top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“የጤና ምስጢራዊ ቁልፍ” - በዶክተር “ፒተር ጀይ ዲ አዳሞ” - (ክፍል 01)


  • የደም ዓይነት ሕያው ዘገምተኛ ለውጥ

ደም እራሱን የቻለ ሕይወት ነው። የመወለድን ሚስጢር በሽታን የመቋቋም አቅም እንዲኖር የሚወሰነው ደም ከሚሰጠው መሠረታዊ ጉልበት በሚፈጥረው የኃይል ምንጭ ነው፡፡ በጠቅላላው የዚህች ዓለም እድገት የተገነባው በደም ሰንሰለታዊ ሐረግ ላይ ነው። በየትኛውመ የዓለም ጫፍ ይገኝ የነበረ የሰው ዘር በማኅበራዊ ኑሮው የደምን ሚስጢራዊ ይዘት በማድነቅ በደም ላይ አትኩረቱ ከማድረግ ወደኃላ አላለም ይኸውም ከአዳኙ ሰብሳቢ ዘመን ጀምሮ የደም መስዋእት ለታዳኙ እንስሳ መንፈስ በማቅረብ ከበሽታና ክፉ መንፈስ ለመዳን ሲባል ሰውነትንና ግንባርን መቀባት፤ መተማመናቸውንና እርቅ መወረዱን ለማስመስከር በሁለቱ ወገኖች እንስሳት ታርደው ደማቸውን ቀላቅሎ መጠጣት! በኦሪት መጽሃፍትም ጭምር ለአማልክታቸው መስዋእት ሲያቀርቡ እንደነበር ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ ያምሆነ ይህ በአፈታሪክ በቆየልንም ይሁን በጽሁፍ ከደም ውጪ ዘሮቻችን ሕይወት እንደሌለ ደርሰወበት ነበር ለማለት ያስፍራል፣ አሁንም ቢሆን እንደ አጉሊ መነጽር በውስጣችን የሚገኝ የደበዘዘውን ማንነታችንን አጉልቶ በማውጣት የሚያሳይና ለመኖራችን የድንጋይ መአዘን ነው።

ባለፉት አርባ ዓመታት የተደረጉ የስነ ሕይወት ምርምሮች እንደ የደም ዓይነት የመሳሰሉትን ጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ መንገዶች ፣ የቅድመ እያቶቻችን በቡድን መኖር፣ የመንቀሳቀስና የመሰደድ ካርታ እንድንነድፍ አስችሎናል፡፡ ይህንንም በማጥናት የጥንት ሰዎች በዚያ ፈታና ባለ ማቋረጥ ይለዋወጥ የነበረውን የአየር ጠባይ፣ የአመጋገብ ሥርዓትና የተዋህሲያን ጠባይ መቀያየር ውስጥ ተላምደው እንዴት እንዳሸነፉ ማወቁ እኛነታችንን እንድናጠና ረድቶናል። የአየር ጠባይ በሚለዋወጥበት ጊዜ የሚፈጠሩ አዳዲስ የአመጋገብ ሥርዓቶች ለእዳዲስ የደም ዓይነቶች መነሳት ምክንያት ሆኑ፡፡ የደም ዓይነት ምንጪ ከአንድ የደም ዓይነት የሆነ እርስ በርስ የሚያስተሳስረን የማይበጠስ ገመድ ነወ፡፡ የደም ዓይነቶች የተፈጠሩት በመሬታችን ላይ ይደርስ በነበረው የማያቋርጥ የአየር ጠባይ መለዋወጥን ተከትሎ ይመጣ በነበረው አዲስ የአመጋገብ ዘዴ ነው። የአዳዲስ የደም ዓይነቶች መፈጠር የሰው ልጆች በተለያየ አካባቢዎች ለመላመድ ትግል መጀመራቸውና ከአካባቢው ጋር የሚያደርጉትን ጥብቅ ትስስርን ያሳያል፡፡ በአብዛኛው ትኩረታችን የሚሆነው የሰው ዘር ለዘመናት በትግል ያቆያቸውን የምግብ መንሸረሸር ስርዓት (Digestive system) እና በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ስርዓት (Immune system) ላይነው። ለምሳሌ አንድ የተበላሸ ቁራጭ ሥጋ መብላት ሞት ሊያስከትል ይችላል። እንዲሁም ትንሽ ጭርት ወይም መቆረጥ ወደ ሞት የሚወስድ ምርቀዛሊያመጣ ይችላል። ሆኖም ግን የሰውረ ዘር ሁሉንም ተቋቁሞ መኖሩን እየቀጠለ ነው፡፡ እናም የሰው የአኗኗር ታሪክ_ከምግብ መንሸራሸር ሥርዓትና በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ሥርዓት ጋር የተሳሰረ ነው።

