top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“የኢፍትሃዊነትና የእኩልነት እጦት የችግሮች ሁሉ ስር ናቸውና ግዜ ሳንሰጥ አሁኑኑ ታግለን ማስቆም እንጀምር” (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)


“የኢፍትሃዊነትና የእኩልነት እጦት የችግሮች ሁሉ ስር ናቸውና ግዜ ሳንሰጥ አሁኑኑ ታግለን ማስቆም እንጀምር”   (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)
  • የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል አድሎች መጨናገፍና የወደፊት እጣ ፋንታው

የቡታጅራ ሆስፒታል በቆራጡ የቡታጅራና ዙሪያዋ ወረዳዎች ህዝቦች ሃብት ጉልበት ጥረትና ትጋት የተገነባና ለብዙሃን ህዝቦች የጤና አገልግሎት ተስፋና መከታ ተደርጎ የሚወሰድ ሆስፒታል ነበር:: በጉራጌና ስልጤ ዞን ደረጃ ብቸኛዉ ሆስፒታል የነበረ ሲሆን በነበረዉ አፈጻጸምና ባለዉ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ በመመረጡ ለተወሰኑ አመታት የተፋጠነ የጤና መኮንኖች ፕሮግራም በሚል ባለሙያዎችን ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ደረጃ ተማሪዎችን በጤና መኮንንነት እያሰለጠነ አስመርቋል፡፡ በርካቶችም ትምህርታቸዉን አሻሽለዉበታል፡፤ ከአገልግሎት ሽፋን አንጻርም ሆስፒታሉ የወራቤ ሆስፒታል እስኪከፈት ድረስ ከ2 ሚሊየን የሚልቁ ዜጎች የሚጠቀሙበት የነበረ ሲሆን እንዲሁም የወልቂጤ ዩንቭርሲቲ የጤና ካምፓስ እሱን ታሳቢ በማድረግ ሊከፈት እንደሚችል ተነግሮ ነበር፡: ይሁን እንጂ በጉራጌ ልማት ማህበር አዲስ ሆስፒታል ወልቂጤ ላይ ሲጀመር ሃሳቡ ተሰረዘ፡፡ በድጋሚ በጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ አማካኝነት በተገኘ የእርዳታ ድጋፍ ከ300 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ ሆስፒታሉ በየዘዉ 70 ሺ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ተጨማሪ ማስፋፊያዎችን በመገንባት ዘመናዊ ቁሳቁሶች እንደሚሟሉለት በማድረግ የምርምርና የማሰልጠኛ ኮሌጅ እንደሚሆን ቃል ተገብቶ ሚኒስትሩ ስራቸዉን ሲለቁ ጉዳዩን ሚከታተል አካል በመጥፋቱ የተገኘዉ ፈንድም ወደ ሌላ ቦታ እንደሄደ ይመጣል የተባለዉም ዘመናዊ መሳሪያዎች ለሌላ ሆስፒታል እንደተሰጠ የሚያዉቁ ግን መረጃዉን ደብቀዉ ዝም ያሉ አመራሮች እንዳሉ ሰምቻለሁ፤፤ እነዚህ አድሎች አጥቶ ሲያበቃ ከሱ ኋላ የመጡና አዲስ የተገነቡት ሆስፒታሎች ስፔሻላዝድና ሪፈራል ሲባሉ ለምን ሪፈራል አይደረግልንም ተብሎ ሲጠየቅ በዞን ደረጃ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ ስለሚፈቀድ ተሸቀዳድመዉ ግንባታዉ ያላለቀለት የወልቂጤ ዩንቭርሲቲዉን ሪፈራል ሆስፒታል ብለዉ ሰይመዉታል፤፤ የቡታጅራ ሆስፒታል ግን ለዞኑ እንደ ማደጎ ልጅ እንጂ እንደ የራስ ልጅ ማሳደግና አድል መስጠት ባለመቻሉ ዛሬ እንኳን በበቂ ደረጃ በቁሳቁስና በሰዉ ሃይል አደራጅቶ ሪፈራል አድርጎ ህዝቡን ችግር መፍታት ቀርቶ አጠቃላይ ሆስፒታሉንም ይዞ መቆየቱ አጠራጣሪ አድርጎታል:: ስለሆነም ህዝብ ሆይ መረጃዉን አጣራ እንደሌሎቹ ሁከት ግርግር በመፍጠር ሳይሆን በጨዋ ደንብ ሞግተህ ጉልበትህ ሃብትህ አፍስሰህ የደከምክለትን ሆስፒታልህን ከማደጎ ቤት አዉጥተህ እራስህ እንደ ልጅ አሳድግ፡፡

