የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ሐሳብ - ክፍል አንድ (በኢዱና አህመድ)
Updated: Jun 9, 2019

በእኔው ዘመን የኑሮ … ንረት
ጣሪያ በነካው የእኔው ክጃሎት
በወገኖቼ… እስርና እንግልት
በአስከፊው የዘረ አዳም…ሄዋን ስደት
በዘረ አዳም…ሄዋን ሰሚ ያጣ ጩኽት
የሃሳበ ውቅያኖስ ሰጥሜ ስዋትት
ተናገር ! እምቢኝ በል ! ዝምታው… ይብቃህ
ይከፈት! የተዘጋው አንደበትህ
የእኔ... ነው በል! የራስህን… ውሰድ
የራስን… ለመውሰድ አያሻህም! ሌላውን ማስፈቀድ
ይለኛል ያ…ሀሳቤ በሃሳብ
ለአፍታ ተዘንግቶት የዛሬው ድባብ
ሃሳብን... በሃሳብ
ሳስብ… ስብሰለሰል...በሃሳብ
ያ...ሃሳብ መጣና በሃሳብ
መለሰኝ… ወሰደኝ…
ይቀጥላል
(በኢዱና አህመድ)