የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ጠቃሚ ምክር ለእርስዎ !

ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም:: ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!
ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም:: ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!
ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም :: በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!
አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም:: ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!
ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም:: በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!
ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም:: ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!
ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም:: ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ
ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም:: ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ!
ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም:: ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!
ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም:: ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!
ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም:: ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!
እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት አይደለም:: ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!
አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም:: ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!
ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም:: ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!
ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክ ነህ ማለት አይደለም:: አምሮብሃል ማለት እንጂ!
አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም:: ብልህ ሁን ማለት እንጂ