top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“የተከበረና ህዝቡን ያከበረ ሽማግሌ ለእዉነት እንጂ ለራሱ ጥቅም ብሎ አያሸማግልም” (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)


በመጀመሪያላለፉት ሶስት አመታት በነበረዉ ግጭት በርካታ የመንግስት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ጭምር የተጎዱበት የመስቃንና የማረቆ ወረዳዎች አካባቢ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የትምህርት ቤት ግንባታ ድጋፍ ከማንኛዉም አካል ማግኘት እያለበት ለዞኑ በድጋፍ መልክ የመጣዉን ሁለት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማለትም በቀዳማዊት እመቤት እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች አለ እፍረት ነጥቆ ለራስ አካባቢ መዉሰድ ኢፍትሃዊነት ብቻ ሳይሆን ኢ-ሰብኣዊነት ነዉ:: በርግጥ ዛሬ ዛሬ በሃገሪቱ ያለ ከፍተኛ ካድሬ በሙሉ ያለማንም ከልካይ የመንግስት በጀት የሚፈስባቸዉን ልማቶች እየነጠቀ የኔ ለሚላቸዉ ማህበረሰቦች እያቀረበ መሆኑ የብልጽግና ጉዞ ካሰበበት ሳይደረስ እየተጠለፈ መሆኑ ማሳያ ነዉ::


ከዚህ ሃሳቤ ስወጣ በዚህ ሳምንት ከሰማሁትና ከገረሙኝ ጉዳዮች ስጀምር የሚከተለዉን ለማለት እገደዳለሁ::


"ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገላል" እንዲሉ...


አንዳንዶቹ የሚደረገው ሴራ ገብቷቹ አንዳንዶቹ ሳይገባችሁ እንደሆነ እረዳለሁ:: የተወሰኑት 2 እና 3 ማትሞሉ የዞኑ መንግሰት ሽማግሌ አድርጎ አስቀምጦናል ብላችሁ የቀጠናዉ ጉዳይ ገዳይና ገዢ ለመሆን የምትኳትኑትና ሚስጥራዊ ግንኙነትም ከሴረኞች ጋር እያደረጋችሁ ህዝባችንን ለማወክ እንደምትሰሩ እናዉቃለን:: ቢያንስ በእድሜ ትልቅ ስለሆናችሁ እናከብራችኋለን ግን ደግሞ በትግላችን ዉስጥ ገብታችሁ ለማደናቀፍ እንዳትሞክሩ እንጠይቃለን:: እኔ ለማኝኛዉም ህገ ወጥ ሽምግልናና ድለላ ጆሮ እንደለሌለኝ ደግሜ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።


እኛ የሚያበረታን እንጂ የሚያደክመን ሌላ የመንደር ጨቋኝ አንሻም ስለዚህ የላኩዋቹን የክልልና የዞን ባለስልጣናት አጀንዳዉ የግለሰብ ሳይሆን የህዝብ ስለሆነ ጥያቄዉን ለፌድራል መንግስት ባለስልጣናት በፉገራ መልኩ ሳይሆን ጥቄዉ የህልዉናና የሞት ሽረት ጉዳይ አድርጋችሁ አስረዱና ጥያቄዉን በአፋጣኝ እንዲመለሱ አድርጉ እንጂ ህዝቡን በመሸንገልና በመናቅ የሚደረግ ጉዞ ያበቃ ይመስለኛል። እኔ በበኩሌ ባለፉት ጊዜ በአካባቢያችን እየተፈጠሩት ካሉት ጥቂት ሽማግሌ መሳይ የፖለቲካ ነጋዴዎች እና ባለሃብቶች ጋር ጉድኝትና ምክክር ኖሮኝም አያዉቅም። እነሱም በድፍረት አጠገቤ ቀርበዉ ወይም ጠርተዉ ችግሬን ሃሳቤና አላማዬ አይጠይቁኝም ምክንያቱም መንገዳችንና አላማችን ስለሚለያይ!! ትግሌና ሃሳቤ ለጭቁኖችና ለተበደሉ ብዙሃኖች የቀጠናዉ ህዝቦች በተለይም ወጣቶች እንጂ ለነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ምቹ መንገድ መጥረግ አይደለም። ዛሬ እነሱ ስለተመቻቸዉ ለልጅ ልጆቻቸዉ የሚሆን ሃብትና ንብረት ስለያዙ ብቻ ትግላችንን ከራሳቸዉ ጥቅም አንጻር በመመዘን በቀጠናችን ጉዳይ ወሳኙ ሰፊዉ የአካባቢዉ ህዝብና የአካባቢዉ ወጣቶች ሳይሆኑ እነሱ እንደሆኑ ይገምታሉ። ህዝቡን እንደፈለጉ ሚነዱት አድርገዉ በመሳል ከዞን ባለስልጣናት ጋር በሚስጥር በመወያት የከተማውን ህዝባዊ አመራሮች ለማስነሳት የሚሞክሩ ናቸው።


