የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የስሜት ብልሃት... የስኬት መወጣጫ

ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence (EQ)) ሀይላችንን በአንድ አቅጣጫ በማድረግ ትልቅ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው። ዶክተር ትራቪስ ብራድበሪ (Dr. Travis Bradberry) የተባለ ተመራማሪ ባጠናው ጥናት መሰረት በስራ ቦታ ውጤታማ ከሚሆኑ እና ከፍተኛ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ሰዎች ውስጥ ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ከፍተኛ የስሜት ብልህነት የሚስተዋልባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ስሜታዊ ብልህነት ባህሪያችንን የምንቆጣጠርበትን ሁኔታ፣ ማህበራዊ ውስብስብነቶች ውስጥ የምንጓዝበትን መንገድ እንዲሁም ጥሩ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ግለሰባዊ ውሳኔዎቻችን ላይ ተጽኖ ያደርጋል። ስሜታዊ ብልህነት በሁለት ዋና ችሎታዎች ውስጥ በተካተቱ አራት ዋነኛ ክህሎቶች የተሰራ ነው።
እነዚህም
1- ግለሰባዊ ችሎታ፦ ትኩርት የሚያደረገው በአብዛኛው ስለ እኛ ስለግላችን እንጂ እኛ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስላለን ግንኙነት አይደለም። ግለሰባዊ ችሎታ ስሜታችንን ስለመረዳት እና ባህሪያችንን እና ዝንባሌያችንን ስለመምራትና ስለመቆጣጠር ብቃት የሚያትት ነው። ግለሰባዊ ችሎታ ሁለት ክህሎቶችን ያካታል።
እነዚህም
• ራስን መረዳት(Self-Awareness) ፦ ስሜቶቻችንን በትክክል የማወቅ እና ሲክሰቱም ሁኔታዎችን የመረዳት ብቃት ነው።
• ራስን መምራት (Self-Management) ፦ ስሜቶቻችንን በመረዳት እና ራሳችን ለነገሮች ዝግጁ በማድረግ ባህሪያችንን ወደ አወንታዊነት የመምራት ብቃት ነው።
2- ማህበራዊ ችሎታ (Social competence) ፦ ይህ ግንኙነትን ከማስተዳደር ክህሎት የሚመነጭ ሲሆን የሌሎች ሰዎችን ስሜት (mood)፣ በሃሪ እና መነሳሳታቸውን (motives) በማወቅ ለግኑኝነቶች ፈጣን መላሽ የመስጠት እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት የማሻሻል ችሎታ ነው፡ ሁለት ክሀሎቶችን ያቀፈ ነው።
እነዚህም
• ማህበራዊ መረዳት (Social Awareness) ፦ የሌሎች ሰዎችን ስሜት እንዲሁም ምን እየተፈጠረ እንደሆነ የመረዳት ችሎታ ነው።
• ግንኙነትን መምራት (Relationship Management) ፦ ራሳችንን የመረዳትና ሰዎችን የመረዳት አቅማችንን በመጠቀም ግንኙነቶቻችንን በብቃት የመምራት ክህሎት ነው። ለመንደርደሪያ ይሄንን ያህል ካልን በሌላ ጊዜ በዝርዝር እስከምንዳስሳቸው ድረስ መልካም ቀን ይሁንልዎ ብለናል :: ሼር
ምንጭ - ጌጡ ተመስገን/HUFFPOST