top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የጉራጌ ካድሬዎች እኩይ ተግባር ተጋለጠ(ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

Updated: Apr 8, 2021


የቀድሞው የመስቃን ወረዳ አስተዳደር አቶ ታዬ ተስፋዬ ስሜ ከወረዳው አስተዳደርነታቸው ለተሻለ ስራ በሚል ወደ ጉራጌ ዞን መዋቅር ወደ ወልቂጤ ከተማ ከተዘዋወሩ በዃላ በጉራጌ ዞን እና በክልሉ ቅልብ ካድሬዎች በመስቃን ህዝብ እና በመስቃን ወረዳዎች ላይ የደረሰው እና እየደረሰ ያለውን አስተዳደራዊ በደልና ጫናን በሚከተለው መልኩ ያወጉናል፡-


“ላለፉትሁለት ዓመት ያህል ማለትም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሮችና ሌሎች ሀላፊዎች በመሩዋቸዉ መድረኮች ሁሉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፊት ለፊት በመረጃና ማስረጃ እንዲስተካከሉ ታግያለሁኝ የሰነድ መረጃዎችም አሉኝ”::


1. 142 ሺሄክታር የጉራጌ ዞን መሬት ከበጀት ቀመር ዉጪ ተደርጎ ተጥሎ ዞኑ በኔ ግምት ከ100-150 ሚሊየን ብር በላይ እንዲያጣ የተደረገ ሲሆን ይህንን ጉዳይ አስከ ጫፍ ድረስ ወስጄ በመታገል የዞኑ የመሬት ሽፋን በ2011 ከ294 ሺ ሄክታር ከነበረበት ወደ 436ሺ ሄክታር እንዲመለስ በማድረጌ ያለ አግባብ ከዞኑ የተቀነሰዉን በጀት በማስመለሴ የተከፋና ቂም የያዘ የግብርና ቢሮ ሃላፊ አሁን ላይ በተሻለ የድርጅት ስልጣን ደረጃ ያለ ግለሰብ ባገኘዉ አጋጣሚ ከስራ ገበታዬ ርቄ ያለሁትን እኔን! ለማጥቃት ከአንድ የዞን አመራር ጋር እያሴረ መገኘቱ እጅጉን ያሳፍራል።


2. የመስቃንናማረቆ ተፈናቃይ ሃብትና ንብረት እንዲተካ ክልሉ በገባዉ ቃል መሰረት በ2 ወር ጊዜ አጥንተን 1670 ቤቶችና ንብረቶች በገንዘብ 371 ሚሊየን ለክልሉ ድጋፍ እንዲያገኙ ቢቀርብም ክልሉ ሃብትና ንብረት አልተካም ጣራና ግርግዳ ብቻ በማለቱ 1670 ቤት 91 ሚሊየን ብር ሰርተን በድጋሚ አቅርበናል ብቻም አይደለም በሃዋሳ በተለያዩ ቀናቶችና አዳራሾች በሆሳዕና እና በአላባ ከተማ በነበሩን መድረኮች በየመድረኩ ብጮህም ያ ሁሉ ጥናት ተትቶ ለሳር ቤት 10ሺ ለቆርቆሮ ቤት 20ሺ ይሰጣቸዉ ብሎ የክልሉ ካቢኔ ሲወስን ትክክል አይደለም ኢ-ፍትሃዊ ነዉ እዚሁ ክልል ዉስጥ የጌድዮ የሃዋሳ የወልቂጤ ከተማ በነበሩ ግጭት በተከሰተዉ ዉድመት ተገቢዉን ካሳ ተከፍሎ ሲያበቃ የመስቃንና ማረቆ ጉዳት በተለየ ሴራ በተለየ መንገድ መታየቱ እንዲታረም ብዬ ከ5 ግዜ በላይ በደብዳቤና ከላይ በጠቀስኳቸዉ መድረኮች ሁሉ በማንሳቴ መድረኮቹን በመሩ የክልሉ ቱባ አመራሮች ጭምር ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለማሸማቀቅ ሞክረዋል አስካሁንም ድረስ ተጎጂዎቹ አልተደገፉም።


3. ከፌድራልና ሌሎች አመራሮች ጋር በነበረን ግምገማ በክልሉ ያሉ ተፈናቃዮች በሙሉ አስመልሰናል ተብሎ የቀረበዉ ሪፖርት ትክክል አይደለም ብቻም አይደለም ተፈናቀዮች እርዳታ በ 3 ወር አንዴ ብቻ ነዉ ሚመጣላቸዉ ለገጽታ ግንባታ ተብሎ የሚቀርብ ሪፖርት ተጎጂዎችን ይጎዳል በማለት ሂስ አድርጌያለሁ እንዲሁም በሚዲያ ሽፋን እንዲቀርብ በመደረጉ በወቅቱ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊና ርዕሰ መስተዳድሩ የወቀሳ መልዕክት ተልኮብኛል የፌድራል አካላትም ወርደዉ ሲያጣሩም ከተባለዉ በላይ ችግር እንደነበር አረጋግጠዋል


4. በመስቃንና ማረቆ አዋሳኝ ቦታዎች የሚገኙ የሁለቱም ማህበረሰብ ህዝቦች ግጭት ምክንያት በህግ ቁጥጥር ስር ያሉት ተጠርጣሪዎች ለ2 ዓመታት ሳይከሰሱ እና ምስክር ሳይሰማ ታጉረዉ መቀመጣቸዉ ህገ ወጥ አሰራር ነው! ትክክል አይደለም እንደማንኛውም ዜጋ ፍትህ ሊያገኙይገባል ብዬ በየመድረኮች እንዲሁም የፌድራል ተወካዮችና ቋሚ ኮሚቴዎች በተገኙበት ሪፖርት በማቅረቤ አንድ የዞኑድርጅት አመራር ከክልል አጋሮቹ ጋር በመሆን ይህን ሰው ከአመራር ፑል እንዲወጣ አድርግልን በማለታቸዉ ያለ ግምገማ ከትግል እንድርቅ ተደርጌያለሁኝ። በግሌ ለእኔ እረፍት እንደሆነአምናለሁ ።


5. የቡታጅራኢንደስትርያል ፓርክ ግንባታ በ2007 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ከፌድራልና ከክልል የመጡ አካላት ጋር በመሆን እኔና የቡታጅራ የቀድሞ ከንቲባ የተከበሩ አቶ “ቶፊቅ ሞሳ”ከዞኑ አስተዳዳሪና ድርጅት ሃላፊ ጋር ዲራማ ፣ዊጣና ኢሌአካባቢ ያሉ ቁጥቋጦና ተራራማ ቦታዎችን መርጠን አሳይተናል ተቀባይነትም አግኝቷል ተብለን አየጠበቅን ባለንበት ሁኔታ ማን ቀለበሰው? ኢንደስትርያል ፓርኩን ለመገንባት ከሚመለከተው የመንግስት አካል የተጠየቅናቸው 5 መስፈርቶች በሙሉ አሟልቷል።የመብራት substation ያለውበቂ ሆስፒታል በአቅራቢያው ያለው፣ በቂ የሰው ሃይል ማግኘት የሚቻልበት፣ ከሞጆ ደረቅ ወደብ 150km ራዲየስ የሚገኝ ቦታና 150 - 300 ሄ/ር መሬት ማቅረብ የሚችል የሚሉ የተጠየቅነውን ሁሉ መስፈርት አሟልተንና ተመርጧል ተብለን ከተነገረንና በሚድያም ከተገለፀ በዋላ ማን ነው የቀለበሰው?? ቆይቶስ ዞናችን ላይ የሆነ ቦታ ተቀየረ ተባለ! ያም… ተተወና ተሰወረ ዛሬ ግን ተመርቆ አይተነዋል። የመስቃን ቤተ ጉራጌን ህዝብ ልማቱን የሚነጥቁና የሚያስነጥቁ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉ የጉራጌ ጥቂት ደካማ ካድሬዎችን አምኖ መቀመጡ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል።


6. የህዝብገንዘብ በማዳበሪያ እዳ አሳቦ መዝረፍ ማስቆም ያልቻለ መሪ ጠያቂውን ሞጋቹን ከመድረክ ገለል ቢያደርግና ፀጥ ሲል ያሸነፈ ከመሰለው ተሳስቷል የአርሶ አደር ማዳበሪያ ገንዘብ በጉራጌ ዞን በሚገኙ 5 በተለይ ደግሞ 3 ወረዳዎች ከሶዶ መስቃንና አበሽጌ ወረዳዎች በ2005 ተበድረው ያልተከፈለ ተብሎ በ2012 ከየወረዳዎቹ በጀት 68 ሚሊየን ብር የክልሉ ህብረት ስራና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋራ በመሆን ከወረዳዎች በጀት ላይ አላግባብ የተቆረጠውን በመረጃና በማስረጃ በዝርዝር ከየወረዳው statment እንዲቀርብ በማድረግ ለማስመለስ ከ1 አመት በላይ ዱላ ቀረሽ ትግል አድርገናል በመጨረሻም የተሰጠው ምላሽ አሁን ያለዉ የክልሉ አመራር አያዉቀዉም ለምን ታስጨንቃለህ ተብያለሁ በወቅቱ በ2005 ከአርሶ አደር የተሰበሰበው ገንዘብ አዋሳ ቅርጫፍ ተቀምጦ እዛው ሳለ እንዳልተመለሰ ተቶጥሮ በየቀኑ 12.5% ወለድ ለ5 አመት እየታሰበበት ቆይቶ በ2011 ወደ እዳው ተቀናሽ ተዛውሯል 5 አመት ሙሉ ገንዘቡ ከሃዋሳ የት ለሽርሽር እንደሄደ የሚያስረዳ የለም በዚህም ምክንያት 560ሺ ብር ብቻ የነበረበት ወረዳ ከአምስት አመት በዃላ 12 ሚልየን አለብህ ተብሎ ከመንግስት ከሚደረግለት የድጎማ በጀትተቆርጦ ተወስዷል። በየመድረኩ አረ… የመንግስት ያለህ! አርሶ አደሩ በመለሰው እዳ የህዝብ ገንዘብ አይቆረጥ ብልም ከንግድ ባንክ እስከ ህብረት ስራ ያሉ ከፍተኛ መሪዎች ጥርሳቸውን አፏጭብኝ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ በተመሳሳይ የወንበዴ ስራ በሚቀጥሉት 3 አመትም ከአርሶ አደር ተሰብስቦ የተመለሰ ገንዘብ አዋሳ አካውንት ላይ ተቀምጦ ከእዳው ላይ ሳይቀነስ እየወለደ መገኘቱ ነው።


ይቀጥላል


96 views0 comments

Comments


bottom of page