  • የሰው ዘር ታሪክ

የሰው ዘር ታሪክ በራሱ የመኖር ቀጣይነትን መተረክ ነው። በተለይ ሰዎች የት ይኖሩ ነበር፤ በአካባቢያቸው የሚያገኙት የሚበላ ነገር ምንድን ነው፤ በአጭሩ ምግብን “ማግኘት እና ምግብ ፍለጋ” መጓዝን ያጠቃልላል። የሰው ዘር እርግጠኛ ሆነን ከዚህ ዘመን ጀምሮ ከዚች ዓለም መኖር ጀመረ ማለት እንችልም፣ በአንዳንድ ሳይንሳዊ መረጃዎች እንደተቀመጠው ቀደምት የሰው ዘሮች (ነያንደርታክስ) ከ500,000 ዓመታት በፊት እንደ ነበሩ ነው።

የሰው ዘር መጀመሪያ በአፍሪቃ እንድ ተፈጠረ በትክክል ታውቋል። በጥቱ ዘመን መኖር በጣም አስከፊና ከባድ፣ ዕድሜም አጭር እንደ ነበረ ይገመታል ምክንቱም ሰዉ በወጣትነት ዕድሜው ይቀጭ ስለ ነበር ነው። የመጀመሪያዎቹ የሰው ዘሮች ምናልባት ያለበሰለ አትክልት እነ ፍራፍሬዎች እጭ እና በሌሎች ሥጋ በሎች የተገደለ እንስሳ ትራፊ በመብላት የእለት ተእለት ኑሮአቸውን ይገፉ ነበር፡፡ በወጀመሪያ የሰው ዘር ገድሎ ለመብላት ብቁ እንዳልነበረና በአብዛኛውም በሌሎች እንስሳት ይታደን እንደ ነበር በተለይም በውስጥ ጥገኞችና በወረሽኝ በሚጠቃበት ጊዜ ጉልበት ስለሚያንሰውና ማምለጥም ስለማይችል የመታደኑ ሁኔታ ይበረክት እንደነበር እንገነዘባለን፡፡

የሰው ዘር በዙሪያው የነበረ ምግብ እያለቀ በመጣ ጊዜ ከቦታው መሰደድ ጀመረ፣ ወደ እዲስ የአየር ጠባይና አከባቢ በመግባት አዳዲስ ምግቦችን ለመለማመድ ተገደደ፡፡ ይህን የአየር ጠባይና አዲስ የአመጋገብ ዘዴ ለመለማመድ በሚፍጨረጨርበት ወቅት በምግብ መንሸራሽርያ ክፍሎችና የተፈጥሮ በሽታ መከላከያ ሥርዓት ላይ ጫና ስለሚያሳድርበት

ለጊዜው ጤነኛ አይሆንም፣ ከአከባቢው ጋር እየተስማማ ሲመጣ ሰውነቱ በመዳበር ጠንካራ ሆኖ መኖር ይቀጥላል፡፡ በእነዚህ ወሳኝ ትግሎች ውስጥ ነው የደም ዓይነት መፈጠር ከሰው ዘር እድገቶች ጋር አብሮ የተከሰተው፡፡

በዚህም ምክንያት ፡

  1. የሰው ዘር እድገትና ለውጦች እያሳየና ጥበብ ያለው የእድን ስልት መጠቀም ሲጀምር የሥጋ ፍጆታው በማደጉ የደም ዓይነት “ኦ” ዎች የመንሸራሸርያ ሥርዓት ጠንካራና አስተማማኝ ብቃት ይዞ መቅርብ ጀመረ

  2. ከአዳኝ ሰብሳቢነት ወደ ተሻሻሉ የእርሻ ሰበሎች ማምረት በስፋት መልመድ ጋር የደም ዓይነት "ኤ" መጣ።

  3. የተለያዩ ዝርያዎች ከአፍሪቃ ወደ ኣውሮጳ፣ ኤስያና አሜሪካ መሰደድና መዘዋወር ሲጀምሩ የደም ዓይነት “ቢ" ታየ፡፡

  4. ዓለማችን በስልጣኔ እየተቀራረበች ስትመጣ የሰው ዘር መቀላቀልና መካለስ ጀመረ፣ ለደም ዓይነት “ኤቢ” መፈጠር ምክንያት ሆነ።

ምንም እንኳን የቅድመ ዝርያዎቻችን የኖሩበት ዘመንና እኛ በምንኖርበት ወቅት መካከል በሚሊዮን የሚቆጠር የዘመናት ርቀት ቢኖርም እያንዳንዱ የደም ዓይነት ከቅድመ ዝርያዎቻችን ጀምሮ ያለው ዘረ-መናዊ (ጀኔቲካዊ) መልእክት እንደተሸከመ ነው፡፡ ይህም አንደ የውስጣዊ ባህርያት ጥንካሬና በደም ዓይነት የአመጋገብ ስነ አመክንዮችዎች ሁኔታ እንድንረዳ እገዛ ያደርግልናል፡፡


"የጤና ምስጢራው ቁልፍ”

ተጻፈ - በዶክተር “ፒተር ጀይ ዲ አዳሞ”

ትርጉም - በዮናስ ተዛረ

19 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page