የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የማህተመ ጋንዲ ምርጥ አባባሎች

እንደሰው ልጅ ትልቅነታችን ያለው የአቶሚክ ዘመን ተረት ተረት እንደሚነግረን ዓለምን እንደገና ለመስራት በመቻላችን ላይ ሳይሆን ራሳችንን ዳግም ለመስራት ያለን ችሎታ ላይ ነው።
ማንም ሰው እኔ ሳልፈቅድለት ጉዳት ሊያደርስብኝ አይቻለውም።
የወደፊቱን ጊዜ አስቀድሜ ማየት አልሻም። የሚያሳስበኝ የአሁኑን ጊዜ መንከባከብ ነው። ቀጥሎ ስላለው ቅጽበት አምላክ ምንም ዓይነት ቁጥጥር አልሰጠኝም።
በራስ ጥበብ በጣም እርግጠኛ መሆን መልካም አይደለም። ጠንካሮች ሁሉ እንደሚደክሙ እና ጠቢባንም እንደሚሳሳቱ ማስተዋል ይጠቅማል።
በመጀመሪያ እነሱ ቸል ይሉሃል። ከዚያ ይስቁብሃል። ከዚያ ይፋለሙሃል። ከዚያ አንተ ታሸንፋለህ።
ደካሞች ይቅር ማለት አይቻላቸውም። ይቅር ባይነት የጠንካሮች ብቻ ባህሪይ ነው።
ከኩንታል ሙሉ ሰበካ ይልቅ አንዲት ኪሎ ድርጊት ትበልጣለች።
የሰዎችን መልካም ገጽታ ብቻ ነው የምመለከተው። እኔ ራሴ እንከን የለሽ ስላልሆንኩ የሌሎችን እንከን የምቆጥርበት ምክንያት የለኝም።
ደስታ ማለት የምታስበው፣ የምትናገረው እና የምታደርገው ሲስማሙ ማለት ነው።
የማያቋርጥ እድገት የተፈጥሮ ሕግ ነው።