የግርማ ወልደጎርጊስ ፋዉንዴሽን ፕሮጀክቶች አንዱ ሁከትትና ብጥብጥ አስነስቶ በለዉጡ መንግስት ሲገነባ አንዱ ሁከት ቀርቶ አስታዋሽ አጥቶ መቅረቱ ያስተዛዝባል

በዞኑ የግርማ ወልደጎርጊስ ፋዉንዴሽን ቃል የገባቸዉ የወልቂጤ ሆስፒታል ግንባታ ሆስፒታላችን ተሰረቅን በሚል ነዉጥ አስነስቶ በክልሉና በፌድራል መንግስት ትብብር በ600 ሚሊየን ብር ወጪ ግንባታዉ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በተመሳሳይ አድል የቡታጅራዉ 110 ሚሊየን ብር ትምህርት ቤት ግንባታ መሰረት ድንጋይ ተጥሎለት በጋዜጣ ብቻ ተነግሮ መጥፋቱ ችግሩ ከማን ይሆን ከህዝቡ ከአመራሩ ወይስ የጉራጌ አመራሮች ትኩረት ማጣት ወይስ እንደተለመደዉ የማደጎ ልጅነቱ እዚህም እንደጠለ ነዉ፡፤ምላሹን የቡታጅራ ከተማ የቀድሞ አመራሮች ይስጡበት አመጽ ባይቀሰቅሱበት እንኳ ለክርክር መረጃ ለምን ለህዝቡ አይሰጥም ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ይሉሃል ይሄ ነዉ አጀንዳ ይዘህ ጠይቅ ሞግት ይመለስልሃል፡፡

ለመጠናቀቅ ያልታደሉት የጉራጌ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤትና የጥያ ባህል ማዕከል ግንባታ**