ሰፊዉ የከተማና የገጠር ህዝብ በትግል ማነስ ምክንያት ዳግም ለድህነትንና ስራ አጥነትን ለማዉረስ ከመንግስት ባንወጣ በሚል ሽፋን ጸረ-ህገ መንግስትና ጸረ-ዲሞክራሲ የሆነ ትዉልድ ገዳይ መልክዕክት ያሰራጫሉ ከመንግስት ባንወጣ የሚባለዉ በምርጫ ተወዳድሮ ስልጣን ከያዘ መንግስት እንጂ ገና ባለፈዉ ምርጫ መንግስት በመሆኑ ከሱ አንዉጣ ከተባለ ምርጫ ለምንስ ያስፈልጋል ህገ መንግስቱስ ለምን ምርጫ ይደረግ ይላል። ዝም ብሎ መቶ አመት በነበረው ባለው መንግስት መገዛት እንጂ!!

የኛ ቀጠና በሃሳብና በሙግት በእዉቀት ፖለቲካዊ ትግል ከማድረግ ይልቅ በኋላ ቀር አስተሳሰብና ባህላዊ ይዘት ባለዉ ፕሮፖጋንዳ እየታለልን ላለፉት 30 አመታት የዘለቅንበትና በአስከፊ ሁኔታ በሃገሪቱና በክልሉ በሚሰጡ ልማቶች ላይ እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ተቋዳሽ ሳንሆን የበይ ተመልካች ሆነን መቅረታችን ምክንያቱ እንደ ባቢሎን ሰዎች እርስ በርሳችን ሳንደማመጥ በመጠላለፍ ለጠላቶቻችን ምቹ ሁኔታን እየፈጠርን ከነበርንበት ወርደን በጎረቤቶቻችን ጭምር የወረደ ግምት ዉስጥ እንድንገባ አድርጎናል።


አሁን ግን ትግላችንና መልዕክታችን ሴረኞቹ ሆይ ይህ ህዝብ እናንተ እንዳላቹሁት የተማረዉም ይሁን ያልተማረዉ ሰው ያልሰለጠነ ምንም የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የሌለዉ ፈሪና በፍርፋሪ የሚታለል እንደሆነና እርስ በርሱ በመከፋፈል ለወደፊቱም ቢሆን ረግጣችሁ የምትገዙት አንደሆነ ትናገራላችሁ።


"ለምን? ብሎ ከሞገተ! ደግሞ በተላላኪዎቻችሁ ስታስፈራሩትና ስታስጨንቁት ዛሬም መሬት ላይ ወድቆ የሚለምን ህዝብ እንደሆነ አድርጎ ማሰብ የውድቀታችሁ መጨረሻ ነዉ"።


ሌላው... በአብዛኛዉ የሃገሪቱ አካባቢዎች አመራሮች የልማት ስራ እየሰሩ ቢሆንም የኛ አካባቢ ግን ህዝቡን በልማት ሳይሆን በጩኸት በስብሰባ ጋጋታ ረፍት ሚከለክል መሪ በአካባቢያችን በገፍ በመፈጠሩ ብዙ ሰዎች ቡታጅራ እና አካባቢዉ ያለዉ የምርጫ ቅስቀሳ ሲመለከቱ ለመሆኑ ስንት የፓርላማ ወንበር ነዉ በዚህ ምርጫ ክልል ያለዉ ይላሉ። ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲ በላይ የግለሰብ እጩነት አስጨንቆን በዞኑ አመራር አካላት ለልማት ትኩረት ያልነበረዉ ቀጠና ለምርጫ ስራ በጀት እና ትኩረታቸዉ በመመደብ እዚህ ቀጠና ላይ ሲያደረጉ ጉዳዩ ብልጽግና ከማስመረጥና ካለማስመረጥ ጋር የሚያያዝ አይደለም። ምክንያቱም የዚህ ቀጠና አጀንዳ ከምርጫ በላይና የሴረኞችን ገመና አጋልጦ ለፌድራል መንግስቱ የሚሰጥ እና የቀጣይ ጊዜ መጻኢ አድላችንን መንገድ የምንከፍትበት በመሆኑ ይህንን አጀንዳችንን ለማዳፈን የማይቆፈር ጉድጓድ የለም።


በተባባሪነት የሚተዉኑት የኛዎቹ ደግሞ ወይ ከመረጃና ማስረጃ በመነሳት የህዝባቸዉን ጭቆናን ማይታገሉ በአለቆቻቸዉ ጭምር ኮባና ገለባ የተባሉና ቅርብ ወራጅ የሆኑ ጭንጋፍ አመራሮች ያሉን በመሆኑ ለአደናቃፊዎቻችን ትልቅ አድል በመስጠት ማህበረሰባችንን በተለይም የገጠሩ ህዝባችንን ለዳግም ጭቆናና ሽያጭ በዉሸት እያደነዘዙ ለጌቶቻቸዉ አላማ ማሳኪያ አድርገዉ እያዘጋጁት ይገኛሉ ባይሳካላቸዉም ቅሉ ::

በመጨረሻም መልዕክቴ በሃገር ዉስጥና በዉጭ ሃገር ያላችሁ የቀጠናዉ ተወላጆች ህዝባችሁ ከጨቋኞች ነጻ ለማዉጣትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ከምንግዜዉም በላይ የናንተን የፖለቲካ ድጋፍ የሚሻበት ግዜ ላይ በመሆኑ ከቻላችሁ በአካል ገብታችሁ ምታግዙበት ካልቻላችሁ በስልክ ቤተሰቦቻችሁን እያገኛችሁ ታሪካዉ ዉሳኔ እንዲያሳርፍ እንድታደርጉ በታፈነው ህዝብ ስም እጠይቃለሁኝ!!


ከተቸገሩት ድሆች አፍ መንጠቅ /SNATCHING FROM THE POORS/

በተቻለኝ አቅም እዚህ አካባቢ ባሉ የበታች አመራሮችን ችግሮች ላይ አስተያየትና ትችት ላለመስጠት ወስኜ ነበር ሁኔታዉ ግን አመራሮቻችን ከመሻሻል ይልቅ እፍረተቢስና አምባገነን/shameless and arrogant/ እያደረጋቸዉመጥቷል።

የሌብነት ሰንሰለቱም ከዞን አስከ ወረዳ እየተጠናከረ የአካባቢዉን ፖለቲካና ኢኮኖሚ በሚጎዳ መልኩ ህዝቡን ለአረመኔዎች አሳልፎ እሰከ መስጠት እየደረሰ ስለሆነ ለመተቸትና ለማሳሰብ እሞክራለሁ በተለይም በምስራቅ መስቃን ወረዳ አካባቢ ያሉ የፊት አመራሮች የከፋ እየሆነ መጥቷል፡፤ ባለፉት ሶስት አመታት በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለዉ ለነበሩ ማህበረሰቦች በተለያዩ አካላት የሚቀርቡ የሰብዓዊ ድጋፎች እየተዘረፉ በባጃጅ እየተጫኑ ሲሸጡ ከርመዋል ፤፤ በድጋፍ የተገኙ አልባሳትና ጫማዎችም ለተጎጂዉ ከማድረስ ይልቅ ለቤሰተሰብ ማልበስና የቀሩትን አስከ መሸጥ ለእርዳታ የቀረቡ በጎች እና የቁም እንሰሳትን በማሸሽ መዝረፍ ደረጃ እንደተደረሰ መረጃዎች አሉን።

የወረዳዉ የፊት አመራሮች በመቶ ሺ የሚቆጠር ገንዘብ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ከግለሰቦች አስከመበደር እና አለመክፈል እያየን ነዉ:: እንደአሰራር ከግለሰብ የሚደረግ ብዱርም ክፍያዉም ህገ ወጥ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። በተፈናቃይስም ከዉጭና ከሃገር ዉስጥ የሚሰበሰቡ ገንዘቦችም ኦዲት ተደርገዉ አስካልታወቁ ድረስ ለርዝራዥ ጁንታዉ የኢኮኖሚ አቅም በመፍጠር ፖለቲካዉን ከህዝብ ፍለጎት በራቀ ለአለቆቻቸዉ ባስደሰተ መንገድ ለመምራት መንገድ እየከፈተ ይገኛል።

በቅርቡም ለአመታት ሜዳ ላይ ወድቆ የተረሳዉን ህዝብ በተጀመረዉ ትግል ምክንያት ትኩረት አግኝቶ ከፌድራል መንግስት ጀምሮ ወደ ቀዬህ በቅርቡ ልመልስህ ግብረሃይል አደራጅቻለሁ የ50 ሚሊየን ብር የእርዳታ አልባሳትና ቁሳቁስም እምጥቻለሁ በማለት ምርጫን ለመሻገር እና ሚስኪኑን ህዝብ ለመሸምገል የሚሯሯጡ ነዉረኞች ማየት ጀምረናል።

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ብልጽግና በምግብ ዋስትና ችግር ምክንያት የሴፍትኔት ድጋፍ ከሚደረግላቸዉ ሚስኪኖች ላይ ለምርጫ ስራ ብሎ በየወሩ 100 ብር እየነጠቃቸዉ እንደሆነ አረጋግጠናል። በአጠቃላይ በዚህ ወረዳ ላይ በፊት አመራሮች በየጊዜዉ የሚደረጉ አሳፋሪ ድርጊቶች ከመሻሻል ይልቅ እየባሰባቸዉ ሲሆን መሪዎቹም ለበላይ አለቆቻቸዉ ታማኝነታቸዉን በማሳየታቸዉ አይነኬሆነዉተቀምጠዋል።


በቅርቡ የመጣዉን 9 ተሳቢ እርዳታ ለመመንተፍ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነም ጭምጭምታዎች እየሰማን በመሆኑ የሚመለከተዉ የጸረ ሙስና የጸጥታ አካልና ስነ ምግባር መከታተያዎች ገብታችሁ አስካሁን ያለዉን ድርጊት እንድትመረምሩ እንዲሁም ተፈናቃዮች አይኖቻችሁን ነቃ አድርጋችሁ ንብረታችሁን እንድትጠብቁ አሳስባለሁ።


ታዬ ተስፋዬ ስሜ

48 views0 comments

Comentários


bottom of page