top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሶስቱ ቤተሰቦች የዘጠና ዓመት ወግ በመስቃን

Updated: Aug 18, 2022
ከአያት ቅድም አያቶች እንደተሰማው ከሆነ ሼህ ኢሳ አልቃጥባሬ ከምስራቅ ጉራጌ ከ1930ዎቹ(ዓም) ጀምሮ ወደ ምእራብ ጉራጌ የኢስላም አስትምሮትን ለመስቃን ማህብረሰብ ለማድረስ እንደመጡ ይነገራል። የጉራጌ ማህበረሰብ ሰፍሮ ከሚገኝበት አካባቢዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በኢስላም አስተምሮትና ማህበረሰብን በመልካም የመቅረጽ ስራን በከፍተኛ ሁኔታ ተወጥተውት እንደነበር ይነገራል።


የሼህ ኢሳን ህለፈት ተከትሎ ልጃቸው #ሻለቃ_ሱልጣን_ኢሳ ከአባታቸውን የሚስተካከል የኢስላም አስተምሮት አቅም ባይኖራቸውም እንኳን በታችኛው ጉራጌ አካባቢዎች አሊሞችን(አዋቂዎች) በማሰባሰብ የኢስላማዊ አስተምሮቱ እንዲቀጥል አድርገው እንደነበር ህያው የሆኑ ምስክሮች እንደዚሁ ይናገራሉ። እነዚሁ ህያው ምስክሮች የአባታቸውን የሼህ ኢሳን ህልፈት ተከትሎ #መንበሩን የተረከቡት ሻለቃ ሱልጣን ምንም እንኳን የኢስላም አስተምሮቱ እንዲቀጥል ያደረጉት የማስተባበር ስራ ቢኖርም #ሰዋዊ ፍላጎታቸው እና የአኗኗር ዘይቤአቸው የታችኛው ጉራጌ ማህበረሰብን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ገፍተው እንዳስቀየሩት እነዚሁ ህያው ምስክሮች ሳይሸሽጉ ይናገራሉ።


በመቀጠል የሼህ ኢሳ የልጅ ልጅ የሆኑት #አቶ_ፋሪስ_ሱልጣን_ኢሳ አንድም ሊጠቀስ የሚችል ደህና ስራ ካለመስራታቸው ባሻገር ምግባራቸው በሚድያ ሊጠቀስ በማይችል መልኩ እጅግ አሳፋሪ እና የሚያሸማቅቅ እንደነበር ይጠቀሳል።


ቀጣዩ እና አራተኛ ትውልድ ወይም የልጅ ልጅ ልጅ የሆነው #ሰልማን_ፋሪስ_ሱልጣን_ቃጥባሬ ሲሆን ይህ ግለሰብ ስለ አለማዊ ትምህርት እና የኢስላም አስተምሮት ሊጠቀስ ወይም ሊነገርለት የሚችል ምንም እውቀት የለውም። ነገር ግን ዝርያው ከተጠቀሱት ቤተስቦች በመሆኑ ብቻ የሃይማኖት መሪ ካባን በመደረብ እና የማይዳሰስ መንበሩ ተረክቦ የማያቋርጥ ጥሪት ከመስቃን ድሃ ማህበረሰብ እየተበረከተለት ያለ አንዳች የተለየ ገቢ ማስገኛ ስራ ከድሃው በሚሰበሰብ ገንዘብ ብቻ ቤተሰቡ እና እራሱን አንደላቅቆ እየኖረ ይገኛል።


ውድ አንባብያ አራቱን ትውልድ በተመለከተ በጣም በትንሹ እና ለአንባቢ በማይሰለች መልኩ አጥሮ ይቅረብ እንጂ በተለይ የቤተሰቡ ቀደምት የሆኑት ሼህ ኢሳ ለትውልድ ሊነገርላቸው በሚችል መልኩ በርካታ መልካም ስራ ሰርተው እንዳለፉ ይነጋራል።


የተቀሩት ሶስት ትውልዶች ግን እንዳመጣጣታቸው መልካም ያልሆነው ስራቻቸው እየገዘፈና እየገዘፍ መጥቶ አሁን ያለበት እጅግ አስቀያሚ ደረጃ ላይ ደረሷል። ስለ እነርሱ ለአንባቢ ለማስረዳት ወይም ለመጻፍ ቢጣር በርካታ እትም ያላቸው መጽሃፎች ይወጡታል። ምናልባት ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት ነገር ተፈጽሟል ወይ ብልን ልንጠይቅ የሚያስችለን ወይም አንዳንድ ልብወለድ መጽሃፍ ላይ እንደሚነበቡት አስገራሚ እና ሰቅጣጭ ከሆኑ የወንጀል ታሪኮች ጋር አቻ በሚሆን መልኩ በማህብረሰቡ ላይ እና በግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል ፈጽመዋል።


ሌላው... አጠያቂ የሆነው እነዚሁ ቤተስቦች በመስቃን ማህብረሰብ ላይ መንበሩን እየተቀባበሉ እንዴት እስከ አራት ትውልድ አደረሱት? የሚለው እጅግ አጠያቂ ከመሆኑ ባሻገር የቤተሰቦቹ ከምእራብ ጉራጌ ክፍል ወደ ምስራቅ ጉራጌ መፍለስ እና እስከ አራት ትውልድ በሃይማኖት መሪ ስም ማስቀጠላቸው በሃይማኖታዊ ስራ የተጀቦነ ነገር ግን ትልቅ የሆነ የፖለቲካ ተልእኮ እና ሴራ እንደነበራቸው እና እንዳላቸው አዋቂዎች ይናገራሉ።በቀጣይ እላይ ያለውን ርእስ በተመለከተ የሚሰሩ ስራዎች በሰፊው ይኖራሉ። ከአነበቡ በኋላ ለሌላ በማድረስ ግዴታዎን በመወጣት ትውልዱን እንዲያድኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።


ቸር እንሰንብት!

104 views0 comments

Comments


bottom of page