የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ፈር ቀዳጅና ቀንዲሎቹ (በኢዱና አህመድ)
Updated: Sep 3

እንደ የትኛውም የኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የመስቃን ህዝብን ስም ለአመታት ፍጹም ከጥቅማ ጥቅም እና ከግል ዝና በጸዳ ሁኔታ ከፍ አድርገዋል። ድምጽ አሰምተዋል። እንዲሁም አንቅተዋል። ማህብረሰቤን በማለታቸውም ተተችተዋል። በተጨማሪም ተዘልፈዋል። ነገር ግን አንዳቸውም... እኔኑ ጨምሮ ከጎዞአችን ወደኋላ አላልንም።
እኒሁ የሚድያ ሰዎቹ
አወል አህመዲን
ዑመር አህመድ
ሰሚራ ቢንት ሽፋ በሚድያው ዘርፍ ለመስቃን ማህበረሰብ ድምጽን በማሰማት ፈር ቀዳጅና ቀንዲል ሆነው እንዲሁም መሰል በርካቶች በማፍራት ድልን ተቀዳጅተዋል።
ዛሬ ላይ ወይም የመስቃን ህዝብ ስኬት ከተጎናጸፈ በኋላ የድል አጥቢያ ጀግኖች ሁሉ እኔ... እኔ በሚሉበት ወቅት የእነዚህ እጹብ ድንቅ ወንድምና እህቶች ስም አለማንሳቱ ወይም አለማመስገኑ በደል ነው የሚሆነው። እናማ... እናንት ፈር ቀዳጅ እና ቀንዲል እንዲሁም መሪ ተዋናዋዮች ለአመታት ባለመታከት ላበረከታችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና በመስቃን ማህብረሰብ ስም፣ በመስቃን ሚድያ ስም እንዲሁም በግሌ ለማቅረብ እወዳለሁ።
በእርግጥ ለአመታት በነበረው የትግል ሂደት በተለያየ ዘርፍ የተሳተፉት በርካቶች ቢሆኑም ዛሬ ላይ በእናንተ ላይ ግዴታውን ከተወጣን በኋላ በተለያየ ዘርፍ ለሁለት አስርት አመታት ያህል የተሳተፉትን ሁሉ ሰንደን እናቀርባለን።
ኢዱና አህመድ ኡስማን
ቸር... እንሰንብት