• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የአክሱም ጅምላ ጭፍጨፋ ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ የሐሰት ሆነ


ሰሞኑን በትህነግ የማህበራዊ ሚዲያ ጀሌዎች (ዲጂታል ወያኔ) በአክሱም የተደረገ የጅምላ ጭፈጨፋ ማስረጃ ነው ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ የሐሰት ሆኖ መገኘቱ ተገለጸ።

በትግራይ አክሱም የተነሳ ነው ተብሎ ሰሞኑን የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ መሆኑን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ነው።

በትግራይ አክሱም የተጨፈጨፉ ሰለባዎች ተብሎ ሃሰተኛ መረጃ ሲሰራጭ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ለዚህም ማስረጃ እንዲሆን ከሰሞኑ ከማህበራዊ እስከ ዓለምአቀፍ ሚዲያ በምስል የተደገፈ መረጃ በስፋት ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወሳል።

ሆኖም በማስረጃ በተደገፈ የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ባደረገው ማጣራት ፎቶው በኖቬምበር 2020 በናይጀሪያ የተነሳ መሆኑን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ጨምሮ ገልጿል፡፡ (ኢቢሲ)

37 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean