top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የየአገሩ ምሳሌያዊ አባባል


  • ዝንጀሮዎችም እንኳን ከዛፍ ላይ ይወድቃሉ፡፡ የጃፓናውያን አባባል

  • ሰባት ጊዜ ወድቀህ በስምንተኛው ተነስ፡፡ የጃፓናውያን አባባል

  • የበሰበሰ እንጨት አይቀረፅም፡፡ የቻይናውያን አባባል

  • አንዲት ውሸት እውነቶችን ታጠፋለች፡፡ የጋናውያን አባባል

  • አመድ መልሶ የሚበተነው ወደበተነው ሰው ፊት ነው፡፡ የናይጄሪያውያን አባባል

  • ለመብላት የቸኮለ አፉን ይቃጠላል፡፡ የሉሃያ አባባል

  • ሙቅ ውሃ የሆነ ጊዜ ላይ ቀዝቃዛ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የአይቮሪኮስት አባባል

  • የልብን ‹ወሬ› ከፈለግህ ፊትን ጠይቀው፡፡ የጊኒያን አባባል

  • በአፉ አጥንት የያዘ ውሻ መጮህ አይችልም፡፡ የዛምብያውያን አባባል

  • ሆድ ከፊት ለመሰለፍ አይፈራም፡፡ የናይጄሪያውያን አባባል

  • የመቃብርን ስቃይ የሚያውቀው የሞተ ሰው ብቻ ነው፡፡ የስዋሂሊ አባባል

  • አይጥ የቱንም ያህል ብትሰክር ድመት አልጋ ላይ መተኛት የለባትም፡፡ የካሜሩናውያን አባባል

  • ጨለማውን ከመራገም ሻማ ማብራት ይሻላል፡፡ የቻይናውያን አባባል

  • ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፡፡ የዙሉ አባባል

  • ትንሽም ኮከብ ብትሆን ጨለማን ትሰብራለች፡፡ የፊንላንዳውያን አባባል

  • ዕድል ስትጎበኝህ ሁሉም ሰው የምትኖርበትን ያውቀዋል፡፡ የቻይናውያን አባባል

  • ጥሩ ምክር እንደሚመር መድኀኒት ነው፡፡ የቻይናውያን አባባል

196 views0 comments
bottom of page