top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

እሳት አንዳጅ (አቀጣጣይ)እሳት አንዳጅ

ለአመታት ለአሰሪው እሳት በማንደድ ሲያገለግል የነበረ ጎልማሳ ክፍት ይለውና ሲያገለግል ከነበረበት ለማንም ሳያሳውቅ ጥሎ ለመሄድ ይወስናል ከመሄዱ በፊት ግን እርሱ ሳይኖር የሚከሰተውን ለማየት ይጓጓና በአቅራቢያቸው በሚገኘው ኮረብታ ላይ በመሆን ወደ አሰሪው ቤት በማነጣጠር ይጠባበቅ ጀመር፡፡

ለአመታት በታማኝነትና በታታሪነት በማገልገሉ ያለእርሱ እንደማይሆንላቸው ሙሉ እምነት አለው በተጨማሪም የማቀጣጠሉን ተግባር እንደ እርሱ የተካነው ከአገልጋዮቹ መሃል እንደሌለ እርግጠኛ ነበር፡፡ በእርሱ አለመኖር የሚደርስባቸውን ትርምስ እያሰላሰለ ፊቱ ፈካ… አለ ብዙም ሳይቆይ በቁጭተ ሀሳቡ "ደሞ… እኮ አለ ደረቅ እንዲሁም እርጥብንም ቢሆን ያለምንም እንከን ማቀጣጠሉን ማያያዙን ከኔ ወዲያ የተካነው የለም፡፡ በጌቶችም አድናቆት እደተቸረኝ እንዲሁም ከቀዬው እኔን የሚደርስ እንደሌለ ሲነገር ሰማን… ያሉ አውግተውኛል"፡፡ ግን ምን በደልኳቸው ? ለምንስ ተለወጡብኝ ? እያለ በማሰላሰል ላይ ሳለ ወቅቱ መድረሱ አይቀርምና አመሻሹ ላይ ግቢው በነበልባል ደመቀ አይኑን ማመን አቃተው የአቀጣጣዩን ማንነት መለየት ቢያዳግተውም እሳቱ ልክ በወቅቱ ነበር የተያያዘው:: የነበልባሉም ውበት እንደዚህ ደምቆ በእድሜው ታይቶት አያውቅም። በአግራሞት ሲመለከት ቆየቶ አይ እሳት አለ በለሆሰሳ “ውበቱ ማራኪ ጥቅሙ ጉዳቱ ዘርፈ ብዙ እሳት ማቀጣጠሉን በእሳት ማያያዙን ሁሉም ተክኖታል። ለካስ እንዲህ ቀላል ኖሯል”? የመሄዱን ሚስጢር ለማንም ባለማካፈሉ ወደ አሰሪው ቢመለስ ችግር እንደማይገጥመው ራሱን በማሳመን አቀና።

ይቀጥላል


25 views0 comments
bottom of page