የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ጠቃሚ ነጥቦች ደግነት ለተሞላበት ሕይወት

የሚሰሙ መስለው መልስ ለመስጠት እራስዎን ከማዘጋጀት ይልቅ በሐቅ ሌሎች የሚሉትን ማድመጥ ይጀምሩ
በመጥፎ ሁኔታ ምላሽ ለሚሰጥዎት ሰው በመልካምነት ይመልሱ። (የሚያመነጫጭቅዎትን ሰው ያስቡና ወዳጅነት በተሞላበት ሁኔታ "ቀንህ/ሽ ጥሩ አልነበረም?" ብለው ይጠይቋቸው። በዚህም ውጥረት የተሞላበትን ሁኔታ በቀላሉ ማርገብ ይችላሉ)
በሰዎች ሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙ ነገሮች ሁሉ ችላ መባል፣ አለመፈለግና አለመፈቀር የሰውነትን ክብር የመግፈፍ ያህል ስለሆነ ችላ የተባለን ሰውን ያቅርቡ። ይህን ሲያደርጉ ለሰዎች ዋጋን ይሰጣሉ።
ከመልካምነት የራቀ ድርጊት ሲፈጸም ሲገጥምዎ የእርሶ ችግር አለመሆኑን ይረዱ። ለድርጊቱ ምላሽ እንዲሰጡ ሲገፋፉም እራስዎን ይቆጥቡና በጥልቀት ትንፋሽ ወስደው እራስዎን ያርቁ።