• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ግጥሞች (ክፍል - 22)


202. አሁን ያልኩህ ዘመን ናት የነዚያ ወራት

ወታደር መንግሥቱ የሚሾምበት

አገር ቤት ሹመቱ የሚገባበት

ወንድ ሴት፣ ልጅ አዋቂ ሁር ባርያ፣ እኩል የሚባልበት::

203. በሰማይ ቀበሌ መላኢሞች ሲያወጉ

በአጼ መባል ቀርቶ ይባላል በደርጉ

ያን ጊዜ በዱአ እንዳትዘነጉ

መሬትና ሹመት እንዳትፈልጉ::

204. ያን ጊዜ ይበጃል ክልል የሚሉት

እንዳይገናኙ ከእነኛ ሐዋይት

ከያዘ በስተቀር ትንሽ ወረቀት

ይህንን ነገረኝ በይሩስ የሚሉት

የዒፍሩት ወንድም ነው በአባትም በእናት

ያዝ ጊዜ ይነዳል ውሃም እንደ እሳት

በቅሎም ትወልዳለች መሐንም ከሴት

ሸምበቆም ያፈራል ልጠው ቢያቆሙት::

205. ይህንን ተናግሯል በቁርዓን አያት

ወኢዘል ቢኋሩ ብሎ ሲጅረት

ያን ጊዜ ይበዛል ጦርና ዱለት

ደላንታ ይዋጋል ቦረና መሬት

አላሽም ይዋጋል ኤርትራ እሚሉት

በሸዋ በደሴ የሚያልቀው ፍጥረት

ያን ጊዜ ነበር አላህ የሻለት

ሌት ቀኑን መወትወት ነው በአሕመድ ሶላዋት::

206. ዱአ በቀኝ እጁ አድርጎ መያዝ

ያን ቀን ያድነዋል ከብዙ መዘዝ

ወንድሜ ልንገርህ እንዳትፋዘዝ::

207. ይመጣሉ እነዚያ፣ እነ አይራራ እነጨካኝ፣ ደርጎች የሚሏቸው

ዱአ አድራጊ በቀር የለም የሚችላቸው

እነዚያ ኃይለኞች እነዚያ ጨካኞች

እነዚያ አሽብሮች እነዚያ አንበሶች

በክፉ ያዩትን እነዚያ እርጉሞች

በደግ ለታያቸው እነዚያ ደጎች::

208. ደርጎች አይቀሩም ይመጣሉ፣

ዝመቱ፣ መንገድ ሥሩ፣ መሬትን ክፈሉ እኩል የሚሉ

ሰማዩን በባላ ገድፉት ባይሉ::

209. ደርጎች ኤርትራ ሕዝቦች ጋር ሦስት ጊዜ ዘምቶ

የሰላም ንጉሥ ይመጣል ጥቂት ቀን ሰንብቶ

ስድስት ዓመት ይገዛል ዲኑን እስላም ነግሦ

ደስታ ይሆናል ለሱስማ አብሶ::

210. በፊት የቆሰለ ያን ጊዜ ያሽራል

ድሉ ለኡስማ ያን ጊዜ ይዞራል

የደርጎች ዘመቻ ኤርትራ በኋላ

በስተጀንበር መግቢያ አለ በመቅደላ::

211. ይህ ዘመቻ ነው አለቃው ዘመቻ

የሄደው አይመጣም የቀረውን እንጃ

መቅደላ ያልኩህ የርብን ጉባዔ ነው::

212. አሥራ ሁለት ኮርማ የሚገጥምበት

የጎበዞች ሥፍራ እርብ የሚሏት

የርብን ጦርነት ልንገርህ ጥቂት

ሰው ይታደላል ስንዴና መሬት

ደግሞ ሁለተኛ ብርና ጥይት፣

ሰው ያበዛል ሐሰድና ውሸት

እርስ በርሱ መዟለም ነው ድርቅና ኩራት

ወራቷም ሚያዚያ ናት ቀኗም እሮብ ናት

ሦስት ሰዓት አንስቶ ሰኞ ድረስ ናት

አዋጁን ልንገርህ እንድትጠብቃት

ዱአ እያደረግክ በቀን በሌሊት::

213. መሬት የምትከጅል ደግሞም ልብስ ጉርስ

ገበያ እንገናኝ መቅደላ ድረስ

የጡርንባው ብዛት ሦስት መቶ ይሆናል

መህሉቃቱ ሁሉ አንደዜ ይሰፍራል::

37 views0 comments