የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ጦርነት (ገብረክርስቶስ ደስታ)

ያዘቀጠው አሰር እየደፈረሰ የተቀጣጠለው እንጨት እየጨሰ መሬት ቁና ሁና የሰው ልጅ ሲጨንቀው እሳት ተያይዞ አገሩን ሲያለብሰው ባለቤት ተሰዶ አዱኛ ፈራርሳ አሞራ ሲያንዣብብ ተከምሮ ሬሣ ሥጋ ሲርበደበድ ነፍስ ይሽቆጠቆጣል የኔ እያቀዘፈው ደም ይገነፍሳል። ኮሽ ባለ ቁጥር ዞሮ ሲገላሙጥ እየተንሻተተ ገደሉን ሲባጥጥ ሲቃትት ሲደክም ሲርበው ሲጠማው ሥጋውን በመካድ ሞትን ይመኛል ሰው፡፡ የፍቅር ጥላነው ጭጋግ የደስታ ኀዘን መንገላታት፣ መታሠር መቸገር መቁሰል መሰቃየት የሌለው ፀጥታ ያንድነት እከክ ነው ልብሱ የነተበ በላብ በጭንቀት ገላው የረጠበ ተለዋዋጭ መልኩ ያልታወቀ ግቡ ኣልቋል ሞቷል ሲሉት ያው ይነትራል ልቡ። ሥጋ ተለያይቶ ሲቀር ኣጥንታቸው ማንንም በስሙ መጥራት የማንችለው መልካቸው ሲያጠፋ ሁነው እንዳልነበር እነሆ ርስታቸው የእኩል ቤት መቃብር፡፡ መድፍ የተከላቸው መትረየስ ዘርዝሮ ቦምብ የመገባቸው አይሮፕሳን በሮ፣ ታንክ በደነጎረው ጠመንጃ ዘርቷቸው ጢስ ወሃ እየሆነ ሲጠጡ ባፋቸው የታል የበቀሉት ወዴት ነው ቦታቸው ልምላሜአቸው የታል ፍሬያቸው የታለ ?? ሐውልቱ ያንጋዩ ምን አጎነቆለ ! ባንድ በኩል ደግሞ የሰላም ሚዛን ነው ። የበዛን አረሞ የሚያስተካከለው:: ሰላም ብዙ ሲቆይ ታምሩ ይሻግታል መሠረቱ ዝጎ ቀስ ብሎ ይወድቃል ፣
አንስቶ በመካብ የፈራረሰውን ቀብሮ በመለሰን ሲያድስ መሰረቱን
ኃይለኛ ሲገባ ሲከተል ዓላማ
ባለህ እርጋ ብሎ አዋጁን ሲያሰማ፣
ይኸው ተጀመረ አዲስ ዓይነት ሰላም
ዳግመኛ እስቲወድቅ ፈርሶ እስቲደመደም፤
ሰሳም ያቻት ብሎ ሁሉም የሚጮኸው
ክፉቀን አታምጣ ብለን የምንተቸው፣
በጸሎታችን ውስጥ መሪ እንዳያሳጣን
ወድቀን እንዳንቀ ርተገዥ በመሆን፤
ያቻት አላማችን ነፋስ ተቀበላት
ብለን የምንቆመው ሰሳም የምንላት
ሰጥታ ሲኖር ነው አልፈን በጦርነት
እንደኛው ሲተኛ ያኛው ሲጠብቀው
ሰላም ወይ ጦርነት ድርና ማግ ናቸው::
በገብረክርስቶስ ደስታ