የጉራጌ አንድነትን ለማጠናከር አንድ የጋራ የልማት ማህበር መመስረትና በጋራ መልማት ያስፈልጋል ተብሎ የጉራጌ ባህልና ልማት ማህበር በመመስረት ቴሌቶን 2002 ታዉጆ ከተሰበሰበዉ ገንዘብ ዉስጥ 20% ለዞናዊ ፕሮጀክቶች ተብሎ አምስት ፕሮጀክቶችን ማለትም የቡታጅራ የልማት ማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ግንባታ፤ የወልቂጤ ሆስፒታል ግንባታ የአዲስ አበባ ባህል ማዕከል ግንባታ፤ የጥያና የጉብሬ የባህል ማዕከል ግንባታ ሲሆኑ፡፤ በእቅዱ መሰረት የመጀመሪያ መሆን ያለበት እንደማንኛዉም ዘላቂ የልማት ፕሮግራም አስፈጻሚ ተቋም የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ግንባታ መሆን ነበረበት ሆኖም ወልቂጤ ከተማ ላይ ሆስፒታል ባለመኖሩ ቅድሚያ ይሰጠዉ መባሉ ምንም ችግር የለዉም በዛ መሰረት የወልቂጤ ሆስፒታል ተጀምሮ 40 ሚሊየን ብር አካባቢ ከወጣበት በዋላ የተሰበሰበዉ ገንዘብ አለቀ በመባሉ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ ወልቂጤ ዩንቭርሲቲ እንዲረከበዉ ተደርጎ አንደኛና ሁለተኛ ፌዝ ተጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል ፡፡ በድጋሚ ለረጅም ግዜ ቡታጅራ መሃል ከተማ ላይ በቆርቆሮ ታጥሮ የቆመዉን የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ይገነባል ተብሎ ሲጠበቅ የአዲስ አበባዉን ባህል ማዕከል ለመስራት ከወረዳዎች በጀት በማሰባሰብ ለመስራት ተሞከረ ባይጠናቀቅም ቅሉ ፡፡ 2010 ላይ የቡታጅራ ከተማ ህዝብ በልማት ማህበሩ የተወሰደዉ መሬት የከተማዉን ገጽታ አበላሽቷል እንዲሁም በርካታ አቅመ ደካሞችን ከእንጀራቸዉ አንስቶ የጣለ መሆኑ ተረስቶ ቦታዉ ያለ ግንባታ 8 ዓመት ታጥሮ መቀመጡ ተገቢነት የለዉም ብሎ ማህበረሰቡ ሲጮህ 12 ሚሊየን ብር ከወረዳዎች ተለቃቀመና መሰረትና ኮለን ካቆመ በዋላ በጀት የለም ተብሎ ለሁለት አመት ቆይቶ ሲያበቃ ልማት ማህበሩ የቡታጅራ ዋና ጽ/ቤት እና በመሰረተ ድንጋይ ላይ የቀረውን የጥያ ባህል ማህከል ፕሮጀክቶችን በመተው አዲስ ፕሮጀክት በመቅረጽ ጉብሬ ላይ አዳሪ ትምህርት ቤት እንገነባለን ተብሎ ሌላ እቅድ በማምጣት በ113 ሚሊየን ብር በአስተዳዳሪዉ አማካኝነት በአንድ ሳምንት ዉስጥ በመወሰን ግንባታዉ ተጀምሮ በመፋጠን ላይ ይገኛል። ለመሆኑ በበጀት የለንም ምክንያት ለዘመናት ተገትሮ የቆመዉ የቡታጅራ ከተማዉ የማህበሩ ዋና ጽ/ቤትና የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል እና በመሰረተ ድንጋይ ደረጃ የቀረዉ የጥያ ባህል ማህከል ግንባታ ለማከናወን የጠፋዉ ገንዘብ ለጉብሬ አዳሪ ት/ት ቤት ከየት መጣ መልሱን ሚያዉቅ ይስጥ ለእኔ ግን አስካሁን የገባኝ ነገር ቢኖር ቡታጅራ ላይ ወይም ጢያ ላይ ታቅዶ ያልተሰሩትን ህንጻዎች ገንብቶ መጨረስ ያልተፈለገዉ በሰላቢ ፓለቲካ የተካኑት አንዳንድ የጉራጌ ካድሬዎች ፍላጎት እንጂ በአቅም ማነስ አይመስለኝ በነሱ እሳቤ እነዚህን ፕሮጀክት ሌላ ጋ መስራት እንደኪሳራ ስለሚቆጠር እንደሆነ አምነን መታገል ይገባናል፡፤


ዞናዊ ትላልቅ ተቋማት ግንባታ ኢፍትሃዊነቶች

ትላልቅ የመስኖ ተቋማት ግንባታ ኢፍትሃዊነት

በዞኑ ዉስጥ በክልል መንግስት በጀትና በፕሮግራሞች የሚገነቡ ከ150-250 ሚሊየን ብር ወጪ የሚወጣባቸዉ መስኖ ተቋማት መስኖ እንብዛም በማታወቅባቸዉ አካባቢዎች እየሰተሩ ሲሆን ወደ እነዚያ አካባቢ የመጡበት መንገድ ፖቴንሺያልን መሰረት ያደረገ ነዉ ማለት ይከብዳል በተቃራኒዉ መስኖ ልማት ልምድ ያደረጉና ለማልማትም ዝግጁ የሆኑ የሶዶ የመስቃንና ማረቆ አካበቢዎች ተገቢዉን ትኩረት ሳይሰጣቸዉ ቆይተዋል ስለሆነም በሙህር በቸሃ በእዣ በጌታ እና እነሞር የተሰሩ ስራዎች በነዚህ አካባቢ መሰራት ይኖርበታል:: ይህ ካልሆነ በክልልና በፌድራል ደረጃ አመራር የራሱን መንደር ታሳቢ በማድረግ የሚጎትታቸዉ ልማቶች ፍትሃዊነት አያረጋግጡም::

