነበረው ውይይት ፍሬያማ ውጤት ማምጣቱ ተነገረ። አመራሮች ተግባብተው የመብት ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ እንዳለባቸው ተስማምተዋል። የመስቃንና ማረቆ ማህበረሰብ ለዘመናት በጋብቻና በአብሮ የመኖር እሴት ተግባብተው እና ተሳስረው ይኖሩ የነበረ ሲሆን የሰላምና የእርቅ ውይይቱ እስከ ህዝብ ወርዶ ዘላቂ መግባባት የሚፈጠርበት ሁኔታ በወረዳዎቹ የሚሰሩት የሁለቱም ማህበረሰቦች አመራሮች ከፍተኛ የሆነ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ስብሰባው አጽንዎት ሰጥቷል። አመራሮቹ በየደረጃው ማህበረሰቡን እያወያያዩ በሰላምና እርቅ ሂደት ውስጥ የገጠማቸውን ችግር በአስቸኳይ ለክልሉ መንግስት ማሳወቅ እንዳለባቸው አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን አመራሮቹ የተቀመጠውን አቅጣጫ ለመተግበር ከፍተኛ የሆነ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የሰላምና እርቁን ውይይት የተካፈሉት የማረቆ ወረዳ አመራር አካላት የ9 ቀበሌ የይገባኛል ጥያቄን አምርረው አቅርበው የነበረ ቢሆንም በ1994 ዓ/ም ሪፈረንደም ተካሂዶ በነበረበት ወቅት 24 ቀበሌዎች በህዝብ ምርጫ በማረቆ ወረዳ ውስጥ መካለላቸውና የተቀሩት ወይም አሁን አወዛጋቢ የሆኑት ቀበሌዎች በውስጡ ይኖሩ የነበሩት ህዝቦች በፍቃዳቸው በመስቃን ወረዳ እና መዋቅር ስር መካተታቸው በሪፈረንደሙ የተካፈለው ህዝቡ ምስክር ከመሆኑ በተጨማሪ ማስረጃው የሚመለከተው የመንግሰት አካል ዘንድ እንደሚገኝ ለስብስቡ መገለጹን የውስጥ አዋቂ ምንጭ ጠቁመዋል።

እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጭ ከሆነ ሁከት በማስነሳት እንዲሁም ሰላምና እርቁ በአካባቢው እንዳይሰፍን በእኩይ ተግባር የተሰማሩ በመንግስት መዋቅር ስር የሚሰሩ እና የማህበረሰብ አካላት ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።


የሰላም እና የእርቅ ወይይት ከስልጤ፣ ከኦሮሞ፣ ከጉራጌ ማህበረሰቦች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች የተሳተፉበት ግጭቱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ ግዜያት የተደረገ ቢሆንም በታቀደው መልኩ በአካባቢው ላይ ሰላም ካለመስፈኑ ባሻገር በማረቆ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ የቤተ መስቃን ተወላጆች በተጨማሪም በሁለቱ አጎራባች ቦታዎች በሚኖሩ የመስቃን ማህበረሰብ ተወላጆች ላይ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ተፈጽመዋል። የሰላምና እርቅ ውይይቱ በክልል መንግስት ደረጃ የተጀመረ ቢሆንም ተመሳሳይ አድፍጦ የማጥቃቱ እኩይ ተግባር ሊኖር ስለሚችል ህዝቡ እኩይ ተግባር ፈጻሚዎች ለመመከት ከመንግስት ጋር በቅርበት መስራት አለበት ሲሉ

ስማቸው እንደይጠቀስ የፈለጉ በምስራቅ መስቃን ወረዳ የእንሴኖ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ አሳውቀዋል።

171 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean