top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

አባባሎች



  • የአንበሳ ጀግንነት ከአዳኝ ቀስት አያድነውም። (የአፍሪካውያን አባባል)

  • ደስተኛ ህዝብ ታሪክ የለውም፡፡ (የቤልጂየሞች አባባል)

  • ጦርነት ላልቀመሱት ጣፋጭ ነው፡፡ (የላቲኖች አባባል)

  • ሽንፈት የሚመረው ስትውጠው ብቻ ነው፡፡ (የቻይናውያን አባባል)

  • አውነት የያዘን ሆድ በበላ እንኳን አይበሱትም፡፡ (የሃውሳ አባባል)

  • እሳት ያቃጠለው ሰው ሁልጊዜ አመድ ያስፈራዋል፡፡ (የሶማሌያውያን አባባል)

  • መጥበሻው ካልጋለ ማሽላው አይፈነዳም፡፡ (የዮሩባ አባባል)

  • ዝሆን ላይ የሚጮህ ሞኝ ውሻ ብቻ ነው፡፡ (የአንጎላውያን አባባል)

  • በግድ ድስት ውስጥ የገባ አጥንት ድስቱን መስመሩ አይቀርም፡፡ (የቼዋ አባባል)

  • አይጥ የገደለ ዝሆን ጀግና አይባልም፡፡ (የካሜሩያውያን አባባል)

  • ትዕግስት የገነት ቁልፍ ነው፡፡ (የአልባንያውያን አባባል)

  • ቤትህን ከመምረጥህ በፊት ጎረቤትህን ምረጥ፡፡ (የሶሪያውያን አባባል)

  • ፈረሱ ከሚጠፋ ኮርቻው ይጥፋ፡፡ (የጣልያኖች አባባል)

  • ምንም ዓይነት ምስጢርህን ከራስህ አትደብቅ፡፡ (የግሪካውያን አባባል)

  • የሥራ ፈት ምላስ ፈፅሞ ሥራ አይፈታም፡፡ (የአፍሪካውያን አባባል)


191 views0 comments
bottom of page