የመጠጥ ዉሃ ተቋማት ግንባታ ስርጭት ኢፍትሃዊነት

የመጠጥ ዉሃ ተቋማት በተመሳሳይ መልኩ በተወሰኑ ወረዳዎች በከፍተኛ በጀት ትላልቅ የዉጭ ድርጅቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ወደ ተወሰኑ አካባቢዎች በማስገባት በገጠር ቀበሌ ደረጃ 6-14 ቀበሌዎችን በአንዴ የሚያጠጡ ተቋማት ስርጭት በተመሳሳይ የክልልና የየፌድራል ባለስልጣን ያለበት ወረዳዎች ጎልተዉ ሲታዩ በምስራቁ አካባቢ ግን ትልቅ ፕሮጅክት ሚባለዉ ቢበዛ ለአንድ ቀበሌ ህዝብ የሚያጠጣ ፕሮጀክት ነዉ ስለሆነም ይህ አሰራር ተገቢነት የሌለዉ ስለሆነ ተገምግሞ መስተካከል ይኖርበታል፡፤

የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ የወረዳዎች ድልድል ኢፍትሃዊነት

የክልሉ መንግስት ባለፉት አመታት በሁሉም ወረዳዎች አንድ ሆስፒታል በየወረዳ እገነባለሁ ባለዉ መሰረት ለዞኖች ወረዳዎችን መርጠዉ እንዲያቀርቡ ሲጠየቅ በህዝብ ብዛት መሆን ሲገባዉ ወረዳ ነዉ በሚል ብቻ ድልድል በማድረግ ተሰራጭተዋል:: የመስቃን ወረዳ ድርሻ እንሴኖ ከተማ ላይ እንደሌሎቹ አካባቢዎች ሆስፒታል ያስፈልገናል በማለት ተጠይቆ ነበር:: ይሁን እንጂ ቡታጅራ ከተማ ላይ ሆስፒታል አለ በሚል በዚህ ህዝብ ኮታ መጣዉን ለሌሎች ትናንሽ ወረዳዎች እንዲሰጥ ተደርጓል ይህም የልማት ፍትሃዊነትን አያረጋግጥምና አሁንም ከዞኑ ወረዳዎች እንሴኖና ኬላ አድሉን አግኝቶ መገንባት አለበት፡፤

የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግንባታ ኢፍትሃዊነት

የክልሉ መንግስት ባለፉት አመታት በሁሉም ወረዳዎች አንድ ኮሌጅ በየወረዳ እገነባለሁ ባለዉ መሰረት ለዞኖች ወረዳዎችን መርጠዉ እንዲያቀርቡ ሲጠየቅ በህዝብ ብዛት መሆን ሲገባዉ ወረዳ በሚል ብቻ ድልድል በማድረግ ተሰራጭተዋል:: የመስቃን ወረዳ ድርሻ እንሴኖ ከተማ ላይ እንደሌሎቹ አካባቢዎች ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያስፈልገናል በማለት ተጠይቆ ነበር ይሁን እንጂ የመስቃን ወረዳ ኮታ ለሌሎች ወረዳዎች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ ይህም የልማት ፍትሃዊነትን አያረጋግጥምና አሁንም ከዞኑ ወረዳዎች እንሴኖና ኬላ አድሉን አግኝቶ መገንባት አለበት፡፤

· ቅጽ 4 ይቀጥላል ተከታትለዉ ያንብቡት

እባክዎ ሌሎች እንዲያነቡት የቻሉትን ያህል share ያድርጉ

ታዬ ተስፋዬ ስሜ

82 views0 comments
bottom of page