top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ይህ የሚጠበቅ ነገር እና ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)የAssociated_Press ጋዜጠኛ Elias Meseret Taye ከአቶ #በረከት_ስምዖን ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ

ጥያቄ: በመጀመርያ ብአዴን ሰሞኑን እርስዎ ላይ ስለወሰደው እርምጃ እናውራ። እርምጃው የተወሰደበት አካሄድ ምን ይመስል ነበር? እርስዎስ እንዴት ያዩታል? ተቀብለውታል?

አቶ በረከት: መሰረተቢስ እርምጃ ነው። እንዲታወቅ የምፈልገው እኔ ስብሰባው ላይ እንዳልነበርኩ እና ይህንንም ለእነርሱ ማሳወቄን ነው። ይህም የሆነው በአሁኑ ሰአት በክልሉ ላይ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው። በአሁን ሰአት ክልሉ ላይ የህግ የበላይነት የለም። እርግጥ እየሆነ ያለው የደቦ ፍርድ (mob justice) ነው። ይህንንም የክልሉ መንግስት መቆጣጠር የቻለበት ሁኔታ አይታይም። የተጠቀሰውን የንግድ ድርጅት በተመለከተ ስለተባለው ጉዳይ ያለኝ ሪከርድ ይመሰክራል። በእኔ አስተዳደር ምንም የጠፋ ነገር የለም። እንደ እኔ አስተሳሰብ ይሄ እርምጃ የመጣው አንደኛ ምክትል ጠ/ሚሩን በቅርቡ በተካሄደው የመተካካት ወቅት አለመደገፌ፣ በአቋሜ የማልደራደር ስለሆነ እና ፊት ለፊት ስለምናገር እንዲሁም የማጥራት አካሄድ (cleansing move) ነው። ምክንያቱም በረከት ከተለየ አካባቢ የመጣ ነው ስለሚባል ነው። እርግጥ ቤተሰቦቼ የኤርትራ ስር መሰረት ቢኖራቸውም እኔ ተወልጄ ያደግኩት ጎንደር ነው። የንግድ ድርጅቱን በተመለከተ አመታዊ የኦዲት ሪፖርት አለው። የእኛ ድርጅት ከኤፈርት ድርጅቶች አንደኛ ነው ታክስን በመክፈል ጨምሮ። በዚህ እኔ እርግጠኛ ነኝ

ጥያቄ: በብአዴን የተወሰደውን እርምጃ ሲሰሙ አዘኑ፣ ደነገጡ ወይስ ሌላ ስሜት አጫረቦት?

አቶ በረከት: ይሄ የሚጠበቅ ነገር ነበር። ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)። ወደፊት ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ይመጣሉ ብዬ እገምታለሁ። እኔ ላይ ግን ምንም ችግር ይመጣል ብዬ አልፈራም ምክንያቱም ንፁህ ነኝ በዛ ላይ ለመብቴ እታገላለሁ።

ጥያቄ: የጠ/ሚር አብይን ፈጣን ለውጦች እንዴት ያዩዋቸዋል?

አቶ በረከት: በእርግጥ ጠ/ሚሩ እየተገበሩት ያለው ለውጥ ኢህአዴግ ባለፈው ዲሴምበር ያሳለፈውን ነው። ሁላችንም የዚህ ለውጥ አካል ነበርን። ስለዚህ ስለ ለውጥ አስፈላጊነት ምንም ጥርጥር የለኝም። ጥሩ ለውጦች እያየን ነው።

ጥያቄ: ከሳምንታት በፊት እርሶ አሉበት ተብሎ የታሰበ በአማራ ክልል የሚገኝ ሆቴል እና መኪና ጥቃት ደርሶበት ነበር። ጥቃቱ አላስደነገጥዎትም? እርስዎስ በወቅቱ እዛ ነበሩ?

አቶ በረከት: በወቅቱ እኔ እቤቴ እንጂ እዛ አልነበርኩም። ይህ የሚሳየው ግን በክልልሉ ያለው አስተዳደር ቁጥጥር ማጣቱን ነው። ህግ ያለው በቡድኖች እጅ ሆኖዋል።

ጥያቄ: የወደፊት የፖለቲካ ህይወቶ ምን ሊመስል ይችላል? ወይስ ፖለቲካ በቃዎት?

አቶ በረከት: አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከእኔ ግለ- አስየሳሰብ ጋር አብሮ ስላማይሄድ አልቀጥልም። I'm thinking of coping with it Lidetu's style (የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)። አሁን ያለው ሁናቴ ፖለቲካን fair በሆነ መልኩ ለማካሄድ ያመቻል ብዬ አላምንም።

ጥያቄ: በቅርቡ የቀድሞው ጠ/ሚር ታምራት ላይኔ ባለቤት እርስዎ ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። እርሳቸው በመታሰራቸው በእርግጥ ደስተኛ ነበሩ? ከሆነስ ለምን?

አቶ በረከት: የእርሱ ጉዳይ በፍርድ ቤት ተወስኖ ከዛ ደሞ በህግ መሰረት ተፈቷል። 12 አመት ትምህርት ካላስተማረው እኔ ምንም ማረግ አልችልም። እስር ላይ የቆየው ባላደረገው ነገር አይደለም። ማንም ጣቱን ወደ እኔ አሁን ላይ ቢቀስር ለእኔ ምንም ማለት አይደለም።

ጥያቄ: አንድ ምክር ለጠ/ሚር አብይ ለግሷቸው ብልዎት እርሱ ምን ይሆናል?

አቶ በረከት: እኔ እየሰራህ ያለውን ጥሩ ስራ ቀጥልበት ነው የምለው። ቃል የገባሀቸውን ነገሮችም ፈፅማቸው ልለው እወዳለሁ። ይህ የይቅርታ እና ምህረት ግዜ ወደፊትም መቀጠል አለበት። ዋናው ግን ይህ ሀገር sensetive ስለሆነ የ balance ስራ ሁሌ መሰራት አለበት። ጠ/ሚሩ እንዲሳካላቸው እመኛለሁ።

ጥያቄ: ጠ/ሚሩ ሹመት ሊሰጥዎ አስበዋል እንበል። ሹመቱን ይቀበላሉ ወይስ በተቃራኒው?

አቶ በረከት: በፍፁም! የእስካሁኑ ይበቃኛል።

ማሳሰብያ: ይህ ለ Associated_Press ዜና ታስቦ የተደረገ እና አንድ ሁለት አንቀጽ ከእሳቸው ለማግኘት ታስቦ የተደረ ቃለ መጠይቅ ነው። ስለዚህ አላማው ለአለም አቀፍ ዜና መሆኑን ተረድታችሁ ይሄንን ሳይጠይቅ፤ ያንኛውን ሳያነሳ እንደማትሉ ተስፋ አረጋለሁ።


10 views0 comments
bottom of page